ለኔ አስተናጋጅ ብቻ ነበረች
የምትሰራበት ሬስቶራንት እሄዳለሁ ። ቢራ አዛለሁ ከቢራው ጋ ቆሎ ይመጣል ። ቆሎ እወዳለሁ ቢራውንም የምሰራውም ስራ ትቼ በትንሽዬ ሳህን የመጣልኝን ቆሎ በቶሎ ከራሴ ጋ እየተሻማው እበላለሁ ሌላ ሰው ካለ የሚያወራኝን ጨዋታ እየሰማው ቶሎ ቶሎ እበላለሁ ።
መፅሃፍ ፣ጋዜጣ አነባለሁ ። ስልክ እነካካለሁ ፣እቆዝማለሁ ።
ትላንት ከሰዓት ሄጄ እንደተቀመጥኩ ቢራ አዘዝኩ ። እንደወትሮ ከቢራ ጋ ቆሎ አልመጣም ። አስተናጋጇን" የታለ ቆሎ" አልኳት በጣም በፈገግታ "አልቋል ተብሎ ነው" አለቺኝ ።
ለመጀመርያ ግዜ አስተዋልኳት
የፊቷ ቀለም ደማቅ ጠይም ነው ። የደስ ደሳም ናት ። ስትስቅ ፊቷ ብርት ይላል ። አይኗ ጎላ ያለ ነው ቅንድቧ ብዙ ነው ።
ታምራለች ደሞ ።
"የየት አገር ልጅ ነሽ " አልኮት
"አሪሲ -ቀርሳ " አለቺኝ ። ትህትናዋ አይኗ ላይ ያለው አክብሮት የሚሰማ አይነት ነው ።
"ስራ ጥሩ ነው ወይ?" አልኳት ።
"እውይ ከብዶኛል ።
ስራ ከዛ እቤት ከዛ ስራ ጎደኛ የለኝ እዚ ..እማውቀው የለ ። ባይተዋርነት ተጫወተብኝ አለቺኝ"
"ስምሽ ማነው ?
"አለም ፀሃይ"
"ጓደኞቼ አለም ነበር የሚሉኝ አገሬ " አለቺኝ
ታስታውቃለች ሰው እርቧታል ። ስሟን እየጠራ በረፍት ሰዓት አብሯት ዎክ የሚሄድ ድራፍት የሚጠጣ ፣ ጉባዬ ወይ ሲኒማ የሚወስዳት ፍለጋ ላይ ነች መሰለኝ
እሰይ ደረስኩላት
"አለም ከዚ በኋላ እኔ አለሁልሽ እሺ"
"እሺ"
©
@Enmare1988