አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለድህረ ምረቃ ትምህርቶች በሰዓት ከ900 እስከ 4,615 ብር ሊያስከፍል ነው
ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ መሆኑን ተከትሎ ለድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች አዲስ የትምህርት ክፍያ ፖሊሲን እና መመሪያን ነሐሴ 2016 በሴነቱ አጽድቋል። በዚሁ መሰረት ለማስተርስ (ወይም ሁለተኛ ዲግሪ) መርኃ ግብር በሰዓት ከ900 እስከ 3,462 ብር እንደ ሙያ መስኩ የክፍያ ተመን አስቀምጧል።
በተመሳሳይ ለፒኤችዲ መርኃ ግብር በሰዓት ከ1,200 እስከ 4,615 ብር እንደ ሙያ መስኩ የክፍያ ተመን ማዘጋጀቱ ታውቋል። ለመመረቂያ እና ለምርምር ለማስተርስ ከ675 እስክ 900 ብር፣ ለፒኤችዲ ደግሞ 18,000 ብር በሴሚስትር ተመን አውጥቷል።
አዲሱ የክፍያ ተመን ተግባራዊ የሚሆነው ከዘንድሮው የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ1ኛ ወሰን ትምህርት ጀምሮ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡ በተጨማሪም የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች በየሴሚስትሩ 300 ብር የመመዝገቢያ ክፍያ ተጥሎባቸዋል። ሁሉም ክፍያዎች ለኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው ያስታወቀ ሲሆን ክፍያዎቹ በዚህ ከፍተኛ መጠን ለምን እንደጨመሩ የሰጠው ማብራርያ የለም። #Meseret_Media
@Ethiopian_Digital_Library