ከፊታችሁ የቆምኩት በፈጣሪ ተዓምር ነው
የመጀመሪያ ድግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ለመመረቅያ ፅሁፋቸው ድፌንስ ዘንጦ ቀርበዋል። ከመካከላቸው አንዱ ተማሪ ግን በተራ አለባበስ እና በተበጣጠሰች የነጠላ ጫማ ቀረበ። ለድፌንስ የተዘጋጁ መምህራን በልጁ ግድየለሽ አለባበስ ተበሳጭተው ይሰድቡትና ይዘልፉት ጀመር፡፡ ዘለፋና ስድባቸውን ከጨረሱ በኋላ እንባ እየተናነቀው መናገር ጀመረ...."እኔ የድግሪ መመረቂያ ፅሁፌን ለማቅረብ እዚህ ከፊታችሁ የቆምኩት በፈጣሪ ተዓምር ነው። አቅሜ በፈቀደው ልክ በጥሩ አለባበስ ቀርብያለሁ።
"ቤተሰቦቼ በጣም ባለፀጋ ነበሩ። የ9 አመት ልጅና የ4ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ እናትና አባቴ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ። ከሁለት እህቶቼ ጋር ብቻችንን ቀረን። የአባቴ ታናሽ አጎቴ ለተወሰኑ ዓመታት ከቤቱ ካጠለለን በኋላ የቤተሰቦቻችንን ሀብት ንብረት በመውረስ ከቤቱ አባረረን። ሳገኝ እየሰራሁ ሳጣ እየለመንኩ እህቶቼንና እራሴን እመግብ ነበር።
"በዚህ ሁኔታ እያለን እኔና እህቶቼ የተሻለ ትምህርት በመማር ህይወታችንን መቀየር እንዳለብን ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡ ግማሽ ቀን ከሰው ማሳ ላይ እያረስኩኝ እህቶቼን እየመግብኩ ግማሽ ቀን የግንባታ ስራ እየሰራሁ አስተምራቸዋለሁ፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን እስከ ዛሬ ቃሌን ለመጠበቅ ችያለሁ። እኔ ድግሪዬን ልመረቅ ነው፣ ሁለቱ እህቶቼንም ኮሌጅ እያስተማርኳቸው ነው። ዛሬ እንደ ጓደኞቼ ዘንጬ ለመምጣት አስቤ ነበር፡ እህቶቼ የስሚስቴር የትምህርት ክፍያ ተጠይቀው ለሱፍና ጫማ ያዘጋጀሁትን ገንዘብ ለመላክ ተገደድኩ…"
"ከፊቱ ተቀምጠው ሲሰድቡትና ሲዘልፉት የነበሩ መምህራን አንገታቸውን ደፉ። ከመምህራኖች መካከል አንዷ፦"እባክህን ከዚህ በላይ አተናገር ። ለመስማት የሚሆን ጥንካሬ የለኝም" አለች እንባ እየተናነቃት። ተማሪው የመመረቅያ ፅሁፍን ዲፌንስ በሚገባ ተወጣ ። ሳይረዱት የዘበቱበት መምህራን ከመቀመጫቸው ተነስተው አጨበጨቡለት፡፡ ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ::
@Ethiopian_Digital_Library