ከ3 ሃኪሞች በስተቀር ሁሉም የ #ካምባ ወረዳ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ሥራ በመልቀቃቸው ነዋሪዎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳረጉ‼️
በ #ደቡብ_ኢትዮጵያ ክልል #ጋሞ ዞን ካምባ ወረዳ የሚገኘው ብቸኛው የካምባ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፤ በክፍያና ጥቅማጥቅም አለመፈጸም እንዲሁም “በወረዳው አመራር ያልተገባ ድርጊት” ምክንያት የሕክምና ባለሙያዎች ከሥራ በመልቀቃቸው በተከሰተ የባለሙያ እጥረት ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጉን ነዋሪዎች ገለጹ።
ሆስፒታሉ በአከባቢው ብቸኛ የሕዝብ መገልገያ የጤና ተቋም በመሆን ለካምባና ለጋርዳ ማርታ ወረዳዎች ግልጋሎት ሲሰጥ ቢቆይም አሁን ላይ 3 ሃኪሞች በቻ በመቅረታቸው የሕክምና አገልግሎት ወደ ማቆም ተቃርቧል ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ሆስፒታሉ ታካሚዎችን ከካምባ ወረዳ በ105 ኮሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው #አርባምንጭ ሆስፒታል በመንግስት አንቡላንስ 7000 ብር በማስከፈል ሪፈር ያደርጋል ተብሏል።
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢዩኤል ቡጋ በበኩላቸው ከ2015 ዓ.ም የካቲት ወር ጀምሮ ችግሮች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ የድንገተኛ ቀዶጥገና ህክምና የሚሰጥ ባለሙያ ባለመኖሩ ሆስፒታሉ መስጠት የሚገባውን አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን ገልጸዋል።
#አዲስስታንዳርድ #ካምባ
======================
@ET_SEBER_ZENA