የጾታዊ ጥቃት አድራሾችን የሚመዘግበው የዲጂታል የመረጃ ሥርዓት በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል ተባለ
ከእለት ተእለት እጨመረ ለመጣው የሴቶችና የሕፃናት ጥቃት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተማሪ ሕግ እየተረቀቀ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናግረዋል። በአሁኑ ሰአት ቀደም ሲል የነበረውን ሕግ ለማሻሻል፤ ሕጉን የመፈተሽ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ማሻሻያው በቀደመው ሕግ ላይ የነበሩበትን ክፍተቶች በመለየት የመከላከሉን ሥራ ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ ተጨማሪ ጠንካራ ሕጎች እና አሠራሮች ተግባራዊ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል፡፡
የሕጉ መሻሻል ያስፈለገው በሴቶችና በሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየጨመሩ መምጣታቸው ፣ጥቃቶቹ በምስክር ፊት የሚደረጉ አለመሆናቸው፣ ከዛም ባለፈ ጥቃቶች እየረቀቁ በመምጣታቸው እንደሆነም ነው የገለጹት። ከሕግ ማሻሻያ ሥራው ጎን ለጎን ጥቃት አድራሾችን መመዝገብ የሚያስችል ዲጂታል የመረጃ ሥርዓት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን እየጎለበተ እንደሚገኝም አስታውሰዋል፡፡ ይህ የመረጃ ሥርዓት ጥቃት አድራሾች ጥቃቱን ሲፈጽሙ መረጃቸው ተመዝግቦ ከዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቱ ጋር እንዲያያዝ እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡
የሚለማው የዲጂታል ሥርዓት ጥቃት አድርሶ እንደተፈለገ መኖር እንደማይቻል እና ቀድሞ ማሰብ እንደሚገባ የሚያደርግ መተግበሪያ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ የማልማት ሥራውም በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል ሲሉ ገልጸዋል። #ኢፕድ
@Ethiopian_Digital_Library