እውን መረጃ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Музыка


📌#ቀዳሚ_ምርጫዎ ➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ ➠ወቅታዊ መረጃዎች ➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች የምታገኙበት ቻናል
📌ጥቆማ ለመስጠት
👉 @ewun_mereja_bot
#እውነተኛ እና #ትኩስ #መረጃዎች
#እውንነት

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Музыка
Статистика
Фильтр публикаций


በሳዑዲ ዓረቢያና በኦማን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 470 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በዚህ ሳምንት ውስጥ 180 ወንዶች፣ 109 ሴቶች እና 13 ጨቅላ ህፃናት በድምሩ 302 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገር የተመለሱ ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 56 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

በተያያዘ ዜና በሳምንቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 157 ወንዶች 11 ሴቶች በድምሩ 168 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው የተመለሱ መሆኑ ታውቋል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ስራ እስካሁን 91 ሺህ 420 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ሆሊውድ በመሬት መንቀጥቀጥ መመታቷ ተሰማ

የኦስካር ሽልማት በተካሄደባት ትናንት ምሽት፣ የካቲት 23/ 2017 ዓ.ም ሆሊውድ በርዕደ መሬት ተመትታ ነበር ተባለ።
የርዕደ መሬቱ ማዕከል የነበረው የኦስካር ሽልማት ከተዘጋጀበት ሰሜናዊ ሆሊውድ፣ ዶልቢ ቲያትር አቅራቢያ መሆኑም ተገልጿል።

3.9 ሬክተር ስኬል የተመዘገበው ርዕደ መሬት ስላደረሰው ጉዳት የተገለጸ ነገር የለም።

ርዕደ መሬቱ የተከሰተው የኦስካር ሽልማትን ተከትሎ ታዋቂው ቫኒቲ ፌይር መጽሄት በሚያዘጋጀውና በርካታ ታዋቂ ሰዎች ድግስ ላይ ተሰባስበው በነበረበት ወቅት ነው።

ርዕደ መሬቱ የተከሰተበት ሰዓት በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ አራት ሰዓት ገደማ ነበር።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


"የፈጠራ ክስ ቀርቦብኛል"- ኤርትራ

ተመድ እና የአውሮፓ ህብረት የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር ገብተው ጥቃት እየፈፀሙ መሆናቸውን ተከትሎ ያቀረበባትን ክስ ኤርትራ አስተባበለች።


የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስቴር የማነ ገ/መስቀል በx ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አውሮፓ ህብረት እና ተመድ እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ተመሳሳይ እና የፈጠራ ክስ በኤርትራ ላይ መስርቷል ሲሉ ገልፀዋል።


በጄኔቫው ስብሰባ ላይ ኤርትራ በትግራይ ክልል ወረዳዎች ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየፈፀመች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ይሁንና ኤርትራ ክሱን የፈጠራ ክስ ነው ስትል አስተባብላለች።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከ9መቶ ጊዜ በላይ ጥሳለች ሲል የጋዛ መንግስት ከሰሰ፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ከጥር 19 ጀምሮ እስራኤል ስምምነቱን ከ9መቶ ጊዜ በላይ ጥሳለች ሲል አስታዉቋል፡፡

ስምምነቱ ተግባራዊ በሆነበት ወቅት እንኳን በተለያዩ የፍልስጤም ግዛቶች ዉስጥ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማዊያን በእስራኤል ጥቃት ህይወታቸዉ እንዲያልፍ እና ከባድ ጉዳት እንዲደርስባቸዉ ሆኗል ነዉ ያለዉ፡፡

ጥቃቱ የአየር እና የከባድ መሳሪያ ድብደባ፣ የሰብዓዊ ድጋፎች እንዳይገቡ ማድረግ፣ በዜጎች ላይ ተኩስ መክፈት ፣ ቤቶችን እና መኪኖችን ማቃጠልን ያካተተ ነበር ሲል አስታዉቋል፡፡

በተጨማሪም ወደ ጋዛ ነዳጅ እንዳይገባ በማድረግ እና ከ2መቶ60 ሺህ በላይ ድንኳኖች እና መጠለያዎች እንዳይደርሱ በማድረግ ጭምር የተደረገ ነዉ ብሎታል፡፡

የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ እና አሸማጋዮች እስራኤል ጥቃት ማድረሷን እንድታቆም እና በተኩስ አቁም ስምምነቱ መሰረት የገባችዉን ሃላፊነት እንድትወጣ ጫና እንዲያደርጉባት ጠይቋል፡፡

የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር፤ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ በእስራኤል ጥቃት ህይወታቸዉ ያለፉ ፍልስጤማዊያን ቁጥር 1መቶ16 ደርሷል፤ የተጎጂዎች ቁጥር ደግሞ ከ4መቶ90 በላይ ሆኗል ሲል አስታዉቋል ሲል ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


በጋምቤላ ክልል ከ 10 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ ተባለ።

በክልሉ ባለፉት ሁለት አመታት በተፈጠረ ግጭት በሶስት  ወረዳዎች ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች  ከመኖሪያ ቀያቸዉ መፈናቀላቸዉ ተነግሮናል።


በክልሉ ተከስቶ በነበረዉ ከፍተኛ  ግጭት እና  አለመረጋጋት ምክንያት በተለይ በጆር÷ ኢታንግ÷ አኮቦ ወረዳዎች ላይ 10 ሺህ 333 ሰዎች ተፈናቅለዋል።

በጋምቤላ ክልል የኑዌር እና አኝዋክ ብሄረሰቦች በሚገኙበት ኢታንግ ልዩ ወረዳ በባለፉት ሁለት አመታት ግጭት የ አስር ቀበሌ ነዋሪዎች ቅያቸውን ጥለዉ መሸሻቸዉ ተገልፆል።

ከኢትዩ ኤፍኤም ጋር ቆይታ ያደረጉት የጋምቤላ ክልል የአደጋ ስጋት  ስራ አመራር አገልግሎት ዳይሬክተር ጃክ ጆይ በነባር ብሄረሰቦቹ መካከል  መነሻ ሆኖ በነበረዉ ግጭት በዚህ ወረዳ ብቻ አምስት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ሁለት ሰዎች ተፈናቅለዉበታል ብለዋል።

በተጨማሪም ከዚህ ዉስጥ በጆር እና አኮቦ ወረዳ ዉስጥ በነበሩ 8 ቀበሌ ዎች ከ 5 ሺህ በላይ  የሚሆኑ ተፈናቃይ  ነዋሪዎች አሉ  ተብሏል። 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን በኢታንግ ልዩ ወረዳ ላይ በተወሰኑ ነዋሪዎች መካከል የተነሳዉ አለመግባባት ብሄርን መሰረት አድርጎ ወደ ዉጥረት መሸጋገሩን ኮምሽኑ ከነዋሪዎች መስማቱን በወቅቱ  ገልፆ ነበር።

አቶ ጃክ በጋምቤላ ክልል የአመራር ለዉጡን ተከትሎ ሁለቱ ብሄረሰቦችን ዉይይት እንዲያደርጉ እና ተፈናቃዩችን ወደ ቀያቸው  ለመመለስ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።

በሶስቱ ወረዳዎች የተፈናቀሉ አብዛኞቹ የአኝዋክ ብሄረሰቦች በመሆናቸዉ ወደ ቀያቸዉ እንዲመለሱ ከስምምነት መደረሱን ዳይሬክተሩ ለጣቢያችን ገልፀዋል።

ተፈናቃዮቹ አሁን ላይ በኢታንግ ልዩ ወረዳ ባለ መጠለያ የሚገኙ ሲሆን የተቃጠሉ ቤቶቻቸዉን መገንባት እና መልሶ ማቋቋም እንዲቻል  ለማድረግ ስራ መጀመሩን አቶ ጃክ ተናግረዋል።


ከዚህ ቀደም ጣቢያችን አነጋግሯቸዉ የነበረዉ የጋምቤላ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ሀላፊዉ አቶ ማበር ኮር አሁን ላይ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ስለመገኘቱ ነግረዉናል።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ቲክቶክ ሕፃናትን በሚያካትቱ የወሲብ የቀጥታ ስርጭት ትርፍ እያገኘ ነው ተባለ

ቲክ ቶክ ገና ከ15 ዓመት በታች በሆኑ እና በአሥራዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች በሚከናወኑ ወሲባዊ የቀጥታ ስርጭት ትርፋማ እየሆነ እንደሚገኝ ተመላክቷል። በኬንያ የሚኖሩ ሦስት ሴቶችን እንደተናገሩት ይህን ተግባር የጀመሩት በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያሉ ነው። በሌሎች የመልእክት መላላኪያ መድረኮች ለሚላክ ወሲባዊ ይዘት በግልፅ ለማስተዋወቅ እና ክፍያ ለመደራደር ቲክቶክን እንደተጠቀሙ ተናግረዋል።

ቲክ ቶክ “ለመሰል ብዝበዛ ምንም ትዕግስት የለኝም” ሲል ለቢቢሲ አስታውቋል። የቀጥታ ስርጭቶች ከኬንያ በቲክ ቶክ ታዋቂ ናቸው ። በእያንዳንዱ ምሽት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ሴቶች  በአለም ዙሪያ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚመለከቱት ገጾች ላይ ሲጨፍሩ ይታያል።ናይሮቢ ውስጥ ከጠዋቱ ሁለት ሰአት ነው፣ እና የቲክ ቶክ ህይወት ሙሉ በሙሉ እንደቀጠለ ነው። አንዲት ሴት ካሜራዋን አብርታ በመቀመጫዋ ስትጨፍር ወይም ቀስቃሽ ምስል ስትነሳ ሙዚቃ በኃይ ይደመጣል፣ ሌሎች ተጠቃሚዎች እርስ በርሳቸው ይጨዋወታሉ። ስሜት ገላጭ ምስሎች "ስጦታዎች" ከዚያም ይቀጥላሉ።ባየናቸው አንዳንድ የቀጥታ ስርጭቶች ላይ የጾታዊ አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ ኮድ የተደረገባቸው የወሲብ ቃላት ጥቅም ላይ ውለዋል ሲል ቢቢሲ ዙግቧል።

የኢሞጂ ስጦታዎች ለቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት ክፍያ ሆነው ያገለግላሉ ። ምክንያቱም ቲክቶክ ግልጽ የሆኑ ወሲባዊ ድርጊቶችን እና እርቃን ይዘቶችን ስለሚያስወግድ ነው።በሌሎች መድረኮች ላይ የበለጠ ግልጽነት ያለው ይዘት ይላካል። ስጦታዎች ወደ ገንዘብ ሊለወጡ ይችላሉ።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል

የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በየካቲት ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የነዳጅ ማደያዎች በነዳጅ ውጤቶች ግብይት አዋጁና በአሠራር መመሪያው መሠረት ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን በታማኝነት እንዲያገለግሉ ለኢፕድ በላከው መረጃ አመላክቷል።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


call 📞0914280819
መርጌታ ውዴ የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች
1🍀 ለገበያ
2🍀 ለመስተፍቀር
3🍀 ለመፍትሄ ሀብት
4🍀 ለበረከት
5🍀 ለጥይት መከላከያ
6🍀 ለስንፈተ ወሲብ
7🍀 የተወሰደ ገንዘብ ለማስመለስ
8🍀 ራዕይ የሚያሳይ
9🍀 ለዓቃቤ ርዕስ
10🍀 ለመክስት
11🍀 ለቀለም(ለትምህርት)
12🍀 ሰላቢ የማያስጠጋ
13🍀 ለመፍትሔ ስራይ
14🍀 ጋኔን ለያዘው ሰው
15🍀 ለሁሉ ሠናይ
16🍀 ለቁራኛ
17🍀 ለአምፅኦ
18🍀 ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ
19🍀 ለግርማ ሞገስ
20🍀 ለቁማር
21🍀 ለዓይነ ጥላ
22🍀 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
23🍀 ለሁሉ መስተፋቅር
24🍀 ጸሎተ ዕለታት
25 🍀ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
26🍀 ለእጅ ስራ

ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ ለማንኛውም ነገር ያናግሩን መፍትሄ አለን!!!
ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
☎ 📞📞
0914280819
 
ባላቹህበት እንሰራለን


የባህር በር ለማግኘት ቆርጫለሁ ያለችው ኢትዮጵያ ከወደ ኬኒያ ያልተጠበቀ የምስራች ሰምታለች።

የኬንያው ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶ ኢትዮጵያ የላሙ ወደብን እንድትጠቀም የሚያስችል ስምምነት መፈፀማቸውን ተናግረዋል፡፡ በላሙ ካውንቲ ተገኝተው ፕሬዝደንቱ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸውን ምርቶች በዚህ ወደብ በኩል ማስገባት የሚያስችል ስምምነት ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር አዲስ ወደብ ለማግኘት ይፋ ባልተደረገ ሰነድ ስምምነት እየፈጸመች መሆኑ ጭምጭምታ በሚሰማበት ሰዓት ነው የኬኒያው ፕሬዝዳንት ይሄን ያበሰሩት።

ፕሬዝዳንት ሩታ ይሄን ሲናገሩም “በቅርቡ ኢትዮጵያ ይህንን ወደብ መጠቀም እንድትችል ስምምነት አድርገናል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ የሚያስገባቸውን ምርቶች በላሙ ወደብ በኩል ማስገባት ሲጀምር ለበርካታ ሰዎች የስራ አድል የምንፈጥር ከመሆኑም በላይ የአካባቢውን ኢኮኖሚ እናሳድጋለን” ያሉ ሲሆን በቅርብ ቀናት ውስጥ በላሙ ወደብ የአካባቢው አገራት መሪዎች የሚገኙበት ግብዣ እንደሚከናወንም አስታውቀዋል፡፡ 

ከሞምባሳ ቀጥሎ የኬንያ ሁለተኛው ትልቁ ወደብ የሆነው ላሙ የመንገድ ስራ ግንባታ ከተጀመረ ከአስር አመታት በላይ ያለፈው ሲሆን መንገዱ በኢትዮጵያ በኩል አድርጎ እስከ ደቡብ ሱዳን የሚዘረጋ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶ እንደገለፁት በዚህ ፕሮጀክት የላሙ ወደብ በሶስት ክፍሎች የማልማት ስራ እንደሚከናወንለት እቅድ የተያዘ ሲሆን አንደኛው ምእራፍ ተጠናቆ አሁን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆኗል ሲል ካፒታል ኒውስ ዘግቧል፡፡

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ከአዲግራት ከተማ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 5.2 የተለካ ርዕደ መሬት ተከሰተ

ዛሬ እሁድ ከአዲግራት ከተማ 46 ኪሎ ሜትር በስተምስራቅ ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ ላይ በሬክተር ስኬል 5.2 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት ገለጸ። ርዕደ መሬቱ የተከሰተው ከቀኑ 5 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ላይ መሆኑንም መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በአፋር ክልል ባሉ አካባቢዎች ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢከሰትም፤ በትግራይ ክልል ከተሞች አቅራቢያ ርዕደ መሬት ሲመዘገብ ግን በዚህ ዓመት የመጀመሪያው ነው። የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ቀጠና የተከሰተ መሆኑን የጠቆመው የአውሮፓ ሜዲትራንያን ሴይስሞሎጂ ማዕከል (EMSC)፤ መጠኑም በሬክተር ስኬል 5.3 የተለካ እንደሆነ አስታውቋል።

በኤርትራ ከአንድ ሳምንት በፊት የደረሰ ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 4.6 ሆኖ ተመዝግቧል። የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው በቀይ ባህር ሰሜናዊ አቅጣጫ ከአስመራ 24 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ አካባቢ ነበር። በሀገሪቱ ባለፈው ታህሳስ ወር አጋማሽም እንዲሁ ተመሳሳይ ርዕደ መሬት ተመዝግቧል።

በሐምሌ 2015 ዓ.ም. በኤርትራ ባህር ዳርቻ ዳህላክ ደሴት አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተደጋጋሚ ንዝረቶች አስከትሎ እንደነበር ይታወሳል። ንዝረቱን በሽሬ፣ አዲግራት፣ አድዋ፣ አክሱም እና መቐለ ከተማ ያሉ ነዋሪዎች መስማታቸውን በወቅቱ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸው ነበር።

Via:ኢትዮጵያ ኢንሳይደር


@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ኢንተርናሽናል ሜዲካል ኮር የተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት፣ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በቋራ ወረዳ ከታኅሳስ ወር መጨረሻ ወዲህ በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ አምስት ሰዎች እንደሞቱና 270 ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ አስታውቋል።

ባካባቢው ያለው የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት፣ የንጽህና አጠባበቅ ጉድለትና የሰዎች እንቅስቃሴ በሽታው በስፋት እንዲሠራጭ ሊያደርገው እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል ተብሏል። በዞኑ በሽታው ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ባንድ የጸበል ቦታ ውስጥ ከተከሰተ ወዲህ፣ በክልሉ በ16 ዞኖች በ60 ወረዳዎች የተሠራጨ ሲኾን፣ እስካሁን 4 ሺሕ 983 ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ የድርጅቱ መረጃ ያመለክታል።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ኢትዮጵያ ላሙ ወደብን ተጠቅማ ምርቶችን ለማስገባት ተስማምታለች ሲሉ ፕሬዝዳንት ሩቶ ገለጹ

ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከየብስ ተከብባ ከምትገኘው ኢትዮጵያ ጋር ወደቡን ወደ ውስጥ ሀገር ለሚገቡ ምርቶች ማጓጓዣነት ለመጠቀም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

የላሙ ወደብ የክልሉ የንግድ ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል ኬንያ እና ጎረቤት ሀገራት ባደረጉት ስምምነት መሰረት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሊደረግበት ተዘጋጅቷል።

ፕሬዝዳንት ሩቶ በላሙ ምስራቅ ክልል በንዳው ደሴት የመጀመሪያውን የኬንያ ከግሪድ ውጪ የፀሐይ ኃይል ተደራሽነት ፕሮጀክት በሐሙስ ዕለት ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት "ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የላሙን ወደብ መጠቀም ለመጀመር ተስማምተናል፤ ይህም ተጨማሪ የስራ እድሎችን ለመፍጠር እና የዚህን ክልል ኢኮኖሚ ለማሳደግ ያስችለናል" ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ከሞምባሳ ወደብ ቀጥሎ ሁለተኛ የሆነውን የላሙን ወደብ ላይ የሀገራት መሪዎችን በቅርቡ እንደሚያስተናግዱ ገልጸዋል።በዚህም በላሙ ወደብ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ዘመናዊ ማቆሚያዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።

Via Capital Newspaper

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


እንኳን ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


የአሜሪካው ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) የገንዘብ እርዳታ ካቆመ ወዲህ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች መካከል 85 በመቶዎቹ ሥራቸውን ማቆማቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

በተለይ በሰብዓዊ መብቶች፣ በሰላም፣ በጤና እና ልማት ዘርፎች የሚሠሩ ድርጅቶች ይበልጥ ተጎጂ እንደኾኑ የጠቀሰው ዘገባው፣ በትግራይ ለ100 ሺሕ የጦርነት ተፈናቃዮች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ያቀርብ የነበረ መንግሥታዊ ያልኾነ ድርጅትም ሥራ ማቆሙን አመልክቷል።

መንግሥትም፣ የውጭ ዜጋ የሆኑ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ የሚያግድ ሕግ እያዘጋጀ መኾኑን ምንጮች መናገራቸውን የዜና ምንጩ ዘገባ ያመለክታል።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


Репост из: እውን መረጃ
call 📞0914280819
መርጌታ ውዴ የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች
1🍀 ለገበያ
2🍀 ለመስተፍቀር
3🍀 ለመፍትሄ ሀብት
4🍀 ለበረከት
5🍀 ለጥይት መከላከያ
6🍀 ለስንፈተ ወሲብ
7🍀 የተወሰደ ገንዘብ ለማስመለስ
8🍀 ራዕይ የሚያሳይ
9🍀 ለዓቃቤ ርዕስ
10🍀 ለመክስት
11🍀 ለቀለም(ለትምህርት)
12🍀 ሰላቢ የማያስጠጋ
13🍀 ለመፍትሔ ስራይ
14🍀 ጋኔን ለያዘው ሰው
15🍀 ለሁሉ ሠናይ
16🍀 ለቁራኛ
17🍀 ለአምፅኦ
18🍀 ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ
19🍀 ለግርማ ሞገስ
20🍀 ለቁማር
21🍀 ለዓይነ ጥላ
22🍀 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
23🍀 ለሁሉ መስተፋቅር
24🍀 ጸሎተ ዕለታት
25 🍀ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
26🍀 ለእጅ ስራ

ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ ለማንኛውም ነገር ያናግሩን መፍትሄ አለን!!!
ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
☎ 📞📞
0914280819
 
ባላቹህበት እንሰራለን


ግብፅ ኢትዮጵያ የባህር ሃይል እንድታቋቁም አልፈቅድም አለች

ወደብ አልባ የሆነችው ኢትዮጵያ በቀይ ባህር የራሷን ወደብ ለማግኘት እና የባህር ሀይል ለመቋቋም እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል።

ግብጽ የቀይ ባህር አካል ያልሆነ ማንኛውም ሀገር በባህሩ ዙሪያ የሚያደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እና የባህር ሀይል ለማቋቋም የሚደረግ ጥረት እንደማትቀበል አስታወቀች፡፡

ይህ የተባለው በግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብዳላቲ የተመራ ልዑክ በኤርትራ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ውይይት ማድረጉን ተከትሎ ነው፡፡

በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት የቀይ ባህርን ጨምሮ የጋራ በሚያደርጓቸው ቀጠናዊ እና በተለያዩ መስኮች የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ተስማተዋል፡፡

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር “የቀይ ባህር ደህንነት በተዋሳኝ ሀገራቱ ፍላጎት ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው ፤ምንም አይነት ወታደራዊም ሆነ የባህር ሃይል በአካባቢው መገኘትን አንፈቅድም” ብለዋል።

አክለውም “ወደብ አልባ ሀገራት በቀይ ባህር ዙሪያ የባህር ሀይል ማቋቋም የቀጠናውን እና የባህሩን ደህንነት ለመጠበቅ የተደረሰውን ስምምነት ክፉኛ የሚጎዳ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ እንዳስታወቀው አብዳላቲ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር ባደረጉት ውይይት፤ በአህጉራዊ የጋራ ጉዳዮች በተለይም በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሰላምና ደህንነትን መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፣ በሶማሊያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት እና ሉዓላዊነቷን በሁሉም ግዛቶቿ ላይ ለማስረፅ የሚያስችል የሃሳብ ልውውጥ ተካሂዷል።

ስብሰባው በሊቢያ እና በአፍሪካ ሳህል
አካባቢ ስላለው ሁኔታ እንዲሁም በቀይ ባህር ውስጥ ያሉ ለውጦች እና ማንኛውም ቀይ ባህር አካል ያልሆነ መንግስት በፀጥታ እና በአስተዳደር ውስጥ ተሳትፎን ውድቅ በማድረግ ላይ ትኩረቱን አድርጓል ።

በተጨማሪም በጥቅምት 2024 በኤርትራ ከተካሄደው የመጀመሪያው የመሪዎች ጉባኤ በኋላ ተመሳሳይ የሚኒስትሮች ስብሰባዎችን በሞቃዲሾ እና በአስመራ ለማካሄድ እና በቅርቡ ለሁለተኛው የፕሬዝዳንት ጉባኤ ለመዘጋጀት መምከራቸውን አብዳላቲ ጠቁመዋል።

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በበኩሉ ትላንት ምሽት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብዳላቲ ከተመራ ልዑካን ጋር በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይቶች ማድረጋቸውን አስታውቋል፡፡

በሱዳን ሶማሊያ እና በአጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም በቀይ ባህር አካባቢዎች የሰላም እና የደህንነት ፈተናዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት መካሄዱንም መግለጫው አክሏል፡፡

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


"የዓድዋ በዓል በአዲስ አበባ ብቻ ነው የሚከበረው የሚለው መረጃ  ትክክል አይደለም" የባህልና ስፓርት ሚኒስቴር

የካቲት 22/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ነገ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም የሚከበረው የዓድዋ ድል በዓልን ታሳቢ በማድረግ ባህልና ስፓርት ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት "አድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል" "አድዋን እንዘክራለን ኢትዮጵያን አጽንተን ለትውልድ እናሻግራለን" በሚል መሪ ቃል ቀኑን አስቦ ውሏል።

'በተለያዩ ክልል ከተሞች በዓሉን የማክበር ፍላጎት ቢኖርም ክልከላዎች መደረጉ ተገቢ አይደለም' የሚሉ አሳቦች ከበዓሉ ተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡

እንዲሁም "የዓድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ ብቻ ከሚከበር መላው አፍሪካን ወደ ኢትዮጵያ በመጋበዝ እንደሌሎች በዓላት የቱሪዝም መዳራሻ ማድረግ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን መፍጠር ያስፈልጋል" ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የባህልና ስፓርት ሚኒስትር ዴኤታ ጸጋዬ ማሞ፤ 'በአዲስ አበባ ብቻ ክብረ በዓሉ እየተከበረ ነው' የሚለው ሀሳብ ወይም መረጃ ትክክል እንዳልሆነ በሌሎች ክልሎችም እየተከበረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአንድ ወቅት እንዳይከበር ክልከላዎች የነበሩት የተሳሳተ አመለካከት ስለነበር እንደሆነም አስታውሰዋል፡፡

በዓድዋ በዓል ላይ ምን ተጨማሪ ሥራዎችን ይሰሩ? የሚለውና የተሰጡ አስተያየቶችን ተቀብሎ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቤት ሥራዎችን ይወስዳል ሲሉም ገልጸዋል።

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ባለበት የአካል ጉዳት ትምህርቱን እንዲያቋርጥ ጫና የደረሰበት ዶክተር ቢኒያም ኢሳያስ በከፍተኛ ውጤት ተመረቀ

በትምህርት ቆይታው ያጋጥሙትን ውስብስብ ችግሮች በማሸንፍ ለበርካቶች አራያ የሆነው ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በከፍተኛ ወጤት ተመርቋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሕክምና ተማሪዎችን አስመርቋል።

ዶክተር ቢኒያም ኢሳያስ የአዲስ አበባ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ካስመረቃቸው ተማረዎች መካከል አንዱ መሆን ችሏል።

ዶክተር ቢኒያም በትምህርት ቆይታው ያጋጥሙትን ውስብስብ ችግሮች አልፎ ዛሬ ለደረሰበት ስኬት በመብቃቱ መደሰቱን ገልጿል።

ዶክተር ቢኒያም እናትና አባትም ልጃቸው ከልጅነቱ ጀምሮ ጎበዝ ተማሪ መሆኑን ገልጸው፤ ለህልሙ መሳካት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣታቸውን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ኮሚሽን በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ የሕክምና ትምህርቱን እንዲቀጥል መወሰኑ ይታወሳል።

Via ኢፕድ

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


የካይሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት አስመራ ተከስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከቀጠናው አገራት ጋር ውጥረት ውስጥ ስትገባ ሹማምንቶቿን ወደ ኢትዮጰያ ጎረቤት የመላክ ልምድ ያላት ግብጽ፤ የኢትዮ ኤርትራን ውጥረት ተከትሎ ከአዛውንቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መክራለች፡፡

ኤርትራን የቀጠናው የቅርብ አጋራቸው ለማድረግ እየተሯሯጡ የሚገኙት  የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በውጭ ጉዳይ የተመራ ልዑክ ወደ አስመራ ልከዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትናንት ማምሻውን በግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድር አብደላቲ የተመራው የካይረሮ ልኡካን ቡድን በቤተ መንግሥታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የፕሬዝዳንቱ እና የካይሮ ባለሥልጣናት ውይይት ከዚህ ቀደም በሁለቱ አገራት ፕሬዝዳንቶች ደረጃ የተጀመረውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማሰቀጠል ላይ ያተኮረ ነው ቢባልም፤ የኢትዮጵያ ጉዳይ በዋነኝነት እንደተነሳ ግን ተገምቷል፡፡ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኤርትራ ቃል አቀባይ የማነ ገ/መስቀል ፕሬዝዳንት ኢሳያስና የግብጽ ባለሥልጣናት በተለያ ገዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል ያሉ ሲሆን፤ ይይቱ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እንዲሁም በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል፡፡

በተለይም አስመራ እና ካይሮ በአፍሪካ ቀንድ እና ቀይ ባህር የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ  አጋርነት አሰላለፍ ለመያዝ መነጋገራቸው ተሰምቷል። ሁለቱ አገራት በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር አካባቢዎች የሰላም እና የደህንነት ፈተናዎችን በጋራ ለመመከት መስማማታቸውን የማነ በማብራሪያቸው ገልጸዋል፡፡ ሁለቱ አገራት ቀይ ባህር ላይ የያዙት የጋራ አቋም ቀድሞውኑ የባህር ጠረፍ ከሌላቸው አገራት ወጪ አናስገባም የሚል ነው፡፡

የግብጽ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ታሚም ካህላፍ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ የቀይ ባህር አንዱ የውይይት አጀንዳ መሆኑን አረጋግጠለዋል፡፡  ቃል አቀባዩ አብደላቲ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና በአፍሪካ ቀንድ፣ በሶማሊያ፣ በሱዳን፣ በሊቢያ እና በቀይ ባህር ያሉ ለውጦችን ጨምሮ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል ብለዋል።

የማነ በበኩላቸው በአስመራው ውይይት የሱዳን ጦርነት አፋጣኝ እና ሰላማዊ መፍትሄ የሚገንበነት አማራጭ ላይ እና የሶማሊያ ሀገር ግንባታ አጀንዳ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡  ሁለቱ አገራት እንደ ሱዳንና ሶማሊያ ባሉ አገራት የጋራ ጥቅማቸውን ማስከበር በሚችሉበት አቅጣጫ ላይ ከዚህ ቀደምም ሲመክሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ውጥረት ውስጥ በገባችበት ወቅት ኤርትራ እና ግብጽ ለሞቋደሾ ውግንና አሳይተው የሦስትዮሽ ግንኑነት መመስረታቸው ይታወሳል፡፡  ይሁን እንጂ አሁን ላይ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነታቸውን ማደሳቸውን ተከትሎ ግብጽ እና ኤርትራ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን አስቀጥለዋል፡፡ ግብጽ እና ኤርትራ በተለይ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር ቀጥተኛ ተጋሪነት የመግባት ፍላጎት እናዳላት ከገለጸች በኋላ ተከታታይ ግንኙነቶችን እያደረጉ ነው፡፡

የሁለቱ አገራት ግንኙነት ዋና ማጠንጠኛ ደግሞ ቀይ ባህር ጉዳይ ሲሆን፣ ግብጽ በአፍሪካ ቀንድ ሚዛን የምትደፋበት አቅም ለማግኘትም እግረ መንገዷን እየፈለገች ነው፡፡ ይህንኑ የግብጽን አሰላለፍ አስመራ የተገኙት የካይሮ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለኤርትራ ዜና አገልግሎት በሰጡት ማብራሪያ ጠቁመዋል፡፡ የውጭጉዳይ ሚኒስትሩ አብደላቲ ከአስመራ በሰጡት ማብራሪያ በሁለቱ አገራት መካከል በየወቅቱ የሚደረጉ ምክክሮች አላማ በቀጠናዊ ጸጥታና መረጋጋት ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋሞችን ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል፡፡

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja


ቻይና በዓለማችን ውድ የሚባለውን አዲስ ማዕድን አገኘች፡፡

የዓለማችን ሁለተኛዋ ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው ቻይና ቶሪየም የተሰኘውን ተፈላጊ ማዕድን ማግኘቷን አረጋግጣለች፡፡

ሀገራት ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር በሚል የዲፕሎማሲ እና የፊት ለፊት ግጭት ውስጥ ሲገቡ የሚታይ ሲሆን ከነዚህ ምክንያቶች መካከል አንዱ የሀይል ፍላጎትን ለማረጋገጥ ሀብት ፍለጋ ዋነኛው ነው፡፡

ነዳጅ ለረጅም ዓመታት ዋነኛ የሀይል ምንጭ መሆኑን ተከትሎ ሀገራት ፍላጎታቸውን ለማስከበር የተለያዩ ጥረቶችን ሲከተሉ ቆይተዋል፡፡

አሁን ላይ የዓለም የሀይል ምንጭ ወደ ታዳሽ እና የከፋ የአካባቢ ብክለት የማያደርስ አማራጭ በመፈለግ ላይ ሲሆን የጸሀይ ሀይል፣ ከውሃ የሚመነጭ የሀይል አማራጭ እና የኑክሌር ሀይል ዋነኛ አማራጮች ናቸው፡፡

ዩራኒየም እና ቶሪየም ደግሞ ለኑክሌር ሀይል አማራጭ ዋነኛ ግብዓት ሲሆኑ ዩራኒየም ማዕድን እንደ ልብ አለመገኘት፣ ማዕድኑም በተወሰኑ የዓለማችን ሀገራት ብቻ መገኘቱ እጥረቱን ሲያባብሰው ቆይቷል፡፡

ቻይና አገኘሁት ያለችው ቶሪየም ማዕድን አንድ ሚሊዮን ቶን መጠን አለው የተባለ ሲሆን፤ ሀገሪቱ የሀይል ፍላጎቷን ለ60 ሺህ ዓመታት እንድትሸፍን ይጠቅማታል ተብሏል፡፡

እንደ መንግስታዊው የሳውዝ ቻይና ፖስት ዘገባ ከሆነ ቶሪየም ማዕድኑ የተገኘው በደቡባዊ የሀገሪቱ አካባቢ ሞንጎሊያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ቶሪየም ማዕድን በተለይም የኑክሌር ሀይልን ለማመንጨት፣ ቴሌስኮፕ ሌንሶችን፣ ሴራሚክ፣ ካሜራዎችን እና ሌሎች ተፈላጊ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ለማምረት ይውላል፡፡

@Ewun_Mereja
@Ewun_Mereja

Показано 20 последних публикаций.