የቱርኩ ፕሬዝደንት ተቀናቃኛቸውን ማሰራቸውን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ ተፋፋመ‼️
የፕሬዝደንት ጣይብ ረሲፕ ኤርዶዋን ቀንደኛ ተቀናቃኝ በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸውን ተከትሎ በመላው ቱርክ የተነሳው ከፍተኛ ተቃውሞ ተባብሶ ቀጥሏል።
ኤክሬም ኢማሞግሉ የኢስታንቡል ከንቲባ ሲሆኑ ባለፈው ከሶስት ዓመታት በኋላ ለሚካሄደው ምርጫ የሪፐብሊካን ፒፕልስ ፓርቲ (ሲኤችፒ) ዕጩ ሆነው እሑድ ዕለት ይመረጣሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር።
ሰውየው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተከትሎ ቱርክ ላለፉት 10 ዓመታት አይታ በማታወቅ ተቃውሞ የተናጠች ሲሆን ፖሊስ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጪስ እና የጎማ ጥይት ተኩሷል።
ኢማሞግሉ እሳቸው ላይ የተከፈቱ ክሶች ፖለቲካዊ እንደሆኑ በመናገር "በፍፁም አላጎበድድም" ሲሉ በቁጥጥር ሥር ከመዋላቸው በፊት በኤክስ ገፃቸው ፅፈዋል።
ኤርዶዋን ሰልፎቹን ወቅሰው ሲኤችፒ "ሰላማችንን ሊበጠብጥ እና ሕዝባችንን ሊከፋፍል የተነሳ" ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
ለአምስተኛ ተከታታይ ምሽት በርካታ ሰዎች በኢስታንቡል ከተማ አዳራሽ አመሻሹን እየተገኙ የቱርክ ባንዲራ እያውለበለቡ ከአድማ በታኝ ፖሊስ ፊት ለፊት ሲዘምሩ እና ሲጮሁ ታይተዋል።
አንዳንድ የፖሊስ መኮንኖች ግፊት ያለው ውሀ እና የሚያቃጥል ኬሚካል ሲረጩ ታይተዋል።
የኢማሞግሉ ባለቤት ዲሌክ ካያ ኢማሞግሉ ለተሰበሰበው ሕዝብ ባደረጉት ንግግር ባላቸው የተጋፈጠው "ኢ-ፍትሐዊነት" ማንም ሊቀበለው የሚገባ እንዳልሆነ ገልፀዋል።
በአውሮፓውያኑ 2013 በቱርክ ከተከሰተው የጌዚ አመፅ በኋላ በሀገሪቱ ታሪክ ትልቁ የሚባል ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
ከቱርክ 81 ግዛቶች መካከል 55 በሚሆኑ የተቃውሞ ሰልፍ እየተደረገ መሆኑን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ኤኤፍፒ ዘግቧል።
@Esat_tv1