✝️✨ ጾመ ነነዌ ✨✝️
ነነዌ የአሦር ጥንታዊ ከተማ ነበረ። ፍርስራሹ በጤግሮስ ወንዝ ምሥራቅ ዳርቻ በሞሱል ዙሪያ አሁን አለ። ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትሆን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ የምትጀመረው ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አትለቅም ቀኑ ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር 17 ድረስ ነው ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ እስከ የካቲት 24 ቀን ይረዝማል፡፡
በእነዚህ 35 ቀናት ውስጥ ስትመላለስ ከፍ ዝቅ ስትል ትኖራለች ከተጠቀሱት ዕለታት አባቶች እንደ ደነገጉት አትወርድም አትወጣም በዚህ ዓመትም የካቲት 03 ቀን ትጀመራለች፡፡ አጭርና የሦስት ቀን ጾም ብትሆንም እንኳ እጅግ ብዙ ጥቅምን የምታስገኝ ጾም ናት፡፡ ይህም "በመባጃ ሐመር ከፍና ዝቅ ስለሚል ቊጥሩ ከአጽዋማት ሐዋርያት ነው፡፡ አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል፡፡" ታዲያ ነነዌ ማን ናት? ነነዌ በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ ናምሩድ በተባለው ሰው ተመሠረተች፡፡ ለአሰራውያን መናገሻ ከተማ ነበረች፡፡ ሰፊና ውብ ከተማ ሆና የተገነባች ናት፡፡ [ዘፍ. 10:1] አስር ከእስራኤላውያን ጋር ጠላት ሆነው በተቀናቃኝነት የኖሩ መንግሥታት ናቸው፡፡ ዮናስ የተላከው ተቀናቃኝ ወደ ሆኑት ሕዝቦች ነው፡፡ ከተማዋ ውብና ብዙ ሕንፃዎች ነበሩባት የከተማዋ ቅጽር ርዝመት 12 ኪ.ሜ እንደነበር በውስጧ ብዙ ሕንፃዎች ተሠርተውባት ነበር፡፡ የባቢሎን መንግሥት ከክርስቶስ ልደት በፊት ከተማዋን አፈረሳት፡፡ [ዮና.4.1]
ሕንፃዎቿን የሠራቸው ሰናክሮም ሲሆን በስተመጨረሻ በ621 ዓ.ዓ የባቢሎን መንግሥት አፍርሷታል፡፡ ነነዌ ዛሬ የኢራቅ ከተማ ምሱል ናት በኩሽ ልጅ ናምሩድ በ1800 ዓ.ዓ ተቆረቆረች፡፡ ሽታር ወይም አስታሮትን ያመልኩ ነበር በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ገጥሟታል፡፡
ታዲያ ለነነዌ ሰዎች የተላከው ዮናስ ከአባቱ አማቴ እና ከእናቱ ሰና እንደተወለደ ታሪኩ ይነግረናል፡፡ ዮናስ ኤልሳዕ ያዳነላት የሰራጵታዎ ሴት ልጅ ነው የሚሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን ይነግሩናል፡፡ ነገር ግን ስለ ነቢዩ ዮናስ ጥልቀት ያለው ታሪክና መረጃ በስፋት አልተገለጸም፡፡ የስሙ ትርጉምም ቢሆን በእብራይስጥ ቋንቋ ርግብ የሚለው ትርጉም እንደሚገልጸው መተርጉማኑ ይገልጻሉ፡፡
ከእግዚአብሔር ዘንድ ለዮናስ የመጣው መልእክት "ክፋቷ በእኔ ፊት ወጥቷልና ወደ ታላቂቷ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ፣ በእርሷ ላይ ስበክ፡፡" [ዮና. 1.1] የሚል ነበር፡፡ ዮናስ ግን ጥሪውን መቀበል ባለመፈለጉ ኮበለለ፡፡ ከእግዚአብሔር መኮብለል አያዋጣምና ነብዩ ዮናስ በትልቅ አሣ እንዲዋጥ ተደረገ፡፡ በዚህ ውስጥ ዮናስ የትንቢት ቃሉን ለነነዌ ሕዝብ ማድረስ እንዳለበት ተረዳ፤ እግዚአብሔር ለኹለተኛ ጊዜ የነገረውን ድምጽም ሰምቶ ወደ ነነዌ ሄደ፡፡
በወቅቱ ነነዌ እጅግ ታላቅ የሆነች ከተማ ነበረች፡፡ በአርኪዮሎጂ ግኝት እንደተረጋገጠውም ከተማዋ ነቢዪ ዮናስ እንዳለው የሦስት ቀን መንገድ ያህል እጅግ ታላቅ ከተማ (ዮና.3.3) ነበረች፡፡ በአሁኑ ወቅት እንዳሉ ከተማዎች ሁሉ ሕዝብ የበዛበት ነበረች፡፡ ከመቶ ሃያ ሺህ በላይ ሕዝብ ይኖርበት እንደነበረም በዚያው በነቢዩ ዮናስ መጽሐፍ ላይ ተጠቀወሶ እናነባለን፡፡ [ዮና.4.1] ሆኖም ግን በዚህ ሁሉ ውስጥ እግዚአብሔርን እጅግ የሚያሳዝን ኀጢያት ይሠራ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ነብዩ ዮናስ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ነነዌ ሕዝቦች ይዞ ሄደ፡፡ ነነዌ እንደምትገለበጥም ተነገራቸው፡፡
በዚህ ታሪክ ውስጥ ትልቁን ትምህርት የምናገኘው እዚህ ጋር ነው፡፡ እግዚአብሔር የንስሐ ጥሪን ለኁሉም ያደርጋል፡፡ ከየሰው በኩል የሚሰጠው ምላሽ ግን የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ የነነዌ ንጉስ ከተማይቱ እንደምትጠፋ በሰማ ጊዜ "ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሱንም አወለቀ፤ ማቅም ለብሶ በዐመድ ላይ ተቀመጠ፡፡" [ዮና.3.6] ከዚህም በኋላ በነነዌ ሕዝብ ዘንድ ጾም እንዲታወጅ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- "ማንም ሰው ወይም እንስሳ፣ ከብትም መንጋም ሆነ የበግ መንጋ፤ ምንም ነገር አይቅመስ፤ አይብላ፤ ውሃም አይጠጣ፡፡ ነገር ግን ሰውም እንስሳም ማቅ ይልበስ፤ ኁሉም አጥብቆ ወደ እግዚአብሔር ይጩህ ሰዎችም ኁሉ ክፉ መንገዳቸውንና የግፍ ሥራቸውን ይተው፡፡ እና እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ራርቶ ከጽኑ ቁጣው ይመለስም እንደሆነ ማን ያውቃል" [ዮና. 3:7-9] በዚህም ጥሪ ምክንያት ሕዝቡ በጾም ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ተመለሰ፡፡
እግዚአብሔርም ለዚህ የሰጠው ምላሽ እንዲህ ነው፡- "እግዚአብሔርም ምን እንዳደረጉና ከክፉ መንገዳቸውም እንዴት እንደ ተመለሱ ባየ ጊዜ ራራላቸው፤ በእነርሱም ላይ ሊያመጣ ያሰበውን ጥፋት አላደረገም፡፡" [ዮና. 3:10]
ነነዌና አንዳንድ ነገሮች
ሀ. በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የዚህ ጾም ስም "የዮናስ ጾም" ይባላል፡፡ ሆኖም ግን ቀደምት መዛግብት ላይ የሠፈሩ መረጃዎች (የነነዌ ጾም) በሚለው ይሄዳሉ፡፡ እዚህ ጋር የምንዘክረው የነነዌ ሰዎች የጾሙትን ጾም ብቻ ሳይሆን ነብዩ ለሦስት ቀን በአሣው ሆድ ውስጥ መቆየቱን እናሳስባለን፡፡
ለ. የዚህን ጾም ታሪክ ወደ ኋላ ይዘን ስንሄድ የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እናገኛለን፡፡ ይህ ጾም በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲጾም የነበረ ነው፡፡ በዚህም ጾም ምክንያት ብዙዎች ከአደጋ ለመዳን ችለዋል፡፡
ሐ. ለመሆኑ ነብዩ ዮናስን የዋጠው የባሕር እንስሳ ምንድር ነው; ግእዙ (ዐንበሪ) ይለዋል፡፡ ብዙዎች (ዐሣ ዐንበሪ) በማለት ዛሬ ላይ በተለምዶ የምናውቀው ትልቅ ዐሣ ዮናስን እንደዋጠው ይናገራሉ፡፡ ግሪኩ (ኬቶስ) ይለዋል፤ ትርጉሙም ታላቅ የባሕር እንስሳ ማለት ነው፡፡ ሊቁ ኒቆዲሞስ ገዳማዊ st. Nicodemus the hagiorite ስለዚህ (ኬቶስ) የተባለ የባህር እንስሳ ሲናገር እንዲህ ይላል፡-
ዕውቀትን እና መማርን ለሚወዱ ሰዎች ስለ ኬቶስ እንዲህ ብለን እንናገራለን፡፡ ቴዎክለስ እንዳለው ከሆነ ኬቶስ ከአስር መርከብ የበለጠ ነው፡፡ አሊያንስ እንደተናገረው ደግሞ ከዝሆን ዐምስት ጊዜ ይበልጣል፡፡ ኤራቶስቴንስ ሲናገር ደግሞ ሀምሳ ኪውቢት (23 ሜትር) በላይ ርዝማኔ አለው ይለናል፡፡ --- እነዚህን ጥንታዊ ሰዎች በመከተል ታላላቅ አባቶች ስለ ኬቶስ ግዙፍነት ይናገራሉ፡፡ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ኤቶስ ሰውነቱ እንደ ትልቅ ተራራ ያለ እንደሆነ እና ደሴት እንደሚመስል ይነግረናል፡፡ (አክሲማሮስ ዘባስልዮስ ድርሳን ሰባት) ታላቁ አምብሮስ ደግሞ ሲናገር ኬቶስ ሲዋኝ ቀና ቢል ሰማይን እንደሚነካ ሁሉ ግዙፍ እንደሆነ እና ትልቅነቱ እንደ ደሴት ወይም እንደ ተራራ እንደሚመስል ይናገራል፡፡ ኤውስጣቴዎስ ዘአንጾኪያ ደግሞ በአክሲማሮስ ሲነግረን አስፒዶኬሎን የታለው ኬቶስ እጅግ ግዙፍ ከመሆኑ የተነሣ ሰዎች ሲያዩት ደሴት እንደሚመስል ተናግሯል፡፡
ሐዋርያትም ሰብአ ነነዌ የተነሣህያን አብነት ናቸውና ሥርዓቱም ጾሙም አይቀር ብለው ሠርተውታል፡፡ እኛም በጾምና በጸሎት ከፈጣሪያችን ምህረትና በረከት ለማግኘት ስንል እንጾመዋለን፡፡ በተጨማሪም ይህ ጾም ለዐብይ ጾም መዘጋጃ በመሆን ያገለግላል፡፡
ጾሙ ከመግባቱ አስቀድሞ ኦርቶዶክሳውያን ሁላችን ንስሓ እንግባ።
ከዚህ ንስሓ ጋር የታወጀውን የየነነዌ ጾም ጠዋት በኪዳንና ከሰዓት በቅዳሴ ማታ ደግሞ በጸሎተ ምሕላ በየአጥቢያችን እየተገኘን አምላካችንን እንማጸነው።
መልካም ጾም ይሁንልን 🙏🤍
💚 💛 ❤️
@Ethiopian_Ortodoks