በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ተክለሃይማኖት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ‘’አካባቢው ለልማት እንደሚፈለግ ተነግሮን፣ ምትክ ቤት እንዲሰጠን ተስማምተን፣ እየጠበቅን እያለን ዛሬ ማለዳ ቤታችንን መፍረስ ጀምሯል’’ አሉ፡፡
‘’ክፍለ ከተማው ምትክ ቦታ ሳይሰጣችሁ እንዳትወጡ ቢለንም ወረዳው በተኛንበት መጥቶ ቤታችን አፈረሰብን’’ ሲሉ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የተክለሓይማኖት አካባቢ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ነገረውናል፡፡
ነዋሪዎቹ ቦታው ለልማት እንደሚፈለግ ተነግሮን እኛም ተስማምተን፣ ምትክ ቦታ በመጠበቅ ላይ እያለን ወረዳው ዛሬ ማለዳ ቤታችንን በድንገት አፈረሰብን ሲሉ ቅሬታቸውን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አቅርበዋል፡፡
ክፍለ ከተማው ‘’አዎ ምትክ ቤት ሳይሰጣቸው ቤታቸው እንደማይፈርስ ቃል ገብቻለሁ፣ ቤቶቹ እየፈረሱ ስለመሆኑም የማውቀው ነገር የለም’’ ብሏል፡፡
ወረዳው በበኩሉ ‘’ለነዋሪዎቹ ምት ቦታ እንደተሰጣቸው እና እንዳፈርስ ከክፍለ ከተማው ትዕዛዝ ስለሰጠኝ ነው ያፈረስኩት ብሏል፡፡
ምትክ ቤት መሰጠቱን ማረጋገጥ የኔ ሃላፊነት አይደለም ሲልም፡፡
አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በበኩሉ ቤቶቹ እንዲርሱ እንዳላዘዘና ስለመፍረሳቸውም መረጃው እንደሌለው ተናግሯል፡፡
#ሸገር
=====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
👉 @Akiyas21bot
@ET_SEBER_ZENA