መንግስት የርዕደ መሬት በታየባቸው አካባቢዎች የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረገ እንደሚገኝ ገለጸ‼️
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው ወቅታዊ መረጃ፤ በአፋር፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ማዕከላቸውን አድርገው የተለያየ መጠን ያላቸው የርዕደ መሬት ክሥተቶች በተደጋጋሚ መከሠታቸው ይታወቃል ብሏል።
ክሥተቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠን እና በድግግሞሽ እያደጉ መሆናቸውን ገልጾ፤ በተለይም በዚህ ሳምንት በርዕደ መሬት መለኪያ እስከ 5 ነጥብ 8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ መንቀጥቀጥ መከሠቱን መረጃዎች ያሳያሉ ሲል አመልክቷል።
መንግሥት ክሥተቶቹን በዘርፉ ባለሙያዎች በቅርብ እየተከታተለ ይገኛል ያለው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፤ በተለይ የርዕደ መሬቱ ማዕከል የሆኑት አካባቢዎችን በመለየት በ12 ቀበሌዎች ላይ መንግሥት ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረገ ይገኛል ሲል ገልጿል።
በእነዚህ ቀበሌዎች ከሚኖሩ 80 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማራቅ ለማሥፈር ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ነው በማለትም ጠቁሟል።
በማኅበራዊ አግልግሎት ሰጭ ተቋማት፣ በኢኮኖሚ ተቋማት እና በመሠረተ ልማት ላይ ሊኖረው የሚችለው ተጽዕኖ ላይ ክትትል እየተደረገ መሆኑንም አመልክቷል።
እስካሁን ባለው ሁኔታ በዋና ዋና ከተሞች የጎላ ተጽዕኖ ያላደረሰ ቢሆንም ዜጎች በባለሙያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መልእክቶችን እንዲከታተሉና በጥብቅ እንዲተገብሩ አሳስቧል።
በቀጣይም ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል አስፈላጊ መረጃዎችን በሚመለከታቸው ተቋማት አማካይነት የሚያደርስ መሆኑንም አስታውቋል።
@Esat_tv1