ሐማስ ታጋቾችን የሚለቀው በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት መሠረት መሆኑን አስታወቀ‼️
እስራኤል ከተወሰኑ የጋዛ አካባቢዎች መውጣቷን ተከትሎ ፍልስጤማዊያን ወደ ቀያቸው መመለስ ጀምረዋል
ከ 2 ሰአት በፊት ሐማስ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት መሠረት ታጋቾችን መልቀቅ እንደሚቀጥል አስታወቀ።
ይህን የሐማስ ውሳኔ ተከትሎ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ፈርሶ ድጋሚ ጦርነት ሊጀምር ይችላል የሚለው ስጋት ቀንሷል።
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን በግብፅ ከተካሄደ ውይይት በኋላ በሰጠው መግለጫ የግብፅ እና የኳታር አደራዳሪዎች "እንቅፋቶችን ያስወግዳሉ" ብሏል።
የግብፅ እና የኳታር አደራዳሪዎችም ተፈጥሮ የነበረው አለግባባት መፈታቱን አስታውቀዋል።
የእስራኤል መንግሥት ቃል አቀባይ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ባይሰጡም ቡድኑ በሚቀጥለው ቅዳሜ ሶስት ታጋቾችን የማይለቅ ከሆነ ጦርነት ይጀመራል ብለዋል።
ሐማስ፤ እስራኤል ስምምነቱን ጥሳለች በሚል ታጋቾችን እንደማይለቅ ማስታወቁን ተከትሎ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለፈው ማክሰኞ ጦርነት ይጀመራል የሚል ዛቻ አሰምተው ነበር።
ሐማስ፤ መጠለያዎችን ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ ሰብዓዊ እርዳታዎች እንዳይደርሱ አድርጋለች ሲል ነው እስራኤልን የከሰሰው። እስራኤል የሐማስን ወቀሳ ታስተባብላለች።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ስምምነቱን እንድታቋርጥ ሐሳብ አቅርበው "ሁሉም ታጋቾች ቅዳሜ የማይፈቱ ከሆነ ገሀነም ይወርዳል" ማለታቸው ይታወሳል።
@Esat_tv1