የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ49 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ በመያዝ የኮንጎ አየር መንገድን ስራ ማስጀመሩ ተገለጸ‼️
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ መንግስት ጋር በጋራ በመሆን “ኤር ኮንጎ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አየር መንገድ አቋቁሞ በይፋ ስራ ማስጀመሩን አስታወቀ።በይፋ ስራውን በጀመረው የኮንጎ አየር መንገድ የሀገሪቱ መንግስት 51 በመቶ የሚሆነውን አብላጫውን ድርሻ መያዙ የተገለጸ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ 49 በመቶ ድርሻ በመያዝ አየር መንገዱን እንደሚያስተዳድር ተጠቁሟል።
ኤር ኮንጎ በሁለት ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ሰባት ኤርፖርቶች በረራ በማድረግ አገልግሎት መጀመሩን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮንጐ ዜጎችን በአብራሪነት፣ በበረራ ሰራተኝነት፣ በሽያጭና አገልግሎት ሰራተኞች እና በቴክኒሻንነት አሰልጥኖ ለማብቃት በስምምነቱ ላይ መካተቱን መረጃው አመላክቷል።
ይህ ጥምረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራዕይ 2035 አንዱ አካል መሆኑን የጠቆመው መረጃው ከዚህም በፊት በሎሜ አስካይ አየር መንገድ፣ በሊሎንግዌ የማላዊ አየር መንገድ እንዲሁም በሉሳካ የዛምቢያ አየር መንገድን በጋራ ማቋቋሙን አስታውሷል።
@Esat_tv1