በአዲስ አበባ ቢቂላ መናፈሻ በሚባለው አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ‼️
ዛሬ ከቀኑ 9:33 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ካራ ቆሬ ቢቂላ መናፈሻ በሚባለው አካባቢ ለፍራሽ መስሪያ የሚሆኑ ግብአቶች በተከማቹበት መጋዘን ላይ የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የእሳት አደጋውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የጸጥታ አካላት እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።
በዚህም እሳቱ በአቅራቢያው ወዳለው መስኪድ እንዲሁም ሌሎች የመኖሪያና ንግድ ቤቶች እንዳይዛመት ማድረግ መቻሉን ኮሚሽኑ ገልጿል።
በእሳት አደጋው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንም ኮሚሽኑ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
@Esat_tv1