👉የወቅቱ ሪል ስቴት ኢንቨስትመንት አደጋዎች
የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት የሚያስገኘው ጥቅም ከፍ ያለ ቢሆንም የራሱ የሆኑ ተግዳሮቶችና አክሳሪ ሁኔታዎች ( Investment Risks) ያሉት ነው።
በዚህ ወቅትም የሀገራችን የሪል እስቴት ዘርፍ በፈታኝ አክሳሪ ሁኔታዎች እየተመታ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች የዘርፉ የኢንቨስትመንት አደጋዎች ብለው ያቀመጧቸውና የሪል እስቴት አስተዳደርና ግብይት መጽሃፌ ላይም የተገለጹት ዝርዝር ማሳያዎች ውስጥ የእኛን ሀገር ወቅታዊ ሁኔታ ሰክቶ ለተመለከተው ያለው በግልጽ ይገነዘበዋል:-
፩) ከንግድ ስራ ጋር የተያያዘ ስጋት (Business Risk)
ይህ ከጠቅላላው የሀገር ኢኮኖሚ ውጣውረድ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ስጋት ሲሆን ይህም በግልጽ የሚታይ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ትግበራ ጋር ምናልባት መፍትሄ ሊያገኝ ከቻለ የሚታይ ይሆናል።
፪) ከገንዘብ አቅርቦት ጋር የተያያዘ ስጋት ( Financial Risk)
ለሪል እስቴት ኢንቨስትመንት የሚውለው ሙዓለ ነዋይ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ የተነሳ በአልሚዎች ብቸኛ አቅም ሊሸፈን የሚችል አይደለም። አስፈላጊ የሆነውን የገንዘብ አቅርቦት ከባንክ ፣ ከደንበኞች ከሚሰበሰብ፣ አብሮ በማልማት፣ አክሲዮን በመሸጥ.. ወጪውን ለመሸፈን የሚደረጉ ጥረቶች ስኬት ሲርቃቸው እየተመለከትን ነውና ዘርፋ በዚህ ረገድም አደጋ ላይ ነው።
፫) ካለመሸጥ( ገዥ ከማጣት) ጋር የተያያዘ ( Liquidity Risk)
የሪል እስቴት ንብረት በቶሎ ተሸጦ ገንዘብ የሚገኝበት ( Liquid ) እንዳልሆነ ይታወቃል። ነገር ግን ልፕገበያ ወጥቶ በሶስት እስከ ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ መሸጥ ካልቻለ ችግር አለ ማለት ነው። በአሁን ወቅት ስለአንድ ቤት ሳይሆን በዘርፉ ላይ ንብረት ለገበያ አውጥቶ ገዢ ማግኘት እየከበደ ከአንድ አመት በላይ ገዢ ያጡ ባርካታ አልሚዎች እንዳሉ እንመለከታለን ይህ ዘርፉ የ liquidity risk ውስጥ እንደገባ የሚያሳይ ነው።
፬) የግሽበት አደጋ ( Inflation Risk) እንደማንኛውም ቁስ የሪል እስቴት ግብዓቶችም ከፍተኛ ለሆነ የዋጋ ግሽበት እየተጋለጡ በመሆኑ ግንባታቸው ከተገመተው በላይ ወጪ በመጠየቅ የሚጠበቀውን ትርፍ ላያስገኝ ለኪሳራም ሊዳርግ ይችላል።
፭) የድርጅት አስተዳደር ችግር ( Management Risk)
ብዙዌች የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ውስጥ የሚገቡት ከተለያየ ስኬታማ ቢዝነስ ውስጥ ተነስተው በመሆኑ ቀድመው የሚሰሩበትን የአስተዳደር ዘይቤ በሪል እስቴት ውስጥ ለማስቀጠል ሲሞክሩ ይታያል። ይህም ብዙዎችን ለኪሳራ እየዳረገ እንደሚሄድ ይጠበቃል ይታያልልም። አበባና ሰሊጥ መላክና ሪል እስቴት አይገናኙም ኮንስትራክሽንና ሪል እስቴት ቢዝነስም ለየቅል ናቸው ።
፮) ከብድር ወለድ ጋር የተያያዘ ( Interest Rate Risk)
ከአራጣ የማይተናነሰው በብዙ መከራና መላ አልፎ አልፎ የሚገኘው የሪል እስቴት ብድር የወለድ ምጣኔ ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር በተለያዩ ጊዜያት የብድር ወለድ ምጣኔ ላይ የሚደረጉ ጭማሪዎች ያልታሰበ ወጪ በማስከተል ለኪሳራ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው።
፯) ከህግና መመሪያዎች ጋር የተያያዘ( Legistlative Risk)
ዘርፉ የሚመራበት ህግ በቅርቡ መጽደቁ ለዘርፉ አንድ ትልቅ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያለው ነው። ነገር ግን ዘርፉ ብዙ ዘርፎችን የሚያካትት በመሆኑ በሌሎች ዘርፎች ውስጥ የሚወጡ ህጎችና መመሪያዎችም ተጽዕኖ ያሳድሩበታል። ለምሳሌ የሊዝ አዋጅ ፣ የህንጻ አዋጅ እና የንብረት ማስመለስ አዋጅ በከፍተኛ ሁኔታ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።
፰)ተፈጥሯዊ ክስተቶች (Natural Disasters)
በሪል እስቴት ግብይት ውስጥ የሚወጣው ወጪ ከፍ ማለቱ ገዢዎች በየጊዜው የሚከሰቱ ያልተጠበቁ ተፈጥራዊ አደጋዎችን ከግብይት ውሳኔ እንዲርቁ ወይም እንዲዘገዩ ሊያደርጓቸው ይችላሉ። ለምሳሌ ሰሞኑን የተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች አፓርትመንት (ኮንዶሞኒየም) ቤቶች ግብይት ላይ ተጽዕኖ መፍጠሩ እየተነገረ ነው።
ከላይ የተዘረዘሩትን የኢንቨስትመንት ስጋቶች በሙሉ በሚገባ የሚያሰጉት ለሰውልጅ መሰረታዊ ፍላጎቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን መኖሪያ ቤት እንዲያቀርብ የሚጠበቅበት የሀገራችን የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ዘርፍ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ችግሮቹ አንድ በአንድ ሊቀረፉና የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ሊደረግ ይገባል። የገበያ ስጋት ( Market Risk ) ያልተካተተው ሌሎች ችግሮች ሲፈቱ አብሮ የሚፈታ በመሆኑ ነው።
ችግሮቹን ከመፍታት አንጻር መንግስት ፣ ተጠባቂው ካፒታል ማርኬትና አልሚዎች የየራሳቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል:-
1) መንግስት በተራ ቁ. ፩፣፬ እና ፯ የሚገኙትን ትኩረት ሰጥቶ ቢፈታ
2) ካፒታል ማርኬት በተራ ቁ. ፪ እና ፮ ያሉትን መላ ቢፈጥር
3) አልሚዎች በበኩላቸው በተራ ቁ. ፫ ፣ ፭ እና ፰ ያሉትን ትኩረት ሰጥተው ቢፈቱና የመንግስትና የካፒታል ማርኬት የሚሰጡትን መፍትሄና የሚፈጠሩ እድሎች በአግባቡ ቢጠቀሙ መልካም ይሆናል ።
Via ደሳለኝ ከበደ። የ መዋቅር መሀንዲስ፣ ገንቢ፣ ሪል ስቴት አማካሪ እና አሰልጣኝ
@etconp