የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ892 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ‼️
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ የክልሉ መንግስት የይቅርታ አዋጁን መስፈርት ላሟሉ 892 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡
ርዕሰ መስትዳድሩ እንደገለጹት፤ ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ-ምግባር ያሳዩ እና በሕግ በተደነገገው የይቅርታ መስፈርትን ማሟላታቸው በክልሉ የይቅርታ ቦርድ ተጣርቶ የቀረቡ ናቸው።
የህግ ታራሚዎቹ በመደበኛ የይቅርታ ሕግ እና ሌሎች ተጨማሪ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተብለዉ በልዩ ሁኔታ የቀረቡ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዚሁ መሰረት የይቅርታው ተጠቃሚዎች ይቅርታ በማያስከለክሉ ወንጀሎች ተሳትፈው በማረሚያ ቤት የቆዩ፤ በጤና ችግር፤ በዕድሜ መግፋትና ከሕጻናት ጋር አብረዉ የታሰሩ፣ ከተጎጂ ወገኖች ጋር ታርቀው የእርቅ ሰነድ ማቅረባቸው በየደረጃው በሚገኝ የፀጥታ መዋቅር በቂ ማረጋገጫ የተሰጣቸዉን ታራሚዎች እንዲሁም ከተፈረደባቸው ሲሶ (1/3) እና ከግማሽ (1/2) በላይ የፍርድ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ይቅርታው ከተደረገላቸው 892 የህግ ታራሚዎች መካከል 879 ከእስር የሚፈቱ ሲሆን ቀሪ 13 ታራሚዎች የእስራት ጊዜያቸው የተቀነሰላቸው መሆኑን ርዕሰ መስትዳድሩ ጨምረው ገልጸዋል።
የይቅርታ ተጠቃሚ ከሆኑት የህግ ታራሚዎች መካከል 831 ወንዶች ሲሆኑ 48 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውንም አመልክተዋል።
@Esat_tv1