👉ሀገር በቀል ህንጻ ተቋራጮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድሆኑ በትኩረት እየተሰራ ነው- የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት
ሀገር በቀል ህንጻ ተቋራጮች ከሀገር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታምራት ሙሉ(ኢ/ር) ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት የኮንስትራክሽን ዘርፉ በቴክኖሎጂ የዘመነና ተወዳዳሪ እንዲሆን ኢንስቲትዩቱ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ነው።
በዘርፉ ላይ ተወዳዳሪና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት ለዘርፉ ባለሙያዎች፣ ተቋማትና ህንጻ ተቋራጮች የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በተለይ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የህንጻ ተቋራጮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የክህሎት፣ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ክፍተትን ለመሙላት እየተሰራ ያለውን ስራ ለአብነት አንስተዋል።
ይህንን ተከትሎ የሀገር ውስጥ ህንጻ ተቋራጮች በሀገር ውስጥ ህንጻዎችን ጨምሮ እየተገነቡ በሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ለኢንዱስትሪው ሽግግርና የቴክኖሎጂ እድገት ከፍተኛ ሚና ባለው የቢውልዲንግ ኢንፎርሜሽን ሞዴል ወይም(BIM) ላይ የህንጻ ተቋራጮች፣ የዘርፉ ምሁራንና ኢንዱስትሪዎች በቴክኖሎጂው ዙርያ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የማድረግና የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል
የፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮፌሽናል ትሬኒንግ የተሰኘው ስልጠናም ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውና የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ለውጥ የሚያመጡ እንደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሳሰሉ ፕሮጀክቶችን የሚመሩ ባለሙያዎችም ስልጠናውን እንዲወስዱ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት 89 ባለሙያዎች ስልጠናውን አጠናቀው አለም አቀፍ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ማረጋገጫ ወረቀት መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።
የኮንስትራክሽን ዘርፉ በቴክኖሎጂ የዘመነና ተወዳዳሪ እንዲሆን ኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
Via Construction Management Institute
@etconp