ፈረንሳይ የአፍሪካን ሰላም ለማስጠበቅ አቅምም ቅቡልነትም የላትም ~ የሴኔጋል ጠ/ሚር
የሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የቻድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለፈረንሳዩ ኘሬዝደንት ጠንከር ያለ የአፀፋ ምላሽ ሰጥተዋል።
የፈረንሳይ ኘሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ትላንት የቀድሞ ቀኝ ግዛቶቻቸው የነበሩ የምዕራብ አፍሪካ እና የሳህል አካባቢ ሃገራትን " አገራቱ በታጣቂዎች እጅ እንዳይወድቁ ታድገናቸዋል ለዚህም ምስጋና ሊያቀበርቡልን ይገባ የነበረ ቢሆንም ፥ እነርሱ ግን ምስጋና ማቅረቡን ረስተውታል " የሚል ንግግር ተናግረው ነበር።
የማክሮን ንግግርን ተከትሎ የሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር ኦስማን ሶኖኮ በፌስቡክ ገፃቸው በፃፉት አስተያየት " ፈረንሳይ የአፍሪካን ሰላም የማስጠበቅ አቅሙም ሆነ ቅቡልነት የሌላት አገር ናት " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ አላበቁም እንደውም አሉ " ፈረንሳይ አፍሪካን በማወክ እና በማተራመስ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተች አገር ናት " በማለት ጭምር ነቅፈዋታል።
ፈረንሳይ በሳህል አገራት እና በሊቢያ የፈፀመችው ተግባር ያስከተለው ጥፋት የቅርብ ማሳያ ነው ብለዋል።
የቻድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱረህማን ኮላማላህ ደግሞ የኢማኑኤል ማክሮን ንግግር የፈረንሳይ መሪዎች ለአፍሪካያን ዛሬም ክብር እንደሌላቸው የሚያሳይ ነው ብለውታል።
የቀድሞ የፈረንሳይ ቀኝ ተገዢ አገራት ለአመታት የዘለቀውን የፈረንሳይ ተፅዕኖ በቃን በማለት የነበራቸውን ግንኙነት እያቋረጡ ሲሆን የጦር ሰፈሮቿን እየዘጉ ሰራዊቷን እያስወጡ ይገኛሉ።
@Ewun_mereja