እስራኤል በህገወጥ በያዘችው የሶርያ ጎላን አካባቢ ዜጎቿን ለማስፈር ውሳኔ አሳለፈች ‼️
የእስራኤል መንግስት በህገወጥ መንገድ በተያዘው የጎላን ኮረብታማ ስፍራዎች ላይ የእስራኤል ሰፋሪዎችን ቁጥር ለመጨመር የያዘውን እቅድ አጽድቋል። የሶሪያ የረዥም ጊዜ መሪ በሽር አል አሳድ ከስልጣን መውረድ በኋላ እና እስራኤል ተጨማሪ የሶሪያ ግዛት ከተቆጣጠረች ከቀናት በኋላ ይህንን ውሳኔ አፅድቃለች። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፅህፈት ቤት መንግስት በተያዘው ግዛት ውስጥ ያለውን የእስራኤል ህዝብ ቁጥር በእጥፍ ለማሳደግ እና የሚፈለገውን "የሕዝብ ልማት" ለማምጣት ውሳኔውን በአንድ ድምጽ አጽድቋል ብሏል።
አዲሱ እቅድ እ.ኤ.አ. ከ1967 ጀምሮ እስራኤል ለያዘችው የጎላን ክፍል ብቻ ተግባራዊ የሚሆን ነው። በ1981 የእስራኤል ክኔሴት የእስራኤልን ህግ በግዛቱ ላይ ለመጫን ተንቀሳቅሷል። ዕቅዱ ተግባራዊ የሆነው ከሳምንት በፊት በአል አሳድ መውደቅ ምክንያት እስራኤል ከያዘችው የሶሪያ ክፍል ጋር አይገናኝም ተብሏል። ከ1973 ጦርነት በኋላ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከወታደራዊ ኃይል ነፃ የሆነውን የሄርሞን ተራራን የሚያካትት ሲሆን ይህ ግዛት የሶሪያ ዋና ከተማን ደማስቆን ለመመልከት የሚያስችል ነው።
ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫ የሰፋሪዎችን ቁጥር ለመጨመር ከ40 ሚሊዮን በላይ ሼክል ወይም 11ሚሊዮን ዶላር በላይ ፈሰስ የሚደረግበትን እቅድ አድንቀዋል።
Reuters
=====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
👉 @Akiyas21bot
@ET_SEBER_ZENA