ምክር ቤቱ ነገ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል‼️
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በ11ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ከተወያየ በኃላ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡ረቂቅ አዋጁ ሰኔ 18 ቀን 2ዐ16 ዓ.ም. ለፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መመራቱ የሚታወስ ነው፡፡
በወቅቱም ረቂቅ አዋጁ ብሔራዊ ባንክ በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ ከሚኖሩ ለውጦች ጋር እንዲጣጣም እና የቁጥጥር አቅሙን እንዲያጎለብት የሚያስችለው ነው ተብሏል፡፡አሁን በሥራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዋጅ ማሻሻያ ሳይደረግበት ለ16 ዓመታት እንደቆየ የተገለጸም ሲሆን፤ ሰፋ ያሉ ሕጋዊና አስተዳደራዊ ክፍተቶች እንዳሉበት መታየቱ ተነስቶ ነበር፡፡
ረቂቅ አዋጁ የብሔራዊ ባንክ አደረጃጀት፣ አላማና ተግባር፣ ስለ ብሔራዊ ባንክ አስተዳደር፣ ባንኩ ከመንግሥትና ከፋይናንስ ተቋማት ጋር ስለሚኖረው ግንኙነትና ሌሎችንም ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች አካትቶ ስለመያዙም ተመላክቷል፡፡
በዚሁ መሰረት በነገው መደበኛ ስብሰባ የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ እንደሚያቀርብ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ምክር ቤቱም ቋሚ ኮሚቴው የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
@Esat_tv1