ሰበር ዜና ET🇪🇹


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский


መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot

የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Статистика
Фильтр публикаций


የሱማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ የኢትዮጵያ ኃይሎች ጌዶ ግዛት ውስጥ ዶሎ በተባለች የድንበር ከተማ በሦስት የሱማሊያ ጸጥታ ኃይሎች ጣቢያዎች ላይ ትናንት ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሷል። ጥቃቱ "የታቀደ" እና "ኾን ተብሎ" የተፈጸመ ነበር ያለው ሚንስቴሩ፣ በጥቃቱ ሲቪል የአካባቢው ነዋሪዎችን ጨምሮ ቁጥራቸውን ያልገለጣቸው ሰዎች እንደተገደሉ ጠቅሷል። ጥቃቱ ኹለቱ አገሮች አንካራ ላይ የተፈራረሙትን የባሕር በር ስምምነት የሚጥስ እንደኾነ ሚንስቴሩ የጠቀሰ ሲኾን፣ ሱማሊያ ጥቃቱን በዝምታ እንደማትመለከተውም ገልጧል። ሱማሊያ ይህን ክስ ያሠማችው፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደኤታዋ ዓሊ ኦማር ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር በኹለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ለመነጋገር አዲስ አበባ ከገቡ ከሰዓታት በኋላ ነው።
======================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ቡግና‼️
ቡግና ወረዳ ከ79 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ይሻሉ‼️
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተዉ ድርቅና የምግብ እጥረት ምክንያት 79 ,418 ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተባለ። በወረዳው ከ 10 ሺህ በላይ እናቶችና ሕፃናት በከፋተኛ የምግብ እጥረት ምክንያት ጉዳት እንደደረሰባቸዉ የወረዳዉ ጤና ጽሕፈት ቤት አሳውቋል።
======================
@ET_SEBER_ZENA


እገታ‼️
ዛሬ ታህሳስ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ረፋድ 3:00 ሰዓት አካባቢ መነሻውን አዲስ አበባ በማድረግ ወደ ደማርቆስ መንገደኞችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ "የኛ ባስ" ገብረ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ አስቁመው ተሳፋሪዎችን ይዘው መሰወራቸው ተሰምቷል።

ከተሳፋሪዎች መካከል 3 ሴቶች ወድያውኑ ከእገታው ያመለጡ ሲሆን ለማምለጥ የሞከረ አንድ ወጣት ተገድሏል ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ እገታው ሲፈፀም  በነበረ መደናገጥ በተፈጠረ ግጭት 3 የጭነት መኪናዎች  ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ቀሪዎቹ ተሳፍሪዎች ታግተው የተወሰዱ መሆናቸውን ከእገታው ያመለጡ ተሳፋሪዎች  ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የታጋቾቹ ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም 45 አካባቢ ሳይሆን እንዳልቀረ ምንጮቼ ገልፀዋል። ሌላ አንድ የተሳቢ ሾፌርም አብሮ ተወስዷል ብለዋል።
======================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ለባለይዞታዎች‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ለ8ኛ ጊዜ የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ እና ምዝገባ ስራ ሊያከናውን ነው ‼️
👉የይዞታ ማረጋገጫ ከታህሳስ 10-ሚያዚያ 15 ይከናወናል ብሏል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ግፋ ወሰን ደሲሳ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ኤጀንሲው ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ከጀመረበት 2007 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2016  በጀት ዓመት ድረስ 7 ጊዜ የይዞታ ማረጋገጥ እወጃ በማካሄድ በ 337 ቀጠናዎች ላይ የማረጋገጥ ስራ ማከናወኑን ተናግረዋል  ፡፡

በዚህ መሰረት በያዝነዉ በጀት  አመት  ለመጨረሻ ጊዜ  ለስምንተኛ ዙር  ቀሪ  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉትን ያልተረጋገጡ  136 ቀጠናዎች   የሚገኙ ቁራሽ መሬቶችን   አረጋግጦ ለመመዝገብ  ዝግጅቱን  በማጠናቀቅ  ዛሬ ታህሳስ 10/4/2017 ዓ.ም እወጃ ማካሄዱን ገልፀዋል ፡፡

የይዞታ ማረጋገጡ ስራ በተመረጡ ስድስት  ክፍለ ከተሞች ማለትም የካ ክፍለ ከተማ( በወረዳ  ወረዳ1፤2፤ 3፤9፤10፤11፤12  በ 25 ቀጠናዎች   በለሚ ኩራ በወረዳ 2፣3፤4፤5፤6፤9፤10፣ 13 እና 14 በ 44 ቀጠናዎች፤ አቃቂ ቃሊቲ  ክፍለ ከተማ  ወረዳ 1፣2፣3፣4፤6፣ 9፣13   በ 19 ቀጠናዎች ንፋስ ስልክ ላፍቶ በወረዳ 6 ፣7፣8፤9፤10፣11፣14 የሚገኙ  በ 22 ቀጠናዎች  ቦሌ በ ወረዳ 11፡12፤13  በ 15 ቀጠናዎች   ኮልፌ ቀራኒዮ  በወረዳ 3፤11   በ 11 ቀጠናዎች አጠቃላይ  በ 136 ቀጠናዎች (በ 467 ሰፈሮች)  ያልተረጋገጡ ይዞታዎችን የማረጋገጡ ስራ  በስልታዊ ዘዴ / በመደዳ /  የማረጋገጥ ስራ የሚከናወን  ሲሆን ስራውም ከ ታህሳስ 10/04/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ወራት ውስጥ እስከ  ሚያዝያ 15 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ሙሉ ወጪውም በመንግስት እንደሚሸፈን ተናግረዋል፡፡
ኤጀንሲው አረጋግጦ ላልመዘገበው ይዞታ ምንም ዓይነት ህጋዊ ዋስትናና ከለላ የማይሰጥ መሆኑን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ባለይዞታዎች ከታህሳስ 20/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስፈላጊውን መረጃ ይዘው የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንድታቀርቡ በድጋሜ አሳስበዋል፡፡

ኤጀንሲው የይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ከጀመረበት 2007 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ 7 ጊዜ የይዞታ ማረጋገጥ እወጃ በማካሄድ በ337 ቀጠናዎች ላይ የማረጋገጥ ሥራ ተካሂዷል፡፡ በዚህም በቁራሽ መሬት 219 ሺ 722፣ በጋራ መኖሪያ ቤት 173 ሺ 136 በመብት 400 ሺ 84 ይዞታዎች ላይ የይዞታ ማረጋገጥ ሥራ በመስራት የአዲስ አበባን ከጠቅላላው የቆዳ ስፋት 54% መሸፈኑ ይታወቃል፡፡
======================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


Репост из: ሰበር ዜና ET🇪🇹
በቀን አንዴ ብቻ በመግባት እና ሸር በማድረግ ነዉ አሰራሩ ቀላል ነዉ


ለ5 ሰዉ ሸር አድርጋችሁ 40 ዶላር በላይ መስራት ትችላላችሁ
👇👇


https://t.me/FinchAirdropBot?start=257399

https://t.me/FinchAirdropBot?start=257399


t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref5078621685
🥳 Hey, want to visit the Zoo together?
🦒 Here, you can buy animals, upgrade enclosures, and take part in an Airdrop!
🎁 Claim your welcome bonus and pick your first animal!


ከ3 ሃኪሞች በስተቀር ሁሉም የ #ካምባ ወረዳ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ሥራ በመልቀቃቸው ነዋሪዎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳረጉ‼️

በ #ደቡብ_ኢትዮጵያ ክልል #ጋሞ ዞን ካምባ ወረዳ የሚገኘው ብቸኛው የካምባ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፤ በክፍያና ጥቅማጥቅም አለመፈጸም እንዲሁም “በወረዳው አመራር ያልተገባ ድርጊት” ምክንያት የሕክምና ባለሙያዎች ከሥራ በመልቀቃቸው በተከሰተ የባለሙያ እጥረት ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጉን ነዋሪዎች ገለጹ።

ሆስፒታሉ በአከባቢው ብቸኛ የሕዝብ መገልገያ የጤና ተቋም በመሆን ለካምባና ለጋርዳ ማርታ ወረዳዎች ግልጋሎት ሲሰጥ ቢቆይም አሁን ላይ 3 ሃኪሞች በቻ በመቅረታቸው የሕክምና አገልግሎት ወደ ማቆም ተቃርቧል ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ሆስፒታሉ ታካሚዎችን ከካምባ ወረዳ በ105 ኮሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው #አርባምንጭ ሆስፒታል በመንግስት አንቡላንስ  7000 ብር በማስከፈል ሪፈር  ያደርጋል ተብሏል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢዩኤል ቡጋ በበኩላቸው ከ2015 ዓ.ም የካቲት ወር ጀምሮ ችግሮች መኖራቸውን ጠቅሰው፤  የድንገተኛ ቀዶጥገና ህክምና የሚሰጥ ባለሙያ ባለመኖሩ ሆስፒታሉ መስጠት የሚገባውን አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን ገልጸዋል።
#አዲስስታንዳርድ #ካምባ
======================
@ET_SEBER_ZENA


ደባርቅ ዩኒቨርስቲ‼️
በአማራ ክልል የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ትናንት  ጀምሮ በካፍቴሪያ የቀረበልን ምግብ ተበላሽቶ ተማሪዎች ተቃውሞ ቢያሰሙም የፀጥታ አካላት ገብተው በርካታ ተማሪዎችን ደብድበዋል፣ ተኩስም ነበር ብለዋል።
አሁን ላይ ወደውጪም መውጣት አይቻልም፣ ትናንት ጀምሮ ምግብ አልበላንም የሚመለከተው አካል መፍትሔ ይስጠን ሲሉ ጥቆማቸውን ለአዩዘሀበሻ አድርሰዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተመሳሳይ የሆነ የምግብ ሜኑ ዝርዝር ማድረጉ ይታወሳል።
======================
@ET_SEBER_ZENA


ኢትዮጵያ ክሪፕቶ ከረንሲን ለመገበያያነት ለመጠቀም የሚያስችል መመሪያ ልታወጣ እንደምትችል የብሔራዊ ባንክ ገዢ ጥቆማ ሰጡ‼️

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክሪፕቶ አሴትን እና የዲጂታል ገንዘብን በኢትዮጵያ መጠቀም የሚያስችል መመሪያ ወደፊት ሊያወጣ እንደሚችል የተቋሙ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ ገለጹ።

ብሔራዊ ባንክ መመሪያውን የሚያወጣው በማዕከላዊ ባንኪንግ፣ በገንዘብ ፖሊሲ እና በገንዘብ አስተዳደር  ያሉ ዓለም አቀፍ “ለውጦችን” እና “እድገቶችን” እያየ መሆኑን አቶ ማሞ ተናግረዋል።

አቶ ማሞ ይህን ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአዋጅ ማሻሻያ ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8፤ 2017 በተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀበት ወቅት ከፓርላማ አባል ለቀረበ ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ ነው።

አዲሱ አዋጅ ካካተታቸው አዳዲስ ድንጋጌዎች መካከል ክሪፕቶ ከረንሲ እና የዲጂታል ገንዘብን መጠቀም የተመለከተው አንዱ ነው።

አዋጁ “አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ብሔራዊ ባንክ ካልፈቀደ በስተቀር፤ ክሪፕቶ ከረንሲ ወይም ሌላ ማንኛውንም ዲጂታል ወይም የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ በመጠቀም ክፍያ መፈጸም አይችልም” ሲል ክልከላ ያስቀምጣል።

አዋጁን በመተላለፍ በእነዚህ መንገዶች ክፍያ የፈጸመ ማንኛውም ሰው፤ ከሶስት ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት እና ከአስር ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ እንደሚቀጣም ተደንግጓል።
#ኢንሳይደር
@ET_SEBER_ZENA


በቀን አንዴ ብቻ በመግባት እና ሸር በማድረግ ነዉ አሰራሩ ቀላል ነዉ


ለ5 ሰዉ ሸር አድርጋችሁ 40 ዶላር በላይ መስራት ትችላላችሁ
👇👇


https://t.me/FinchAirdropBot?start=257399

https://t.me/FinchAirdropBot?start=257399


እስራኤል በህገወጥ በያዘችው የሶርያ ጎላን አካባቢ ዜጎቿን ለማስፈር ውሳኔ አሳለፈች ‼️
የእስራኤል መንግስት በህገወጥ መንገድ በተያዘው የጎላን ኮረብታማ ስፍራዎች ላይ የእስራኤል ሰፋሪዎችን ቁጥር ለመጨመር የያዘውን እቅድ አጽድቋል። የሶሪያ የረዥም ጊዜ መሪ በሽር አል አሳድ ከስልጣን መውረድ በኋላ እና እስራኤል ተጨማሪ የሶሪያ ግዛት ከተቆጣጠረች ከቀናት በኋላ ይህንን ውሳኔ አፅድቃለች። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፅህፈት ቤት መንግስት በተያዘው ግዛት ውስጥ ያለውን የእስራኤል ህዝብ ቁጥር በእጥፍ ለማሳደግ እና የሚፈለገውን "የሕዝብ ልማት" ለማምጣት ውሳኔውን በአንድ ድምጽ አጽድቋል ብሏል።

አዲሱ እቅድ እ.ኤ.አ. ከ1967 ጀምሮ እስራኤል ለያዘችው የጎላን ክፍል ብቻ ተግባራዊ የሚሆን ነው። በ1981 የእስራኤል ክኔሴት የእስራኤልን ህግ በግዛቱ ላይ ለመጫን ተንቀሳቅሷል። ዕቅዱ ተግባራዊ የሆነው ከሳምንት በፊት በአል አሳድ መውደቅ ምክንያት እስራኤል ከያዘችው የሶሪያ ክፍል ጋር አይገናኝም ተብሏል። ከ1973 ጦርነት በኋላ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከወታደራዊ ኃይል ነፃ የሆነውን የሄርሞን ተራራን የሚያካትት ሲሆን ይህ ግዛት የሶሪያ ዋና ከተማን ደማስቆን ለመመልከት የሚያስችል ነው።

ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫ የሰፋሪዎችን ቁጥር ለመጨመር ከ40 ሚሊዮን በላይ ሼክል ወይም 11ሚሊዮን ዶላር በላይ ፈሰስ የሚደረግበትን እቅድ አድንቀዋል።
Reuters
=====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ባባ ቫንጋ በቀጣዩ የፈረንጆች አመት 2025 ምን ይከሰታል ብለው ተነበዩ?
ታዋቂዋ የቡልጋሪያ ጠንቋይ "ሶሪያ በአሸናፊዎች እጅ ትገባለች፤ በምስራቁ ምዕራባውያንን የሚያጠፋ ሶስተኛው የአለም ጦርነት ይጀመራል" ብለዋል‼️
ከ28 አመት በፊት ህይወታቸው ያለፈው ባባ ቫንጋ እስከ 2030 ድረስ አለማችን የምታስተናግዳቸውን አበይት ክስተቶች ተንብየዋል
ቫንገሊያ ፓንዴቫ ጉሽቴሮቫ ወይም በተለምዶ ባባ ቫንጋ እየተባሉ የሚጠሩት ቡልጋሪያዊት ጠንቋይ አዲስ አመት ሲቃረብ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ይስባሉ።
አይነስውሯ ባባ ቫንጋ በ85 አመታቸው በፈረንጆቹ 1996 ህይወታቸው ቢያልፍም እስከ 2030 አለማችን የምታስተናግዳቸውን አበይት ክስተት ተንብየዋልና አሁንም ድረስ ይነሳሉ።
በ12 አመታቸው የአይን ብርሃናቸው ካጡ በኋላ የወደፊቱን የመተንበይ ብቃት እንዳዳበሩ የሚናገሩት ባባ ቫንጋ የመስከረም 11ዱን የኒውዮርክ መንትያ ህንጻዎች ጥቃት፤ የሶቪየት ህብረት መፈራረስና ካንሰር የተባለ በሽታ ቀጣይ ስጋትነትን አስቀድመው ተንብየዋል።
ከ16 ቀናት በኋላ በሚገባው 2025ም በአለማችን የሚከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችን ከህልፈታቸው በፊት ተንብየዋል ብሏል ዴይሊ ታር በዘገባው።
የአውሮፓ ጥፋት
ባባ ቫንጋ የፈረንጆቹ 2025 ምዕራባውያንን ክፉኛ የሚጎዳ አስከፊ ጦርነት የሚከሰትበት መሆኑን ተንብየዋል። በሶሪያ ጉዳይ አስቀድመው ተናገሩት የተባለውም የቡልጋሪያዊቷን እንስት የመተንበይ ችሎታ በጉልህ አሳይቷል። "ሶሪያ በመጨረሻ በአሸናፊዎች እጅ ትወድቃለች፤ አሸናፊው ግን አንድ አይሆንም" ያሉት ባባ ቫንጋ፥ "በምስራቁ ምዕራባውያንን የሚያጠፋ ሶስተኛ የአለም ጦርነት ይጀመራል" ሲሉ ተንብየዋል።
ከዮፎ ጋር ግንኙነት
ባባ ቫንጋ "በ2025 የሰው ልጆች ምንነታቸው ከማይታወቁ በራሪዎች (ዮፎ) ጋር ግንኙነት ይጀምራሉ፤ ይህም ምናልባትም አለማቀፍ ቀውስ ያስከትላል" ይላሉ።
የአሜሪካዋ ኒው ጀርሲ ከአንድ ወር በላይ ዩፎ ይሁኑ ድሮኖች እስካሁን በውል ያልተለዩ በረሪ አካላት በሰማይ እያንዣበቡባት ነው።
ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ካሸነፉ የአሜሪካ መንግስት በዩፎዎች ዙሪያ ያለውን ዝርዝር መረጃ ይፋ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። የትራምፕ መመረጥም የባባ ቫንጋ ትንበያ እውን ሊሆን እንደሚችል አመላካች ነው ተብሏል።
#Alain #Vanga
=====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA




ይህ ለ5 ሰዉ ሸር አድርጋችሁ 40 ዶላር በላይ መስራት ትችላላችሁ
👇👇


https://t.me/FinchAirdropBot?start=257399

https://t.me/FinchAirdropBot?start=257399


በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ተክለሃይማኖት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ‘’አካባቢው ለልማት እንደሚፈለግ ተነግሮን፣ ምትክ ቤት እንዲሰጠን ተስማምተን፣ እየጠበቅን እያለን ዛሬ ማለዳ ቤታችንን መፍረስ ጀምሯል’’ አሉ፡፡

‘’ክፍለ ከተማው ምትክ ቦታ ሳይሰጣችሁ እንዳትወጡ ቢለንም ወረዳው በተኛንበት መጥቶ ቤታችን አፈረሰብን’’ ሲሉ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የተክለሓይማኖት አካባቢ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን  ነገረውናል፡፡

ነዋሪዎቹ ቦታው ለልማት እንደሚፈለግ ተነግሮን እኛም ተስማምተን፣ ምትክ ቦታ በመጠበቅ ላይ እያለን ወረዳው ዛሬ ማለዳ ቤታችንን በድንገት አፈረሰብን ሲሉ ቅሬታቸውን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አቅርበዋል፡፡

ክፍለ ከተማው ‘’አዎ ምትክ ቤት ሳይሰጣቸው ቤታቸው እንደማይፈርስ ቃል ገብቻለሁ፣ ቤቶቹ እየፈረሱ ስለመሆኑም የማውቀው ነገር የለም’’ ብሏል፡፡

ወረዳው በበኩሉ ‘’ለነዋሪዎቹ ምት ቦታ እንደተሰጣቸው እና እንዳፈርስ ከክፍለ ከተማው ትዕዛዝ ስለሰጠኝ ነው ያፈረስኩት ብሏል፡፡

ምትክ ቤት መሰጠቱን ማረጋገጥ የኔ ሃላፊነት አይደለም  ሲልም፡፡

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በበኩሉ ቤቶቹ እንዲርሱ እንዳላዘዘና ስለመፍረሳቸውም መረጃው እንደሌለው ተናግሯል፡፡
#ሸገር
=====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ግብፅ
ግብፅ በሶማሊያ እንደተካደችና ሞቃዲሾ ካይሮን ከጀርባ እንደወጋቻት  በመቁጠር መበሳጨቷ ተገለፀ
የሶማሊያ የስለላ ተቋም መሪ የነበሩት አብዲሳላን ጉሌድ  የግብፅ መንግስት ሃሰን ሼክ በአንካራ ከኢትዮጵያ ጋር መፈራረማቸው በጣም እንዳሳዘናት ባደረጉት ቃለ መጠይቃቸው ይፋ አድርገዋል።

የካይሮ ቤተመንግስት ታማኝ የባለስልጣናት ምንጮችን ዋቢ ያደረጉት ሰውየው፣ የግብፅ አገዛዝ ይህን የሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ድርጊት ከጀርባ እንደተወጋ በመቁጠር ክህደት እንደተፈፀመባት አድርጋ እንደምትመለከተው እወቁት ብለዋል።
=====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


በተከለከለ አየር ክልል በረራ አድርገዋል የተባሉ የኢትዮጵያንና የ ኢትሃድ አየር መንገዶችን በአሜሪካ መቀጣታቸው ተሰምቷል።

የአሜሪካ የትራንስፖርት ክፍል የኢትዮጵያ አየር መንገድን 425,000 ዶላር እና የኢትሃድ አየር መንገድን 400,000 ዶላር  መቅታቱ ተገለጸ። 

አየር መንገዶቹ የተቀጡት ያለፍቃድ በተቀከለከለ አየር ክልል በረራ ማከናወናቸው በደንበኞች ጥበቃ አቪየሽን ቢሮ ምርመራ መደረጉን ተከትሎ ነው ተብሏል።

ምርመራው እንዳመለከተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጎርጎሮሳውያኑ 2020 እስከ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ እና በጂቡቲ መካከል የተባበሩት አየር መንገድ መለያ ኮዶችን የያዙ በረራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

አየር መንገዱ ከሀምሌ 2022 እስከ ሚያዚያ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ ጄትብሉ አየር መንገድን (B6) ኮድን በመጠቀም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና አሜሪካ መካከል በረራዎችን አካሄዷል ሲል የአቪየሽን ድር ገጾች ዘግበዋል።

የአሜሪካ የትራንስፖርት ክፍል እነዚህ በረራዎች በአሜሪካ ደንቦች መሠረት ተገቢ ፈቃድ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጸ ሲሆን ምርመራው አየር መንገዶቹ ቀደም ብሎ ማሳወቂያ ቢሰጣቸውም በራራዎቹ መቀጠላቸውን ከአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ተመልክተናል።

ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ኢሳያስ አፈወርቂ‼️
ከብዙ ጊዜ በኋላ ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ አሰብ አቅንተው ለካቢኒያቸው አመራር ሰጡ ‼️
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ  ከረጅም ጊዜ ቦኃላ አሰብ ተገኝቶ የደቡባዊ ቀይ ባህር ዞን አመራሮችን ሰብስቦ ጥብቅ መመርያ ሰጥቷል።
ኢሳይያስ አፈወርቂ ይሄን ያደረጉት በትናትናው ዕለት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት እና በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ አፍሪካ ጉዳይ ረዳት ፀሀፊ የሆኑት ቲቦር ናጊ "በሶሪያው መሪ በሽር አላሳድ ላይ የተደገመው በኤርትራ መንግሥት ላይ ይደገማል" የሚል ፅሁፍ በቲዊተር ገፃቸው ካስተላለፉ በኋላ ነው።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


አነጋጋሪው ፅሁፍ
የሶርያው በኤርትራ ይደገማል ሲሉ ቲቦር ናጊ ተናገረ
ይህን ያሉት ከዚህ ቀደም የአሜሪካ አምባሳደር በመሆን በኢትዮጲያና በጊኒ ያገለገሉት ዲፕሎማቱ ቲቦር ናጊ ሲሆኑ አነጋጋሪውን አስተያየት በኤክስ ገፃቸው ላይ አጋርተዋል።

"የባሽር አል አሳድን ውድቀት ሶርያውያን በደስታ እንዳከበሩት ሁሉ አምባገነኑ ኢሳያስ አፍወርቂ ሲወድቅም ኤርትራውያን በተመሳሳይ መንገድ ደስታቸውን ይገልፃሉ ሲሉ ዲፕሎማቱ በኤክስ ገፃቸው ተመልክቷል።

አክለውም "ከጥቂት ቀናት በፊት የባሽር አልአሳድ ደጋፊዎች የነበሩት አሁን ስርዓቱን ሲቃወሙት እንደነበር የተናገሩ ሲሆ፤ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው ይህ በኤርትራ ላይ ይደገማል ሲሉ የአሜሪካ መንግስትን ለበርካታ ዓመታት ዲፕሎማት ሆነው ያገለገሉት ቲቦር ናጊ ተናግረዋል።
===================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


t.me/seed_coin_bot/app?startapp=6359053212
SEED App - No.1 Play2Earn Telegram App
Join now with me and ready to receive SEED airdrop!

🥳 Get Welcome Gift Pack including in-game items and SEED
💲Earn 20% cashback from frens

Показано 20 последних публикаций.