እስራኤል እና ሄዝቦላህ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ባይደን አረጋገጡ‼️
እስራኤል እና የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ለ13 ወራት የዘለቀውን ውጊያ ለመቋጨት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አረጋገጡ።“በሊባኖስ እና በእስራኤል ድንበር ላይ እየተደረገ ያለው ፍልሚያ ማክሰኞ ከሌሊቱ አስር ሰዓት ጀምሮ በአገሬው ሰዓት ይቋጫል” ሲሉ ባይደን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንት ባይደን የተኩስ አቁሙ ግጭትን በዘላቂነት ወደማቆም ስምምነት ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል።ሄዝቦላህ ስምምነቱን ከጣሰ እስራኤል ጥቃት ከመሰንዘር ወደኋላ እንደማትል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ተናግረዋል።በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ በስምምነቱ ላይ የሰጠው መግለጫ የለም።
እስራኤል ከአየር ጥቃት በተጨማሪ ሊባኖስ ላይ ወረራ በመፈጸም የተቀናጀ ጥቃቷን አጠናክራ መቆየቷ ይታወሳል።በሊባኖስ ውስጥ በአስርት ዓመታት ውስጥ ከታዩ የከፋ በተባለው በዚህ ጦርነት ከ3 ሺህ 823 በላይ ነዋሪዎች መገደላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንደታቀደው ረቡዕ፣ ህዳር 18/ 2017 ዓ.ም እንደተጀመረ ተገልጿል።
@Esat_tv1