ባሻዬ! ዛሬ ለካ የፍቅረኞች ቀን ነው። አንዷ የጨርቆስ ልጅ "የፍቅረኞች ቀን Valentine's Day የሚባለውን አልወደውም" አለችኝ።
እኔም "ለምን?" ብዬ ስጠይቃት ዝርዝሩን አጫወተችኝ፣
አንድ ቀን የፍቅረኞች ቀን ዕለት ዝንጥ ብላ ስትሄድ አንድ በዕድሜው ጠና ያለ ሰው መኪናውን አቆመና ልሸኝሽ አላት። እሺ ብላ መኪናው ውስጥ ገብታ በዚያው ቀረች።
አብረው መኖር ከጀመሩ በኋላ ዕድሜ ጠገቡ ሰውዬ እየቆየ ክፉ ባህሪውን ማሳየት ጀመረ። የቤቱን የምግብ ፍጆታ ለቤተሰቦቿ ትሰጣለች ብሎ ስለሚያስብ እሷ ከቤት ስትወጣ እሱ ደሞ መሶብ ከፍቶ የመሶቡን ክዳን ጭንቅላቱ ላይ ደፍቶ እንጀራ ይቆጥራል።
ሰውዬው ምንም ስህተት ሲያጣባት ምናልባት ከእንጀራው ይልቅ በሊጥ መልክ ለቤተሰቦቿ ትሰጣለች ብሎ ስለሚያስብ እንደ መኪና ዘይት ሊጡን በረጅም እንጨት deep stick ሊቤሎ ለክቶ ወደ ሥራው ይሄዳል።
ሰውዬው ስለሚቀና አንዳንዴ ከሥራ ሲመለስ ጫማዎቿን እያገላበጠ ያይና አቧራ ካገኘ የት ሄደሽ ነበር እያለ እንደ ምርጥ ተጫዎች እየተወረወረ በቴስታ ይመታታል። በዚህ ተማርራ ቤቱን ጥላለት ወጣች።
ባሻዬ! ልጅቷ ባትነግረኝም ሰውዬው የቤቱን ቅቤ ለቤተሰቦቿ ትሰጣለች ብሎ ስለሚያስብ የቅቤ መያዣውን ከፍቶ የረጋው ቅቤ ላይ በጣቱ ለምልክት ፈርሞበት እንደሚወጣ ልቤ ጠርጥሯል።
ይቺ ልጅ የፍቅረኞች ቀን በመጣ ቁጥር ያንን የመጋዘን ተቆጣጣሪና የካዝና ቁልፍ የሆነው ባሏን ታስታውሰዋለች።
ሴቶቻችን ዛሬ በፍቅረኞች ቀን ደስታ ተሰምቷችሁ ከተዘናጋችሁና ነገ ጠዋት ፋርማሲ ከተዘጋባችሁ ከወዲሁ መልካም የእናቶች ቀን እመኛለሁ።
Tesfaye Hailemariam
@Ethiopian_Digital_Library