በአፋር ክልል ባለ ብሔራዊ ፓርክ ባለፈው ቅዳሜ የተቀሰቀሰ ሰደድ እሳት እስካሁን በቁጥጥር ስር አለመዋሉ ተገለጸ
በአፋር እና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል በሚገኘው ሃላይዳጌ አሰቦት ብሔራዊ ፓርክ ከትላንት በስቲያ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት እስከ ዛሬ ሰኞ እኩለ ቀን ድረስ በቁጥጥር ስር አለመዋሉን የፓርኩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ እድሪስ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። በሰደድ እሳቱ 200 ሄክታር የሚገመት የፓርኩ ክፍል መቃጠሉን ኃላፊው ገልጸዋል።
ከ1965 ዓ.ም ጀምሮ የዱር እንስሳት ጥብቅ ቦታ ሆኖ የቆየው ሃላይዳጌ አሰቦት ብሔራዊ ፓርክ፤ 1099 ገደማ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ነው።
ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ብሔራዊ ፓርክ ደረጃ ያደገው ጥብቅ ቦታው፤ የ325 የእጽዋት ዝርያ፣ የ244 የአእዋፍ ዝርያ እና ከ42 በላይ አጥቢ እንስሳት መኖሪያ ነው።
በኢትዮጵያ እና በኬንያ ብቻ የሚገኝ የሜዳ አህያ ዝርያ እንዲሁም ሳላ የተሰኘው አጥቢ እንስሳ በብዛት በሚገኝበት በዚህ ፓርክ፤ የእሳት አደጋ የተከሰተው ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ የካቲት 1፤ 2017 ከቀኑ ስምንት ሰዓት በኋላ ባለው ጊዜው ውስጥ ነው።
እሳቱ በከፍተኛ ንፋስ የታገዘ በርካታ ቦታ ማዳረሱን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተናገሩት የፓርኩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፤ እሳቱን ለማጥፋት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የአካባቢው አስተዳደር ሰራተኞች ርብርብ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15018/
@EthiopiaInsiderNews