ከአማራ ክልል ተማሪዎች 60 በመቶ የሚጠጉት “ከትምህርት ገበታ ውጭ” መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩ አስታወቁ
በአማራ ክልል ከሚገኙ ተማሪዎች ውስጥ 59.8 በመቶ የሚሆኑት፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን “ከትምህርት ገበታ ውጭ” መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ተናገሩ።
በክልሉ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 32 በመቶ የሚሆኑት ከመማር ማስተማር ተልዕኮዋቸው “መስተጓጎላቸውንም” ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል።
አቶ አረጋ ይህንን ያሉት፤ ትላንት ማክሰኞ የካቲት 4፤ 2017 ዓ.ም በተጀመረው እና ዛሬም በቀጠለው የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ነው። አቶ አረጋ በዚሁ ሪፖርታቸው ካነሷቸው ጉዳይ መካከል በክልሉ ያለውን የትምህርት ሁኔታ የተመለከተው ይገኝበታል።
በአማራ ክልል በአሁኑ ወቅት “በተጨባጭ በመማር ማስተማር ሂደት እየተሳተፉ” የሚገኙ ተማሪዎች ብዛት 2.78 ሚሊዮን እንደሆኑ ርዕሰ መስተዳድሩ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ጠቅሰዋል።
ይህ አሃዝ በክልሉ በትምህርት ገበታቸው ላይ ሊገኙ የገባቸው ከነበሩ ተማሪዎች ውስጥ 40.2 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ብቻ የሚሸፍን እንደሆነም አቶ አረጋ አስረድተዋል።
“ቀሪ 59.8 በመቶ የሚሆነው ተማሪ ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆኑን ለተከበረው ምክር ቤት ማስረዳት ያስፈልጋል” የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በትላንቱ ጉባኤ ውሎ ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል።
🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15040/
@EthiopiaInsiderNews