የ15 ዓመት ታዳጊን ለአራት በመሆን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ‼️
በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ኦፓላሼ ቀበሌ ለአራት በመሆን የ15 ዓመት ታዳጊን አስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ።
ተከሳሾች በቁጥር አራት ሲሆን አስፋቸው አለሙ፣ አሻግሬ አበራ፤ ማቲዎስ ደዋና እና አስማማው አሉላ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው።
ግለሰቦቹ በአመያ ዙሪያ ወረዳ በግምት 8:00 አካባቢ ጫሬ ዶቄ ቀበሌ ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ኦፓላሼ ቀበሌ እየሄደች የምትገኝ የ15 አመት ታዳጊ አስገድደው መድፈራቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞች ጳግሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 7 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥተዋል።
አራተኛ ተከሳሽ ዕድሜው ከ10 እስከ 13 ዓመት በመሆኑ ተከሳሹ መታሰር የማይችልና እንደዚህ ዓይነት ታዳጊ እስረኞችን ተቀብሎ በማረምያ ተቋም በዞኑ ባለመኖሩ ምክንያት ቤተሰቡ ፈርሞ ወስዶት ክትትልና በቁጥጥር እንዲያደርግ በማለት ውሳኔ መሰጠቱን ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
@Esat_tv1