በነቀምቴ ከተማ በተደረገ ዘመቻ በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ‼️
ዘመቻው የኮሩ ሰራዊት ከከተማው ፓሊስ እና ሚሊሺያ ጋር በመቀናጀት የተደረገ ሲሆን ለጠላት መረጃ የሚያቀብሉ የአባ ቶርቤ ቡድን አባላት ጨምሮ 117 የተለያዩ ዓይነት ሽጉጦች ፣ 646 የሽጉጥ ጥይት፣ 30 ክላሽ፣ 34 ኋላቀር መሳሪያ ፣ 563 የክላሽ ጥይት እና 50 የእጅ ቦምብ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ተናግረዋል።
የነቀምቴ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ሻሎም በዳሳ በበኩላቸው በተደረገው ኦፕሬሽን እና በተገኘው ውጤት
ለኮሩ የሰራዊት አባላትና ለፀጥታ ሃይሎች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
የተገኙ ድሎችን በሚመለከት በነቀምቴ ከተማ ውይይት የተደረገ ሲሆን የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ በማስቀጠል የዞኑን ሰላም ማስጠበቅ እንደሚገባ መገለፁን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ የትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
@Esat_tv1