የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን ለሶስት ወራት ከማንኛውም የፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አገደ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ለሶስት ወራት “በምንም አይነት” ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዳይሳተፍ አገደ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ የሚያስችል “የእርምት እርምጃ” ካልወሰደ፤ የፓርቲው ምዘገባ በቀጥታ እንደሚሰረዝ ቦርዱ አስታውቋል።
ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ ይህን ያስታወቀው፤ ህወሓትን በተመለከተ ዛሬ ሐሙስ የካቲት 6፤ 2017 ባወጣው መግለጫ ነው። ቦርዱ ለህወሓት ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት “በልዩ ሁኔታ” መስጠቱን የገለጸው፤ በነሐሴ 2016 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ነበር።
ይህ እርምጃ በጥር 2013 ዓ.ም. በምርጫ ቦርድ አማካኝነት ከፓርቲነት የተሰረዘው ህወሓትን፤ ወደ “ህጋዊ ሰውነት” የመለሰ እንደሆነ በወቅቱ ተገልጾ ነበር። ቦርዱ ህወሓትን ከፓርቲነት ሰርዞ የነበረው፤ “ኃይልን መሠረት ባደረገ የአመጻ ተግባር ላይ መሳተፉን” እንዳረጋገጠ በመጥቀስ ነበር።
ለህወሓት ህጋዊ ሰውነት ማጣት በምክንያትነት ተጠቅሶ የነበረው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፤ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተካሄደ የግጭት ማቆም ስምምነት በጥቅምት 2015 ዓ.ም. መቋጨቱ ይታወሳል።
ስምምነቱን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈራረመው ህወሓት፤ ህጋዊ ሰውነቱ እንዲመለስ ለቦርዱ ያቀረበው ጥያቄ “በህግ የተደገፈ አይደለም” በሚል ውድቅ ተደርጎ ነበር።
🔴 ለዝርዝሩ:- https://ethiopiainsider.com/2025/15059/
@EthiopiaInsiderNews