የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደት ቴክኖሎጂን መሰረት እንዲያደርግ አቅጣጫ ተቀመጠ
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደታቸው ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ እንዲሆን አቅጣጫ መቀመጡን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደተናገሩት፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን የሚያስጠብቁ እንዲሆኑ የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮች ተዘርግተዋል።
ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ የመማር ማስተማር ሂደት፣ ጥሩ የትምህርት ከባቢን ጨምሮ የመምህራን ድጋፍ፣ በቴክኖሎጂ የተደራጀ ቤተመጻሕፍት እንዲኖራቸው ይጠበቃል ብለዋል።
ተቋማቱ በውጤት የሚመዘኑበት ቁልፍ መለኪያዎች ላይ ተመስርተው እንዲሰሩ አቅጣጫ መቀመጡን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ውጤታማ ተግባር በማከናወን ተማሪዎቻቸው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን በብቃት እንዲያልፉ ማስቻል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የመውጫ ፈተናን ማሳለፍ ካልቻሉ ተቋማቱ የሚገመገሙበትና ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር መዘርጋቱን ገልጸዋል።
@Ethio_fastnews🤩