በሐረር ከተማ የታሸጉ 35 የባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት ወደ መስጠት እንዲመለሱ ለሀረሪ ክልል አቤቱታ ቀረበ
የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር በሐረር ከተማ የታሸጉ 35 የባንክ ቅርንጫፎች ተከፍተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ እንዲደረግ ለሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቤቱታ አቀረበ።
የክልሉ መንግስት ቅርንጫፎቹ የታሸጉት “ግንባታቸው ባላለቁ ህንጻዎች አገልግሎት እየሰጡ በመሆኑ ነው” ቢልም፤ ማህበሩ ግን ከሌሎች የንግድ ድርጅቶች በተለየ መልኩ እርምጃው በእነርሱ ላይ መወሰዱ ለክልሉ የኮሪደር ልማት የተጠየቀው መዋጮ ተግባራዊ ባለመደረጉ ምክንያት የተፈጸመ እንደሆነ “ከድምዳሜ ላይ እንዲደርስ” እንዳደረገው ገልጿል።
በሀረሪ ክልል የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ባንኮች የሁለት ሚሊዮን ብር “ድጋፍ” እንዲያደርጉ በደብዳቤ የተጠየቁት የዛሬ ሶስት ሳምንት ገደማ ነው።
ደብዳቤውን ለባንክ ቅርንጫፎች የጻፈው የሀረሪ ክልል የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ፤ የገንዘብ መጠኑን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ገቢ እንዲያደርጉ ቀነ ገደብ ሰጥቷቸው ነበር።
ሃያ ስድስት ባንኮችን በአባልነት ያቀፈው የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር፤ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ታህሳስ 9፤ 2017 ለሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በጻፈው ደብዳቤ፤ የባንክ ቅርንጫፎች የተጠየቁትን ያህል የገንዘብ መጠን በመዋጮ መልክ ለመክፈል “ስልጣን እንደሌላቸው” ገልጿል።
የገንዘብ መዋጮ ጥያቄው በባንኮቹ “ዋና መስሪያ ቤት ታይቶ” እንዲሁም “በቂ በጀት የተመደበለት መሆኑ ተረጋግጦ” የሚፈቀድ መሆኑንም ማህበሩ አመልክቷል።
🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2024/14648/
@EthiopiaInsiderNews