አዲሱ የባንክ ስራ አዋጅ ያካተታቸው ተጨማሪ ድንጋጌዎች የትኞቹ ናቸው?
ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8፤ 2017 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የባንክ ስራ አዋጅ፤ በረቂቅ ደረጃ ከነበረው ይዘት የተወሰኑ ማሻሻያዎች ተደርገውበታል።
በሶስት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ የጸደቀው ይህ አዋጅ፤ በረቅቁ ላይ ተካትተው በነበሩ ትርጓሜዎች እና ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።
ማሻሻያ ከተደረገባቸው ድንጋጌዎች መካከል የባንክ ቅርንጫፎች እና የውጭ ባንኮችን የተመለከቱት ይገኙበታል። የውጭ ዜጎች በባንክ ስራ የሚሳተፉበትን አካሄድ በሚዘረዝረው የአዋጅ ክፍል ላይ አዲስ አንቀጽ እንዲካተት ተደርጓል።
በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋ በባንክ ስራ ስለሚሰማራበት ሁኔታ በረቂቁ ላይ ከተቀመጠው በተጨማሪም አዲስ ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ ላይ ተካትቷል።
ከማሻሻያዎቹ እና ከአዳዲስ አንቀጾች ውስጥ የተወሰኑት በ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተጠናቅረዋል። ዝርዝሩን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/14627/
@EthiopiaInsiderNews