ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


🥰 እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሄርን ያመስግነው።
መዝ. ፻፶ ፡ ፮
❝በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማነው?
1.ጴጥ 3፡13

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций




✝️✨ ጾመ ነነዌ ✨✝️

ነነዌ የአሦር ጥንታዊ ከተማ ነበረ። ፍርስራሹ በጤግሮስ ወንዝ ምሥራቅ ዳርቻ በሞሱል ዙሪያ አሁን አለ። ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትሆን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ የምትጀመረው ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አትለቅም ቀኑ ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር 17 ድረስ ነው ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ እስከ የካቲት 24 ቀን ይረዝማል፡፡

በእነዚህ 35 ቀናት ውስጥ ስትመላለስ ከፍ ዝቅ ስትል ትኖራለች ከተጠቀሱት ዕለታት አባቶች እንደ ደነገጉት አትወርድም አትወጣም በዚህ ዓመትም የካቲት 03 ቀን ትጀመራለች፡፡ አጭርና የሦስት ቀን ጾም ብትሆንም እንኳ እጅግ ብዙ ጥቅምን የምታስገኝ ጾም ናት፡፡ ይህም "በመባጃ ሐመር ከፍና ዝቅ ስለሚል ቊጥሩ ከአጽዋማት ሐዋርያት ነው፡፡ አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል፡፡" ታዲያ ነነዌ ማን ናት? ነነዌ በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ ናምሩድ በተባለው ሰው ተመሠረተች፡፡ ለአሰራውያን መናገሻ ከተማ ነበረች፡፡ ሰፊና ውብ ከተማ ሆና የተገነባች ናት፡፡ [ዘፍ. 10:1] አስር ከእስራኤላውያን ጋር ጠላት ሆነው በተቀናቃኝነት የኖሩ መንግሥታት ናቸው፡፡ ዮናስ የተላከው ተቀናቃኝ ወደ ሆኑት ሕዝቦች ነው፡፡ ከተማዋ ውብና ብዙ ሕንፃዎች ነበሩባት የከተማዋ ቅጽር ርዝመት 12 ኪ.ሜ እንደነበር በውስጧ ብዙ ሕንፃዎች ተሠርተውባት ነበር፡፡ የባቢሎን መንግሥት ከክርስቶስ ልደት በፊት ከተማዋን አፈረሳት፡፡ [ዮና.4.1]
 
ሕንፃዎቿን የሠራቸው ሰናክሮም ሲሆን በስተመጨረሻ በ621 ዓ.ዓ የባቢሎን መንግሥት አፍርሷታል፡፡ ነነዌ ዛሬ የኢራቅ ከተማ ምሱል ናት በኩሽ ልጅ ናምሩድ በ1800 ዓ.ዓ ተቆረቆረች፡፡ ሽታር ወይም አስታሮትን ያመልኩ ነበር በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ገጥሟታል፡፡

ታዲያ ለነነዌ ሰዎች የተላከው ዮናስ ከአባቱ አማቴ እና ከእናቱ ሰና እንደተወለደ ታሪኩ ይነግረናል፡፡ ዮናስ ኤልሳዕ ያዳነላት የሰራጵታዎ ሴት ልጅ ነው የሚሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን ይነግሩናል፡፡ ነገር ግን ስለ ነቢዩ ዮናስ ጥልቀት ያለው ታሪክና መረጃ በስፋት አልተገለጸም፡፡ የስሙ ትርጉምም ቢሆን በእብራይስጥ ቋንቋ ርግብ የሚለው ትርጉም እንደሚገልጸው መተርጉማኑ ይገልጻሉ፡፡

ከእግዚአብሔር ዘንድ ለዮናስ የመጣው መልእክት "ክፋቷ በእኔ ፊት ወጥቷልና ወደ ታላቂቷ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ፣ በእርሷ ላይ ስበክ፡፡" [ዮና. 1.1] የሚል ነበር፡፡ ዮናስ ግን ጥሪውን መቀበል ባለመፈለጉ ኮበለለ፡፡ ከእግዚአብሔር መኮብለል አያዋጣምና ነብዩ ዮናስ በትልቅ አሣ እንዲዋጥ ተደረገ፡፡ በዚህ ውስጥ ዮናስ የትንቢት ቃሉን ለነነዌ ሕዝብ ማድረስ እንዳለበት ተረዳ፤ እግዚአብሔር ለኹለተኛ ጊዜ የነገረውን ድምጽም ሰምቶ ወደ ነነዌ ሄደ፡፡

በወቅቱ ነነዌ እጅግ ታላቅ የሆነች ከተማ ነበረች፡፡ በአርኪዮሎጂ ግኝት እንደተረጋገጠውም ከተማዋ ነቢዪ ዮናስ እንዳለው የሦስት ቀን መንገድ ያህል እጅግ ታላቅ ከተማ (ዮና.3.3) ነበረች፡፡ በአሁኑ ወቅት እንዳሉ ከተማዎች ሁሉ ሕዝብ የበዛበት ነበረች፡፡ ከመቶ ሃያ ሺህ በላይ ሕዝብ ይኖርበት እንደነበረም በዚያው በነቢዩ ዮናስ መጽሐፍ ላይ ተጠቀወሶ እናነባለን፡፡ [ዮና.4.1] ሆኖም ግን በዚህ ሁሉ ውስጥ እግዚአብሔርን እጅግ የሚያሳዝን ኀጢያት ይሠራ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ነብዩ ዮናስ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ነነዌ ሕዝቦች ይዞ ሄደ፡፡ ነነዌ እንደምትገለበጥም ተነገራቸው፡፡ 

በዚህ ታሪክ ውስጥ ትልቁን ትምህርት የምናገኘው እዚህ ጋር ነው፡፡ እግዚአብሔር የንስሐ ጥሪን ለኁሉም ያደርጋል፡፡ ከየሰው በኩል የሚሰጠው ምላሽ ግን የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ የነነዌ ንጉስ ከተማይቱ እንደምትጠፋ በሰማ ጊዜ "ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሱንም አወለቀ፤ ማቅም ለብሶ በዐመድ ላይ ተቀመጠ፡፡" [ዮና.3.6] ከዚህም በኋላ በነነዌ ሕዝብ ዘንድ ጾም እንዲታወጅ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- "ማንም ሰው ወይም እንስሳ፣ ከብትም መንጋም ሆነ የበግ መንጋ፤ ምንም ነገር አይቅመስ፤ አይብላ፤ ውሃም አይጠጣ፡፡ ነገር ግን ሰውም እንስሳም ማቅ ይልበስ፤ ኁሉም አጥብቆ ወደ እግዚአብሔር ይጩህ ሰዎችም ኁሉ ክፉ መንገዳቸውንና የግፍ ሥራቸውን ይተው፡፡ እና እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ራርቶ ከጽኑ ቁጣው ይመለስም እንደሆነ ማን ያውቃል" [ዮና. 3:7-9] በዚህም ጥሪ ምክንያት ሕዝቡ በጾም ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ተመለሰ፡፡ 

እግዚአብሔርም ለዚህ የሰጠው ምላሽ እንዲህ ነው፡- "እግዚአብሔርም ምን እንዳደረጉና ከክፉ መንገዳቸውም እንዴት እንደ ተመለሱ ባየ ጊዜ ራራላቸው፤ በእነርሱም ላይ ሊያመጣ ያሰበውን ጥፋት አላደረገም፡፡" [ዮና. 3:10]

ነነዌና አንዳንድ ነገሮች
ሀ. በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የዚህ ጾም ስም "የዮናስ ጾም" ይባላል፡፡ ሆኖም ግን ቀደምት መዛግብት ላይ የሠፈሩ መረጃዎች (የነነዌ ጾም) በሚለው ይሄዳሉ፡፡ እዚህ ጋር የምንዘክረው የነነዌ ሰዎች የጾሙትን ጾም ብቻ ሳይሆን ነብዩ ለሦስት ቀን በአሣው ሆድ ውስጥ መቆየቱን እናሳስባለን፡፡

ለ. የዚህን ጾም ታሪክ ወደ ኋላ ይዘን ስንሄድ የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እናገኛለን፡፡ ይህ ጾም በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲጾም የነበረ ነው፡፡ በዚህም ጾም ምክንያት ብዙዎች ከአደጋ ለመዳን ችለዋል፡፡   
 
ሐ. ለመሆኑ ነብዩ ዮናስን የዋጠው የባሕር እንስሳ ምንድር ነው; ግእዙ (ዐንበሪ) ይለዋል፡፡ ብዙዎች (ዐሣ ዐንበሪ) በማለት ዛሬ ላይ በተለምዶ የምናውቀው ትልቅ ዐሣ ዮናስን እንደዋጠው ይናገራሉ፡፡ ግሪኩ (ኬቶስ) ይለዋል፤ ትርጉሙም ታላቅ የባሕር እንስሳ ማለት ነው፡፡ ሊቁ ኒቆዲሞስ ገዳማዊ st. Nicodemus the hagiorite ስለዚህ (ኬቶስ) የተባለ የባህር እንስሳ ሲናገር እንዲህ ይላል፡-
ዕውቀትን እና መማርን ለሚወዱ ሰዎች ስለ ኬቶስ እንዲህ ብለን እንናገራለን፡፡ ቴዎክለስ እንዳለው ከሆነ ኬቶስ ከአስር መርከብ የበለጠ ነው፡፡ አሊያንስ እንደተናገረው ደግሞ ከዝሆን ዐምስት ጊዜ ይበልጣል፡፡ ኤራቶስቴንስ ሲናገር ደግሞ ሀምሳ ኪውቢት (23 ሜትር) በላይ ርዝማኔ አለው ይለናል፡፡ --- እነዚህን ጥንታዊ ሰዎች በመከተል ታላላቅ አባቶች ስለ ኬቶስ ግዙፍነት ይናገራሉ፡፡ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ኤቶስ ሰውነቱ እንደ ትልቅ ተራራ ያለ እንደሆነ እና ደሴት እንደሚመስል ይነግረናል፡፡ (አክሲማሮስ ዘባስልዮስ ድርሳን ሰባት) ታላቁ አምብሮስ ደግሞ ሲናገር ኬቶስ ሲዋኝ ቀና ቢል ሰማይን እንደሚነካ ሁሉ ግዙፍ እንደሆነ እና ትልቅነቱ እንደ ደሴት ወይም እንደ ተራራ እንደሚመስል ይናገራል፡፡ ኤውስጣቴዎስ ዘአንጾኪያ ደግሞ በአክሲማሮስ ሲነግረን አስፒዶኬሎን የታለው ኬቶስ እጅግ ግዙፍ ከመሆኑ የተነሣ ሰዎች ሲያዩት ደሴት እንደሚመስል ተናግሯል፡፡

ሐዋርያትም ሰብአ ነነዌ የተነሣህያን አብነት ናቸውና ሥርዓቱም ጾሙም አይቀር ብለው ሠርተውታል፡፡ እኛም በጾምና በጸሎት ከፈጣሪያችን ምህረትና በረከት ለማግኘት ስንል እንጾመዋለን፡፡ በተጨማሪም ይህ ጾም ለዐብይ ጾም መዘጋጃ በመሆን ያገለግላል፡፡

ጾሙ ከመግባቱ አስቀድሞ ኦርቶዶክሳውያን ሁላችን ንስሓ እንግባ።
ከዚህ ንስሓ ጋር የታወጀውን የየነነዌ ጾም ጠዋት በኪዳንና ከሰዓት በቅዳሴ ማታ ደግሞ በጸሎተ ምሕላ በየአጥቢያችን እየተገኘን አምላካችንን እንማጸነው።

መልካም ጾም ይሁንልን 🙏🤍
💚 💛 ❤️
@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks


ጾመ ነነዌ ሰኞ የካቲት ፫ ይገባል።

3.7k 0 35 21 143

*አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሷል፤ ያበሰብሷልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ

@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks


ትልቁ መሳሪያችን ፀሎት ነው
እስካሁን ያላነው በአባቶች ፀሎት ልመና፣ በእናቱ በድንግል ማርያም፣ በፃድቃን መላእክት አማላጅነት ነውና
አሁንም የአባቶች ፀሎት ይጠብቀን🙏
የድንግል ማርያም፣ ፃድቃን መላእክት አማላጅነት የልጇ የወዳጇ ይቅር ባይነት አይለየን🙏

3.6k 0 7 16 168

🥰 ደስ የሚል መዝሙር
♡ ናና አማኑኤል ♡


ናና አማኑኤል ና መድኃኒቴ
ጽድቅህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/
ናና አማኑኤል ና መድኀኒቴ
ፍቅርህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ /2/

የምሕረት አባት     አማኑኤል
የቸርነት ጌታ           ''
ፊትህ የተመላ         ''
ሁሌ በይቅርታ         ''
ካለው ፍቅር በላይ    ''
አባት ለአንድ ልጁ     ''
አምላክ ይወደናል       ''
አይጥለንም ከእጁ      ''

መድኃኒቴ ልበል        አማኑኤል
ድኛለው በሞትህ         ''
ቁስሌ ተፈውሷል         ''
በቁስልህ በሞትህ        ''
ስሸጥህ አቀፍከኝ         ''
ስወጋህ አይኔ በራ         ''
በፍቅርህ አወጣኽኝ       ''
ከዚያ ከመከራ               ''

አንተ ከኔ ጋር ነህ          አማኑኤል
አዎ ከኔ ጋራ                    ''
ድል አርገህልኛል             ''
የጭንቄን ተራራ               ''
በጉባኤ መሀል                ''
አፌ አንተን አወጀ             ''
የከበረ ደምህ                 ''
ነፍሴን ስለዋጀ                ''

የድንግሏ ፍሬ                አማኑኤል
የበላቴናዋ                       ''
የቤቴ ምሰሶ                     ''
የነፍሴ ቤዛዋ                    ''
መሠረቴ አንተ ነህ              ''
ያሳደገኝ እጅህ                  ''
አተወኝም አንተ                  ''
ስለሆንኩኝ ልጅህ               ''

ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ
✝ሼር
👉
@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks

4k 0 80 5 78

“አካሔድህን አስተካክል”

“ከአፍቃሪያችን ክርስቶስ
ያገኘነው ስጦታ እንዲህ ነው ተብሎ በቃላት መግለጥ የሚቻል አይደለም፡፡ እንዴት ያልን እንደሆነ እኛ በኀጢአት እየተንፏቀቅን I'mባለንበት ወራት እርሱ በምሕረቱ ጐብኝቶናልና፡፡ ኀጢአት ሸክም በሆነችብን ጊዜ እርሱ በእኛ ቦታ ተገብቶ ተሸክሞልናልና፡፡ በዚህ የማይለካ ፍቅሩ ከዲያብሎስ አገዛዝ ወደ መንግሥቱ አፈለሰን /ቈላ.1፡14/፡፡ እኛው ራሳችን ርቀን እርሱ ራሱ አቀረበን፡፡ እኛ ራሳችን በድለን እርሱ ካሠልን፡፡ ተወዳጆች ሆይ! ይህን ሁልጊዜ ከልቡናችን አናውጣ፡፡ የተሠጠንን ነጻ ሥጦታ አንዘንጋ፡፡ከምን እንደወጣን አንርሳ፡፡

ሰው ሆይ! የተጠራኸው ወደ ዘለዓለም ሕይወት ነው፡፡ የተጋበዝከው ወደ ልጁ መንግሥት ነው፡፡ ታድያ አንተእዚህ ስለምን ታንጠራራለህ? ስለምን እዚህ ትቀመጣለህ? ስለምን እዚህ
ትንፏቀቃለህ? ስለ ሥጋህ ድሎት ብዙ ዋጋን ትከፍላለህ፡፡ ታድያ ስለ ነፍስህስ ትንሽ አይገድህምን? ወደ ሕይወት ተጠርተህ ሳለ ስለምን ወደ ሞት ትሮጣለህ? ቢያስፈለግ ይህ
ያገኘኸው ስጦታ ላለማቆሸሽ ብዙ መሥዋዕትነትን መክፈል በተገባኽ ነበር፡፡ ብዙ ሰይፍን መታገሥ በተገባህ ነበር፡፡ ወደ እሳት እንኳ ብትጣል ስለ ድኅነተ ነፍስህ መቋቋም ይገባህ ነበር፡፡
ወዳጄ ሆይ! እስኪ ንገረኝ! የመንግሥተ ሰማያት ዜጋ ለመሆን ተጠርተህ ሳለ ራስህን የዚህ ዓለም ዜጋ ማድረግህ ስለምንድነው? እንደምን ያለ ስንፍና እንደያዘህስ ታስተውላለህን? ይህን
ዓለም የመውደደህ ምስጢር ምቾትን መሻትህ ያሳያል፡፡ በዚህ ዓለም በምቾት መኖርን የሚሻሰው ደግሞ ክርስቲያን መሆን፣ ክርስቲያን ተብሎ መጠራት፣ ክርስቶስን መስሎ መመላለስ
ምቾት ሳይሆን እስር ቤት መስሎ ይታየዋል፡፡ ሁላችንም ወደዚሁ ቈጥ ካስገባን ሰነባብተናል፡፡ ከዚህች ዓለም ጋር የተወዳጀ ግን ምንም ክርስቲያን ቢባልም ምንም በአርባና በሰማንያ ቀኑ የሥላሴን ልጅነት ቢያገኝም ክርስቲያን ክርስቲያን መሽተቱ እየጠፋ ይሔዳል፡፡በዚኽ ዓለም ወጥመድ ተቀፍድዶ ይያዛል፡፡

ወዳጄ ሆይ! ይህን አድምጥና ፍርሐትና ረዓድ ይያዝህ!!! ምንም በቤተ መንግሥት
ብትኖርም፣ ምንም በተሽቆጠቆጠ መኖርያ ቤት ብትኖርም እንደተመቸህ አድርገህ
አትንገረኝ፡፡ አንተ የምትኖርበት ኑሮ ለእኔ ወኅኒ ቤት ነው፤ ያውም ሊፈርስ የተቃረበ ቤት!!!
ይኽ ቤትህ ክረምት ሲመጣ ይፈርሳል፡፡ ክረምት (የመጨረሻይቱ ቀን) ስትመጣ ቤትህ ይፈርሳል፡፡ ክረምት ስላልኩህ ደግሞ “ለሁሉም ሰው ክረምት ከሆነበት እኔ ከማን እለያለሁ” ብለህ አታስብ፤ ይህቺ ቀን ለሁሉም ክረምት አትሆንምና፡፡ ዳግመኛም እግዚአብሔር ሌሊትና
ቀን ብሎ ጠርቷታልና፡፡ ሌሊት የምትሆንባቸው ለኀጥአን ነው፤ ቀን የምትሆንላቸው ደግሞ ለጻድቃን ነው፡፡ እኔም ክረምት ብዬ መናገሬ ከዚህ አንጻር ነው፡፡ ሁላችንም ክረምት ሲመጣ
መብረር እንችል ዘንድ በበጋው ላይ ካላደግን የገዛ እናቶቻችን እንኳ ቢሆኑ ትተዉን ይሔዳሉ እንጂ በዚያ ሰዓት እኛን መሸከም (ማዳን) አይቻላቸውም፡፡ የገዛ እናቶቻችን እንኳ በረሃብ እንሞት ዘንድ ትተዉን ይሔዳሉ፡፡ ቈጡ (ቤቱ) በላያችን ላይ ሲፈርስ እኛን መታደግ አይቻላቸውም ፡፡ እግዚአብሔር ቤቱን ሲያፈርሰው፣ አሮጌው እንደ አዲስ ሲያደርገው፣ እያንዳንዱ እንዳልነበረ ሲሆን እኛን መርዳት የሚችል አንድ ስንኳ አይገኝም፡፡ የዚያን ጊዜ ጌታን በአየር ላይ መገናኘት የማይችሉቱ፣ የመንፈስ ክንፍ ተሰጥቶአቸው መብረር የማይችሉቱ ቤቱ በላያቸው ላይ ይፈርስባቸዋል፡፡ ስቃይ የስቃይም ስቃይ ይሆንባቸዋል፡፡ ስቃዩ
የስቃይ ስቃይ ነው ማለቴ ከ እስከ የሚባል ስለሌለው ነው፤ ለዘለዓለም ስቃይ ስለሆነ ነው፡፡ ክረምት ብዬ መጥራቴ ስለዚሁ ነው፤ ኧረ እንደውም ከክረምት የባሰ ነው፡፡ እንዴት ያልከኝ እንደሆነ በዚሁ፡ክረምት ላይ የሚዘንበው ውኃ አይደለምና፤ እሳት እንጂ፡፡ በዚሁ ክረምት ዙርያህ ጨለማ የሚሆነው ከደመና ብዛት የተነሣ አይደለምና፤ ጽኑ ጨለማ እንጂ፡፡ የብርሃን
ጭላንጭል የሌለው ጨለማ እንጂ፡፡ እዚህ የሚገቡት ሰዎች ተድላ መንግሥትን ማየት
አይቻላቸውም፤ ሰማያትን ማየት አይቻላቸውም፡፡ ከመቃብር ውስጥ የባሰ ጨለማ ይውጣቸዋል እንጂ፡፡
ወዳጄ ሆይ! አሁንስ አትርድምን? ወዴት እየሔድክ እንደሆነ አታስተውልምን? ፊትህንስ ወደ ልጁ መንግሥት አታደርግምን?”… አካሔድህን አስተካክል…

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ )

@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks



4.6k 0 37 5 118

በጨነቃችሁ በችግራችሁ ጊዜ ሁሉ ቅዱስ አማኑኤል አለሁ ይበላችሁ።

🥰🙏🥰

4.5k 0 6 30 216

❤️‍🩹" የተሻለ ነገር አስብህልኝ ነው መከራ የበዛው " በሚለው ዝማሬ የምትታወቀው ዘማሪት መስከረም ወልዴ ስርዓተ ጋብቻ ፈጸመች 🥰

በዝማሬ አገልግሎት ቅድስት ቤተክርስቲያንን እያገለገለች የምትገኘው እህታችን ዘማሪት መስከረም ወልዴ በስርዓተ ቁርባን በአገልግሎት አጋራችን ከሆነው ወንድማችን ጸጋአብ ኢያሳያስ ጋር በአርባ ምንጭ ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ገዳም ስርዓተ ጋብቻ ፈጽማለች።

የመንፈስ ቅዱስ ማኅተም ያለበት፣ የንጽህና መኝታ ፣ ፍሬው የተባረከ፣ በሁለት ገላ አንድነት የሚገለጥበት የተዋሕዶ ምልክት ወደ ሆነው ቅዱስ ጋብቻ ትደርሱ ዘንድ እንኳን ቅድስት ሥላሴ ረዳችሁ!!!

በእዚህ ቤት ድንግል ከእነ ልጇ ትግባበት!!!
እንደ ዶኪማስ ቤት ያኑራችሁ!
የአብርሐም እና የሣራ በረከት ይደርበት።
✤✞✤
@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks


" ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥
እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ
ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።” — ሮሜ 9፥5


መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ።
ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።

መልካሙን ሁሉ የምትሰሙበት ሌሊት ይሁንላችሁ🙏🥰✝

6.1k 0 25 13 164


6k 0 10 1 147

የነበረ ሲሆን አንድ ወንድ ልጅ መድኃኒነ እግዚእንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፡፡ ሶስቱ ሴቶች ልጆችም እምነ ጽዮን፣ ትቤ ጽዮንና ክርስቶስ ዘመዳ ይባላሉ፡፡ ሦስቱ እኅትማማቾችም ደጋጎቹን አባቶቻችንን ወለዱልን፡፡ እምነ ጽዮን የእነ ዜና ማርቆስን እናት ማርያም ዘመዳንና ወለደች፡፡ ትቤ ጽዮንም ሕፃን ሞዐን ወለደች፡፡ ክርስቶስ ዘመዳ ደግሞ ታላቁን አኖሬዎስን ወለደች፡፡ የፈጠጋሩ ገዥ መድኃኒነ እግዚእ ደግሞ የተክለ ሃይማኖትን እናት እግዚእ ኀረያን ወይም በሌላ ስሟ ሣራን ወለደ፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከልጅነታቸው ጀምሮ በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በ15 እና በ22 ዓመታቸው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ከአቡነ ቄርሎስ (ጌርሎስ) ዲቁናንና ቅስናን ተቀብለዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ቅድስት ቤተክርስቲያንን በወጣትነት ዕድሜያቸው ያገለግሉ እንደነበር በዚህ ይታወቀል፡፡
ከዕለታት በአንዱ ቀን አባታችን ከጓደኞቻቸው ጋር ለአደን ወደ ዱር ሄደው ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ታያቸው፡፡ ቅዱስ አባታችንም ‹‹እንደዚህ ባለ ገናንነት የማይህ ጌታዬ ማነህ?›› ባሉት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ዘወትር የምጠብቅህ ካንተ የማልለይ እናትህንና አባትህንም ስላንተ ከውኃ ስጥመትና ከምርኮ ያዳንኳቸው እኔ ሚካኤል ነኝ፡፡ ከእንግዲህ አውሬ አዳኝ አትሁን፤ ሰውን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ሰውን በትምህርት የምታድን ሁን እንጂ፡፡ እነሆ እግዚአብሔር ጽኑዕ ሥልጣን ሰጥቶሃልና፤ ሙት ታስነሣለህ፤ ድውያንን ትፈውሳለህ፤ አጋንንትም አንተን በመፍራት ይሸሻሉ፡፡ ስምህ ፍሥሐ ጽዮን አይሁን፤ ተክለ ሃይማኖት ይሁን እንጂ፡፡ ትርጓሜውም ተክለ አብ፥ ተክለ ወልድ፥ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው›› አላቸው፡፡
ቅዱስ ሚካኤል ይህን ሲነግራቸው ጌታችን በሥጋ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እንደነበር ሆኖ መልከ መልካም ጎልማሳ መስሎ ታያቸው፡፡ ጌታችንም ‹‹ወዳጄ እንዴት ሰነበትክ? ቸር አለህን?›› አላቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ‹‹ጌታዬ ሆይ አንተ ማነህ?›› ብለው ሲጠይቁት ጌታችንም ‹‹እኔ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ነኝ፤ በናትህ ማኅፀን ፈጥሬህ ያከበርኩህ እኔ ነኝ፡፡ በተወለድክ በሦስተኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለህ ታመሰግነኝ ዘንድ የምስጋና ሀብት ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ፡፡ በርሃብ ዘመን በቤት የሚያሻው ምግብ ሁሉ ቅቤው፣ የስንዴው ዱቄት በእናት በአባትህ ቤት ይመላ ዘንድ በእጅህ ሀብተ በረከት ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ፡፡ ያንን ሰው አንተን በተጣላ ጊዜ በነፋስ አውታር የሰቀለኩት በመዓት ጨንገር የገረፍኩት እኔ ነኝ፡፡ ውኃ ጠምቶህ በለመንከኝ ጊዜ ከደረቅ መሬት የጣፈጠ ውኃ ያመነጨሁልህ እኔ ነኝ፡፡ ከልጅነትህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ተአምራት እያደረግሁ በአንተ እጅ የታመሙትን ያዳንኳቸው እኔ ነኝ፡፡ ወደፊትም አደርግልሃለሁ›› አላቸው፡፡ ይህንን ብሎ በእጆቹ ባረካቸውና ‹‹ንሣእ መንፈስ ቅዱስ›› ብሎ የሹመትን ሀብት አሳደረባቸው፡፡ ዳግመኛም ‹‹በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሁን፤ በምድርም የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሁን፤ አንተን የሰማ እኔን መስማቱ ነው፤ የላከኝ አባቴንም መስማቱ ነው፡፡ አንተን እንቢ ያለ እኔን እንቢ ማለቱ ነው፡፡ የላከኝ አባቴንም እንቢ ማለቱ ነው፡፡ ይህን ሥልጣን ቀድሞ ለሐዋርያት ሰጥቻቸው ነበር፡፡ ከሐዋርያትም ሹመትን የተቀበለ ጳጳሱ ትሾምና ትሽር፣ ትተክልና ትነቅል ዘንድ ሥልጣንን ሰጠህ፡፡ ይህንንም ያደረኩልህ የጳጳሱን ቃል በመናቅ አይደለም፡፡ የፍቅሬን ጽናት ባንተ እገልጽ ዘንድ ነው እንጂ፡፡ ሐዋርያት ወዳልደረሱበት ሕዝብ በመምህርነት እልክህ ዘንድ በሚካኤል ቃል አዲስ ስም አወጣሁልህ፡፡ አንተም በማናቸውም ሥራ ከእነርሱ አታንስም፣ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጌሃለሁና፡፡ ሰውን ሁሉ በእኔ ስም እያስተማርክ ታሳምን ዘንድ፣ ሚካኤልም ባሰብከው ሥራ ሁሉ ረዳት ይሁንህ፣ ሁል ጊዜ ካንተ አይለይም፤ በምትሄድበትም ጎዳና ሁሉ እርሱ መሪ ይሁንህ፤ እኔም ባለ ዘመንህ ሁሉ አልለይህም›› ካላቸው በኋላ ሰላምታ ሰጥቷቸው ዐረገ፡፡
ብፁዕ አባታችንም እጅ ነሥተው ‹‹ለእኔ ለኀጥኡ የማይገባኝ ሲሆን ይህን ሁሉ ጸጋ የጠኸኝ ስምህ በሰማይ በምድር የተመሰገነ ይሁን›› አሉ፡፡ ከዚያች ቀን ጀምሮ ሀብተ ኃይልን የተመሉ ሆኑ፡፡ ወደቤታቸው ተመልሰው ያላቸውን ሀብት ንብረት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን፣ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጥተው ጨረሱ፡፡ ከዚያም ‹‹አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደተከፈተ ተውኩልህ›› ብለው ቤታቸውን እንደተከፈተ ትተው ወንጌልን ለማስተማር ወጡ፡፡ ጻድቁ አባታችን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ኃይማኖት ስለመለሱት በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ተብለዋል፡፡
አባታችን ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው በመቆም ያለምግብና ያለውኃ በትኅርምት ሌትና ቀን እንቅልፍ በማጣት እንደ ምሰሶ ጸንተው፤ በተመስጦ በትጋት ለሰው ዘር ሁሉ ድኅነትን ሲለምኑ ኖረዋል፡፡ ከሰባቱ ዓመታት ውስጥ ጥቂት ውኃ የቀመሱት በአራተኛው ዓመት ብቻ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ጌታችን ተገልጦላቸው በሰው አእምሮ ሊታሰብና ሊለካ የማይችል ትልቅና ልዩ የመንግሥት አዳራሽ ከሰጣቸው በኋላ የመለኮትን ነገር የሚናገር የእሳት አንደበት ያላቸው የመንግሥት ልብስ አለበሳቸው፡፡ በመስቀል ምልክት የተጌጡት ሰባት የሕይወት አክሊላትን አቀዳጅቷቸዋል፡፡ ይኸውም ‹‹ስለ ቀናች ሃይማኖትህ፣ ሃይማኖትን ለማስተማር መላዋን ኢትዮጵያን ስለመዞርህ፣ ከአረማውያን ሕዝብ ጋር በሃይማኖት ስትታገል ደምህን ስለማፍሰስህ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ወርደህ ልዩ ልዩ የቅዱሳን ቦታዎች ስለመሳለምህ፣ በሰባት ዓመታት ቊመት የአንዱ አገዳ እግርህ ስለመሰበሩ፣ ስለብዙ ጾም ጸሎት ስግደትህ፣ ስለልብህ ንጽሕናና ቅድስና›› በማለት የሕይወት አክሊላትን ካቀዳጃቸው በኋላ ዝክራቸውን በማዘከር መታሰቢያቸውን የሚያደርጉ ሁሉ በዚህ ዓለምም ሆነ በወዲያኛው ዓለም ፍጹም ዋጋና ፍጹም ክብር እንደሚሰጣቸው ጌታችን ታላቅ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ሥጋቸውም ወዴት ይቀበር ዘንድ እንዳላቸው ሲነግራቸው ‹‹እስከ 57 ዓመት ሥጋህ ከዚህ ይቀበራል፤ ከ57 ዓመት በኋላ ግን ይህች ዋሻ ትናዳላች፡ በዚህም ገዳም አደባባይ በስምህ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ልጆችህ ሠርተው ሥጋህን አፍልሰው በውስጡ ያኖራሉ›› አላቸው፡፡ በመጨረሻም አባታችን ለ10 ቀናት ያህል በተስቦ ሕመም ቆይተው ፈጣሪያቸው የገባላቸውን ቃል ኪዳን ለመነኰሳት መንፈሳውያን ልጆቻቸው ከነገሯቸው በኋላ ነሐሴ 24 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡
የቅዱስ አባታችን በዓላቶቻቸው እነዚህ ናቸው፡- መጋቢት 24 ቀን 1196 ዓ.ም ፅንሰታቸው፣ ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ልደታቸው፣ ኅዳር 24 ቀን ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር በሕይወተ ሥጋ እያሉ የሥላሴን መንበር ያጠኑበት ነው፡፡ ነሐሴ 24 ቀን 1296 ዓ.ም ዕረፍታቸው ነው፤ ግንቦት 12 ቀን 1353 ዓ.ም ፍልሰተ ዐፅማቸው ነው፡፡ ጥር 4 ቀን 1289 ዓ.ም ደግሞ በጸሎት ብዛት አንድ እግራቸው የተሰበረበት ነው ነገር ግን የዕረፍታቸውን ቀን ይዞ በዚሁ በጥር ወር በ24 ከመነኮሱበት በዓላቸው ጋር አብሮ ይከበራል፡፡
የቅዱስ አባታችን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!🙏🙏🙏


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ጥር 24-ሐዲስ ሐዋርያ ፀሐይ ዘኢትዮጵያ አቡነ ተክለሃይማኖት የመነኮሱበትና አንድ እግራቸው በጸሎት ብዛት የተሰበረበት ዕለት ነው፡፡

+ በዓቷን በማጽናት ለ22 ዓመታት ዘግታ የኖረችውና የላመ የጣፈጠ ቀምሳ የማታውቀው ቅድስት ማርያ ዕረፍቷ ነው፡፡
+ የሸዋው እጨጌ መርሐ ክርስቶስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
ቅድስት ማርያ፡- ይኽችም ቅድስት ከታላላቅ ወገኖች የሆነች የከበረች ተጋዳይ ናት፡፡ ወላጆቿ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ እነርሱም በልጃቸውን ማርያን በሃይማኖት በምግባር አሳደጓትና ዕድሜዋ ሲደርስ ሊያገቧት አሰቡ፡፡ ነገር ግን ቅድስር ማርያ አግታ በዓለም መኖርን አልወደደችምና እሺ አላለቻቸውም፡፡ ወላጆቿም በሞቱ ጊዜ የተውላትን ብዙ ወርቅና ንብረት ሁሉንም ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጥታ ከእስክንድርያ ውጭ ወዳሉ ገዳማት ሄዳ ወደ አንዱ ገባች፡፡
ወደ ገዳምም ገብታ ከመነኮሰች በኋላ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለች፡፡ ሁልጊዜ እስከማታ ድረስ በመጾም ሌሊቱንም ሁሉ እየጸለየች ለ12 ዓመታት ከቶ ምንም ሳትተኛ ተጋድሎዋን አበዛች፡፡ የክብር አስኬማን ከለበሰች በኋላም ከጥጥ ባዘቶ የተሠራ ልብስ ከላይዋ ላይ ጥላ ለበሰች፡፡ በዓቷም ለመዝጋት ወሰነች፡፡ ይህንንም ሀሳቧን ትፈቅድላት እንደሆነ ወደ እመ ምኔቷ ዘንድ በመሄድ መልካም ፈቃዷን ጠየቀቻት፡፡ እርሷም ፈቀደችላት፡፡ ከዚህም በኋላ ቅድስት ማርያ በዓቷን ዘጋች፡፡ የዕለት ጉርሷን የምትቀበልበት ትንሽ መስኮት ቀደደች፡፡ ቅዱስ ሥጋ ወደሙንም በዚያው ትቀበላለች፡፡ በዚያችም በዓቷ ውስጥ ለ22 ዓመታት ዘግታ ኖረች፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ ቁማ ትጸልያለች፣ በእንቅልፍም ጊዜ ጥቂት ታርፋለች፡፡ ሌሊቱንም ሁሉ ቁማ ታድራለች፡፡ በየሁለት ቀኑ በውኃ ብቻ የራሰ እንጀራ እየተመገበች ኖረች፡፡ ዓቢይ ጾምም በመጣ ጊዜ በየሦስት ቀኑ እየጾመች በውኃ የራሰ ሽምብራ ብቻ ትቀምስ ነበር፡፡
ጥር 11 ቀን የከበረ የጥምቀት በዓል በሆነ ጊዜ ከተባረከው ውኃ ያመጡላት ዘንድ ለምና አመጡላት፡፡ ቅዱስ ሥጋ ወደሙን ከተቀበለች በኋላ ከጥምቀቱ ውኃ ጠጣች፡፡ ከዚህም በኋላ የዕረፍቷ ጊዜ እንደደረሰ ዐውቃ እስከ ጥር 21 ቀን ቅዱስ ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ተኛች፡፡ እመ ምኔቷን አስጠራቻትና ስትመጣላት እጆቿንና እግሮቿን እየሳመች ‹‹ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታዬ ክርስቶስ ላደረሱኝ እግሮችሽ እገዛለሁ›› አለቻት፡፡ ደናግሉንም ሁሉ አስጠርታ ተሳለመቻቸውና ከ3 ቀን በኋላ ሁሉም ተመልሰው መጥተው እንዲጎበኟት ለመነቻቸው፡፡ ይኸውም በጥር 24 ቀን ነው፡፡ እነርሱም እንደለመነቻቸው በሦስተኛው ቀን ተመልሰው ቢመጡ ቅድስት ማርያን ዐርፋ አገኟት፡፡ በክብር ገንዘው ከደናግል አስክሬን ጋር አኖሯት፡፡ ረድኤት በረከቷ ይደርብን በጸሎቷ ይማረን!
+ + +
እጨጌ መርሐ ክርስቶስ፡- ጻድቁ የገዳማት ሁሉ አባት እየተባሉም ይጠራሉ፡፡ ትውልዳቸው ሸዋ መራቤቴ ሜዳ ሲሆን ለገዳማት ብዙ የደከሙ አባት ናቸው፡፡ በተለይም በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ገድል አላቸው፡፡ ይኸውም እንደ ነዳይ ሆነው ለምነው ያገኙትን ለጦም አዳሪዎች በመመጽወት ይታወቃሉ፡፡ ከባለ ሀብቶች ለምነው ያገኙትን ለድሆች ይመጸውቱትና በቀረው ቤተ ክርስቲያን ይሠሩበታል፡፡ አስደናቂ ገድላቸውና ዐፅማቸው በደብረ ሊባኖስ ይገኛል፡፡ በትግራይም ትልቅ ገዳም አላቸው፡፡ ዕረፍታቸው ጥር 24 ቀን ሲሆን ሕዝቡ ግን የሚያከብረው በዓለ ልደታቸውን ነው፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ፡- ተክለ ሃይማኖት ማለት ‹‹የሃይማኖት ተክል፣ ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ›› ማለት ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ማለትም ‹‹አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነውታል፡፡ ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍሥሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ይኸውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ የወላጆቻቸው የቀድሞ ስማቸው ዘርዐ ዮሐንስና ሣራ ይባል ነበር፡፡
ቅዱሳን አባቶቻችን እነ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና እነ አቡነ ዜና ማርቆስ ሌሎቹም እነ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፣ አቡነ ሕፃን ሞዐ፣ አቡነ አኖሪዮስ(ትልቁ)፣ አቡነ ገላውዲዮስ፣ አቡነ ማትያስ ዘፈጠጋርና አቡነ ቀውስጦስ ዘመሐግል የትውልዳቸው መሠረት ኢያሱ ለሌዋውያን ክፍል ትሆን ዘንድ ከለያት ከኢየሩሳሌም ነው፡፡ ስማቸውን የጠቀስኳቸው እነዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን የወንድማማቾች ልጆች ሲሆኑ ከአዳም ጀምሮ 61ኛ ትውልድ ናቸው፡፡ ይኸውም እንዴት ነው ቢሉ ትውልዱ ከአዳም ጀምሮ በካህኑ አሮን በኩል የሆነውና የሌዋዊያን ሊቀ ካህን የነበረው የሳዶቅ ልጅ አዛርያስ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ከታቦተ ጽዮንና ከብዙ ሌዋዊያን ካህናት ጋር ሊቀ ካህን ሆኖ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ አክሱም ተቀምጦ ኖረ፡፡ የኦሪትንም ሕግ እየዞረ ለኢትዮጵያ ሰዎች አስተማረ፡፡ ትውልዱም በአብርሃ ወአጽብሓና በአባ ሰላማ ዘመን እስከነበረው እንበረም የሚባለው ጻድቅ ድረስ ደረሰ፡፡ የእንበረምም ትውልድ ደገኛው ሕይወት ብነ በጽዮን ድረስ ደረሰ፡፡ ሕይወት ብነ በጽዮንም የደማስቆ ምድር ከሚሏት ከወለቃ ሀገር የመኮንን ልጅ የሆነችውን ወለተ ሳውልን አግብቶ አበይድላን ወለደ፡፡ አበ ይድላም በንጉሡ ድልዓዥን ዘመነ መንግሥት ለ150 ካህናት አለቃ ሆኖ በወለቃ ሀገር የክርስቶስን የወንጌል ሕግ እያስተማረ ብዙዎችን አጠመቀ፡፡ እስከ ሸዋ ምድር ድረስ እያስተማረ መጥቶ በሸዋ ምድር ተቀመጠ፡፡ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳነጸ፡፡ እጅግ አስደናቂ ተአምራትንም ያደርግ ነበር፡፡ ‹‹በሸዋ ጽላልሽ ተቀምጦ ሲያስተምርም በአንዲት ቀን እስከ ሁለት መቶ ሺህ ሕዝብ ያጠምቅ ነበር›› በማለት ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ይመሰክርለታል፡፡
አበይድላ በመጨረሻ በፈቃደ እግዚአብሔር ከሸዋ ጽላልሽ ምድረ ዞረሬ ሚስት አግቶ ሀበነ እግዚእን ወለደ፤ ሀበነ እግዚእም በኩረ ጽዮንን ወለደ፤ በኩረ ጽዮንም ሕዝበ ቀድስን ወለደ፤ እርሱም ነገደ እግዚእ የተባለ ነው፡፡ ሕዝበ ቀድስም ብርሃነ መስቀልን ወለደ፤ እርሱም ዐቃቢነ እግዚእ የተባለ ነው፡፡ ብርሃነ መስቀልም ሕይወት ብነን ወለደ፤ እርሱም ሴትን ወለደ፡፡ ሴትም ወረደ ምሕረትን ወለደ፡፡ ወረደ ምሕረትም ዘካርያስን ወለደ፡፡ ዘካርያስም የእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት የሆኑ 6 ወንድማማች ልጆችን ወለደ፡፡ እነርሱም እንድርያስ፣ አርከሌድስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብ፣ ቀሲስ ዮሐንስና ቀሲስ ዮናስ ናቸው፡፡ እንድርያስም ሳሙኤል ዘወገግን ወለደ፤ አርከሌድስም ሕፃን ሞዐን ወለደ፤ ዘርዐ አብርሃምም ታላቁን አኖርዮስን ወለደ፤ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብም ተክለ ሃይማኖትን ወለደ፤ ቀሲስ ዮሐንስም ዜና ማርቆስን ወለደ፣ ቀሲስ ዮናስ ደግሞ የፈጠጋሩን ማትያስንና ገላውዲዮስን ወለዳቸው፡፡ ገላውዲዮስም የመሐግሉ ቀውስጦስን ወለደ፡፡ እነዚህ ደጋግ ቅዱሳን በእናታቸውም በኩል እንዲሁ በዝምድና የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ማቴዎስ የተባለው ደገኛ ክርስቲያን የሸዋ ገዥ


ኣንድ ብር ላይ ያለውን የሚስቀውን ልጅ ስመለከት ይገርመኛል፡፡
ኣንድ ላይ ነኝ ብሎ ኣላዘነም፡ የሆነ የተደበቀ ተስፋ ስላለው በተስፋ እና በደስታ ይኖራል ፡፡100 ብር ላይ ማክሮስኮፕ የሚመለከተው ሰውየ በጣም የተጨናነቀ ነው ፡፡100 ላይ ነኝ ብሎ ኣይዝናናም፣ ሌላ 100 ለመጨመር ይጨናነቃል ፡፡የዚህ ዓለም ሰወች ከመቶ ብር የተሳሉት ነን፡፡ በቃኝ የለም፣ ተመስገን የለም፣ በባንኩ በካዝናው ማጠራቀም ጥሎ መሄድ ፡፡መንፈሳዊ ኣባቶቻችን በኣንድ ብሩ ላይ ተስለዋል፡፡ ነዳያን፣የቆሎ ተማሪዎች እና የገዳማት እናቶቻችን እና ኣባቶቻችን ምንም የላቸው፡፡ ነገር ግን ደስተኛ ናቸው። ምክንያቱም ተስፋቸው
ኣምላካቸው ብቻ ስለሆነ ነው፡፡
ውጣውረዱ ወጭ ቀሪው  ኣያሳስባቸውም።

🌷ሰናይ ምሽት ቤተሰብ
🤲

4.9k 0 58 7 158

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
@Ethiopian_Ortodoks
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


ተወዳጆች

“ጌታ ሆይ! የሥጋ ጤና ስጠኝ፡፡ ሀብቴን ዕጥፍ አድርግልኝ፡፡ ጠላቴንም አርቅልኝ" እያሉ ብዙ ቃላትን የሚደግሙ አያሌ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ፍጹም ዕብደት ነው፡፡

ይህን ኹሉ ከእኛ ልናርቅና፡-

“አምላክ ሆይ፥ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ” እያለ ደጋግሞ እንደ ጸለየው እንደ ቀራጩ ሰውም ልንጸልይና ልንማጸን ብቻ ይገባናል (ሉቃ.18፡13)፡፡

ከዚህ በኋላ እንዴት አንተን መርዳት እንዳለበት እርሱ ያውቃል፡፡ “አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ፈልጉ፤ ይህም ኹሉ ይጨመርላችኋል” ብሎአልና (ማቴ.6፡33)።

ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ!

ተግተን ጥበብን እንከታተላት፡፡ እንደ ቀራጩም ደረታችንን እየደቃን ትሕትናን ገንዘብ እናድርግ፡፡ ያንጊዜም የለመንነውን ኹሉ እንቀበላለን፡፡

ቊጣንና ግልፍተኝነትን ተሞልተን የጸለይን እንደ ኾነ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላን በፊቱም አስጸያፊዎች እንኾናለን፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️


አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።
፤ አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማፅኛለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ።አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፤ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት።
፤ በምሕረትህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፥ እኔ ባሪያህ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቁአትን ሁሉ አጥፋቸው።
መዝሙረ ዳዊት 143 ቁ 8-12


🥀በቀኝ ያውለን ክፉውን ያርቅልን🤲

5.3k 0 32 10 155


5.1k 0 14 14 155
Показано 20 последних публикаций.