የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች ለሀገር አቀፍ ምክክር እንዲቀርቡ የጠቆሟቸው አጀንዳዎች የትኞቹ ናቸው?
የኦሮሚያ ክልል የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮቹ በመጪው ሀገር አቀፍ የምክክር አጀንዳነት እንዲያዙ ተደጋጋሚ ጥቆማ ካቀረቡባቸው ጉዳዮች ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ የባለቤትነት ጉዳይ ይገኝበታል።
የፌደራል የስራ ቋንቋ፣ የሰንደቅ አላማ፣ የክልላዊ አስተዳደር ወሰን እንዲሁም ሰላም እና ጸጥታን የተመለከቱት ጉዳዮችም እንዲሁ በተወካዮቹ በተደጋጋሚ የተነሱ አጀንዳዎች ናቸው።
ከምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ጎቢሰዩ ወረዳ ወጣቶችን በመወከል በአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረኩ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው አቶ ቡሻ ጎተታ “አዲስ አበባ ከተማ ባለቤትነቷ የኦሮሞ ህዝብ መሆኑ በህግ እንዲደነገግ፣ አፋን ኦሮሞ የፌደራል የስራ ቋንቋ እንዲሆን፣ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው የሸኔ ታጣቂ ቡድን አባላት እጃቸውን እንዲሰጡ” የሚጠይቁ አጀንዳዎች በትላንትናው የምክክር ውሎ ጎልተው መውጣታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
የመንግስት ሰራተኞችን በመወከል ከአርሲ ዞን፣ በሌ ገስካር ወረዳ በምክክር ሂደቱ እየተሳተፉ የሚገኙት አቶ መለሰ ተፈራ የተባሉ ተወካይ፤ እርሳቸው በሚገኙበት ቡድን ጎልቶ የወጣው የታሪክ ጉዳይ እንደሆነ አስረድተዋል።
የማህበረሰብ መሪዎችን በመወከል ከጅማ ዞን፣ ሸቤ ሶንቦ ወረዳ የመጡት አቶ ኢብራሂም አባጅሀድ “በሌሎች ክልሎች ስር ያሉ የኦሮሞ መሬቶች እንዲመለሱ፣ በጫካ ያሉ ኃይሎች ወደ ምክክሩ እንዲመጡ” የሚጠይቁ አጀንዳዎች መቅረባቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።
🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ:- https://ethiopiainsider.com/2024/14640/
@EthiopiaInsiderNews