በመሬት መንቀጥቀጥ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች፤ አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግላቸው ጠየቁ
ቪዲዮ(1):- በአፋር ክልል የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ በተከሰተባቸው ስፍራዎች የሚኖሩ ነዋሪዎችን፤ የአደጋ ስጋት ወደሌለባቸው ቦታዎች የማጓጓዝ ስራ ዛሬ ቅዳሜ ታህሳስ 26፤ 2017 በስፋት ሲከናወን ውሏል።
ከከሰም የስኳር ፋብሪካ አቅራቢያ በሚገኘው እና በተለምዶ “ቀበና” ተብሎ በሚጠራው አነስተኛ ከተማ ያሉ ነዋሪዎች፤ በዛሬው ዕለት አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርገዋል።
ዛሬ ረፋዱን በስፍራው የነበረ አንድ የዓይን እማኝ፤ የተወሰኑ የከተማይቱ ነዋሪዎች በስድስት ወታደራዊ ካሚዮን ተጭነው ሲጓጓዙ መመልከታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
ጥቂት ንብረቶቻቸውን ይዘው አካባቢውን የለቀቁ እነዚህ ነዋሪዎች፤ ለጭነት ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች የሚያውሉት ገንዘብ የሌላቸው ናቸው።
በተሻለ የገቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ ጥቂት ነዋሪዎች፤ የጭነት መኪናዎችን በመከራየት ወደ አዋሽ አርባ፣ ወደ አዋሽ ሰባት እና ሌሎችም ከተሞች ንብረቶቻቸውን ሸክፈው ሲጓዙ በስፍራው የነበረው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ ተመልክቷል።
ነዋሪዎቹ እንደ “አይሱዙ” ያሉ የጭነት መኪናዎችን ለመከራየት ከ10 ሺህ እስከ 15 ሺህ ብር እንደሚጠየቁም ዘጋቢው ተረድቷል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
🔴 ተፈናቃዮች ያሉበትን ሁኔታ እና ያቀረቡትን ተማጽኖ በቪዲዮ ለመመልከት ▶️ https://youtu.be/QPiMGGunsm0?feature=shared
@EthiopiaInsiderNews