የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት የ3 ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ መግለጫ ሰጠ።
ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በዚህ በጀት አመት አገልግሎት ተቋሙ አዳዲስ የአሰራር፣ የአደረጃጃት እና የአመራር ሪፎርም በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
የሠው ሀይሉን በአዲስ መልክ ለማደራጀት ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸውን ወጣቶች በመቅጠር ለማሰልጠንና ለማሰማራት አስፈላጊው ዝግጅት የተደረገ መሆኑን ገልፀው 125 ሰራተኞች ስልጠናቸውን አጠናቀው በሚቀጥለው ሳምንት ስራ እንደሚጀምሩ አሳውቀዋል።
አሰራር ስርአት ማሻሻል እና ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ማሻሻያን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ የኢ-ፓስፖርት ምርት መጀመሩንና ከፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ጀምሮ ወደ ስራ ለማስገባት አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀው ተቋሙ ምቹ የስራ ሁኔታ ከመፍጠር ጋር በተያያዘ ካሳንቺስ የነበረውን ቢሮ በመቀየር በተለይም የውጭ ዜጎች አገልግሎትን፣ የቁጥጥር አገልግሎትን የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
አያይዘውም የቪዛ ስቲከር፣ የትውልደ ኢትዮጲያዊ እና የመኖሪያ ፈቃድ የመታወቂያ ካርዶች በዘመናዊ መልኩ ተዘጋጀተው መጠናቀቃቸውንና በሚቀጥለው ሩብ አመት ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል።
የፓስፖርት የጊዜ ገደብ በማራዘም ከ25 አመት በላይ ለሆኑ ደንበኞች ከ5 ወደ 10 ዓመት የማሻሻል ስራዎች የተሰራ መሆኑንና ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ አገልግሎቱ መሰጠት እንደሚጀመር ገልፀዋል።
አክለውም በዚህ 3 ወር ውስጥ 478 ሽህ ቡክሌት ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ከ367 ሽህ በላይ መደበኛ፣ አስቸኳይ፣ ዲፕሎማቲክና ሰርቪስ ፖስፖርቶች ታትመው ለተገልጋዮች መሰራጨቱንና በአጠቃላይ በሀገሪቱ በቀን ከ7000 በላይ ፓስፖርት አመልካቾችን በመደበኛ እና 600 አመልካቾችን በአስቸኳይ ማስተናገድ መቻሉን ገልፀዋል።
በኢትዬጵያ ለቱሪስትም ሆነ ለቢዝነስ የሚገቡትን በስፋት ለማስተናገድ 188 ሀገራት ቪዛ ኦን አራይቫል ተከፍተው እየተሰራ መሆኑንና በቦሌ የማስተናገድ አቅም እየተሻሻለ መምጣቱንና በዚህም በአየር ኬላ ወደ ሀገር የገቡ 559,848 ከሃገር የወጡ 581,704 በድምሩ1,141,552 መንገደኛ አገልግሎት መሰጠቱን እና በየብስ ኬላ ወደሀገር የገቡ 106,003 ከአገር የወጡ 131,869 በድምሩ 237,872 መንገደኛ አገልግሎት መሰጠቱን አሳውቀዋል።
የውጭ ዜጎች በመቆጠጠር ስራም በአጠቃላይ በአንደኛ ሩብ አመት አገልግሎት ተቋሙ ያከናወናቸው ስራዎች በመግለጫው በዝርዝር ገልፀዋል።
አክለውም የቪዛ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልፀው በአዲስ የኢ-ቪዛ 166,957 ፣ በመዳረሻ ቪዛ 55,229፣ የታደሰ 22,612 እና በቆንስላ ደረጃ 5,799 አጠቃላይ 259,705(109%) ቪዛዎችን ለመስጠት መቻሉን አሳውቀዋል።
በአጠቃላይ የዉጭ ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ አገልግሎትን በተመለከተ 5,259 ቋሚ እና ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድና የትውልደ ኢትዮጲያዊያን መታወቂያ አገልግሎት 17,671(106%) እንዲሁም 12 ዜግነት መሰጠታቸውን ገልፀዋል።
በመጨረሻም የቤተሰብ ምዝገባ፣ የአገልግሎት ቅርንጫፎች የመከፈት እንዲሁም የሪፎሮም ስራዎች በመግለጫው ተካተዋል።
—
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/