በሩሲያ 22 ሰዎችን ያሳፈረች ሄሊኮፕተር ጠፋች‼️
የካምቻትካ ገዥ ቭላድሚር ሶሎዶቭ በቴሌግራም ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ተንቀሳቃሽ ምስል፥ 22 ሰዎች ማለትም 19 ተሳፋሪዎች እና ሦስት የበረራ ሠራተኞችን የያዘችው ኤምአይ-8 ሄሊኮፕተር ጋር የነበረው ግንኙነት እንደተቋረጠ አስታውቀዋል፡፡
የነፍስ አድን ቡድኖች ሄሊኮፕተሯ ልትበር በነበረችበት የወንዝ ሸለቆ ላይ ትኩረት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን፥ ምሽቱን ፍለጋ ላይ መሆናቸውን የሩሲያ ባለስልጣናት ገልፀዋል።
ኤምአይ-8 በፈረንጆቹ 1960ዎቹ ንድፈ ሃሳብ የተሰራላት ባሁለት ሞተር ሄሊኮፕተር ስትሆን፥ አደጋው በተደጋጋሚ በሚከሰትባት ሩሲያ እንዲሁም በአጎራባች ሀገራትና በሌሎች በርካታ ሀገራት በስፋት ጥቅም ላይ እንደምትውል ዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
ሄሊኮፕተሯ በመልክዓ ምድሮች እና እሳተ ገሞራዎች ሌትና ቀን በሚንተከተክበት ቫችካጄክ አቅራቢያ ተሳፋሪዎችን ይዛ ያቀናችውም ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ኒኮላይቭካ መንደር ነው ተብሏል፡፡
ሄሊኮፕተሯ ከተነሳች በኋላ ወዲያውኑ ከራዳር የጠፋ ቢሆንም እና የሄሊኮፕተሯ ሰራተኞች ምን ዓይነት ችግር እንደገጠማቸው አለማሳወቃቸውም ነው የተገለጸው።
በአካባቢው ያለው የአየር ሁኔታ አገልግሎት እንዳለው፥ የአውሮፕላን ማረፊያ አካባቢው ለእይታ አመቺ አይደለም፡፡
@Esat_tv1