የባህር በር ለማግኘት ቆርጫለሁ ያለችው ኢትዮጵያ ከወደ ኬኒያ ያልተጠበቀ የምስራች ሰምታለች።
የኬንያው ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶ ኢትዮጵያ የላሙ ወደብን እንድትጠቀም የሚያስችል ስምምነት መፈፀማቸውን ተናግረዋል፡፡ በላሙ ካውንቲ ተገኝተው ፕሬዝደንቱ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸውን ምርቶች በዚህ ወደብ በኩል ማስገባት የሚያስችል ስምምነት ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር አዲስ ወደብ ለማግኘት ይፋ ባልተደረገ ሰነድ ስምምነት እየፈጸመች መሆኑ ጭምጭምታ በሚሰማበት ሰዓት ነው የኬኒያው ፕሬዝዳንት ይሄን ያበሰሩት።
ፕሬዝዳንት ሩታ ይሄን ሲናገሩም “በቅርቡ ኢትዮጵያ ይህንን ወደብ መጠቀም እንድትችል ስምምነት አድርገናል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ የሚያስገባቸውን ምርቶች በላሙ ወደብ በኩል ማስገባት ሲጀምር ለበርካታ ሰዎች የስራ አድል የምንፈጥር ከመሆኑም በላይ የአካባቢውን ኢኮኖሚ እናሳድጋለን” ያሉ ሲሆን በቅርብ ቀናት ውስጥ በላሙ ወደብ የአካባቢው አገራት መሪዎች የሚገኙበት ግብዣ እንደሚከናወንም አስታውቀዋል፡፡
ከሞምባሳ ቀጥሎ የኬንያ ሁለተኛው ትልቁ ወደብ የሆነው ላሙ የመንገድ ስራ ግንባታ ከተጀመረ ከአስር አመታት በላይ ያለፈው ሲሆን መንገዱ በኢትዮጵያ በኩል አድርጎ እስከ ደቡብ ሱዳን የሚዘረጋ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶ እንደገለፁት በዚህ ፕሮጀክት የላሙ ወደብ በሶስት ክፍሎች የማልማት ስራ እንደሚከናወንለት እቅድ የተያዘ ሲሆን አንደኛው ምእራፍ ተጠናቆ አሁን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆኗል ሲል ካፒታል ኒውስ ዘግቧል፡፡
@Ewun_Mereja