በተባበሩት አረብ ኤምሬት የሚኖሩ ኮሚኒቲዎች አሁን ላይ ባለው የፓስፖርት አፈፃፀም መደሰታቸውን ገለፁ።
———————————
የካቲት 1/2017 ዓ.ም.
በአቡዳዊ እና በዱባይ አካባቢ የሚገኙ ዜጎች ተቋሙ ከዚህ በፊት የነበረውን ችግር በመቅረፍ በፍጥነት ፓስፖርት እየሰጠ በመሆኑ ለተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ተቋሙ እየሰራ ላለው ስራ ያዘጋጁትን የእውቅና ስጦታ በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ዶ/ር ዑመር ሁሴን ለአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በኮሚኒቲ ማህበራቱና በሚሲዮኑ ስም አስረክበዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው ለተደረገላቸው የእውቅና ስጦታ ምስጋናቸውን አቅርበው ከባዱን ጊዜ በፍጥነትና በትጋት በመስራት የፓስፖርት እጥረት እንዳይኖር በወቅቱ ቡክሌቶችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚገኙ ዜጎቻችን ቅድሚያ በመስጠት የነበረውን የፓስፖርት ውዝፍ መጨረስ ብቻ ሳይሆን ፓስፖርት በ3 ሳምንት ውስጥ እንዲደርስ በማድረግ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር አድርገናል ብለዋል።
አክለውም በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ የቆንስላና የዜግነት አገልግሎት ዘርፍ አመራርና ሰራተኞች ሊመሰገኑ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
——
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/