“በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት አሳስቦናል፣ #በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያሉ የእርስ በርስ ግጭቶች እልባት እንዲያገኙ የፖለቲካ ውይይት ወሳኝነት አለው” - አንቶኒ ብሊንከን‼️
#የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በስልክ ማውራታቸው ተገለጸ።
“በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያሉ የእርስ በርስ ግጭቶች እልባት እንዲያገኙ የፖለቲካ ውይይት ወሳኝነት አለው” ሲሉ አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር አብይ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ወቅት መናገራቸው የመስሪያ ቤታቸው መግለጫ አመላክቷል።
አሜሪካ “#በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት ያሳስባታል” ሲሉ መናገራቸውን መግለጫው አካቷል።
አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር አብይ ጋር በስልክ ያወሩት #በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ዙሪያ እንደነበር ጸ/ቤታቸው ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
አንቶኒ ብሊንከን “ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲደረግ ለምታደርገው ጥረት ሀገራቸው እገዛ ለማድረግ ዝግጁ ናት” ሲሉ መናገራቸውን መግለጫው ጠቁሟል።
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ጠ/ሚኒሰትር አብይ በአፍሪካ ቀንድ እየተካረረ በመጣው ውጥረት ዙሪያም መምከራቸውንም የመስሪያ ቤታቸው ቃል አቀባይ ቢሮ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
⬇️⬇️ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
👉 @Akiyas21bot
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA⬇️⬇️