Фильтр публикаций


ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች አሳዳጊዎች፤

የተማሪዎች ወርሀዊ ክፍያ ወር በገባ ከ25-30 መከናወን እንዳለበት ይታወቃል ።

ስለዚህ ክፍያችሁን ያልፈፀማችሁ ወላጆች ደብዳቤ ለተማሪዎች ከመላካችን በፊት ቀድማችሁ እንድትከፍሉ ስንል ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ማሳሰብያ:-ጊዜያችሁን ጠብቃችሁ ለምትከፍሉ ወላጆች ምስጋናችን የላቀ ነው።




ጆርጎ አካዳሚ




ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች አሳዳጊዎች፤

ነገ ሀሙስ 5/3/2017 ዓ-ም በትምህርት ቤታችን እና በወረዳ ደረጃ የሴቶች ቀን ይከበራል።

በመሆኑም ሁሊም ከ1-8ኛ ክፍል ያሉ ሴት ተማሪዋች ብቻ ባህላዊ ልብስ ለብሰው እንዲመጡ ስንል እናሳስባለን ።


ማሳሰብያ:-1.መደበኛ ትምህርት ትምህርት ይኖራል።


ጆርጎ አካዳሚ


ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች አሳዳጊዎች፤

የተማሪዎች ወርሀዊ ክፍያ ወር የቀጠለ ወር ወር በገባ ከ25-30 መከናወን እንዳለበት ይታወቃል ።

ስለዚህ ክፍያችሁን ያልፈፀማችሁ ወላጆች ቅጣት ውስጥ ከመግባታችሁ በፊት የመጀመሪያ መንፈቅ አጋማሽ ፈተና ከመጀመሩ አስቀድሞ  እንድትከፍሉ ስንል ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ጊዜያችሁን ጠብቃችሁ ለምትከፍሉ ወላጆች ምስጋናችን የላቀ ነው።

ማሳሰብያ:-1.ወርሃዊ ክፍያ ከፍላችሁ ካላጠናቀቃችሁ ፈተና ላይ የማናስቀምጥ መሆኑን እንገልፃለን ።


ጆርጎ አካዳሚ


ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች አሳዳጊዎች፤

የተማሪዎች ወርሀዊ ክፍያ ወር በገባ ከ25-30 መከናወን እንዳለበት ይታወቃል ።

ስለዚህ ክፍያችሁን ያልፈፀማችሁ ወላጆች ቅጣት ውስጥ ከመግባታችሁ በፊት ቀድማችሁ እንድትከፍሉ ስንል ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ጊዜያችሁን ጠብቃችሁ ለምትከፍሉ ወላጆች ምስጋናችን የላቀ ነው።

ማሳሰብያ:-1.ቅጣት ውስጥ ከገባችሁ እንደማንኛውም ትምህርት ቤት  ቅጣት 10 ብር ነው።
2.የመማሪያ መፃህፍት ከሀሙስ ጀምሮ ከኦሮሚያ ትምህር ቤቶች ማህበር ስለምንረከብ ከአርብ ጀምሮ በአካል በመገኘት መግዛት ትችላላችሁ።


ጆርጎ አካዳሚ


ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች አሳዳጊዎች፤

የተማሪዎች ወርሀዊ ክፍያ ወር በገባ ከ25-30 መከናወን እንዳለበት ይታወቃል ።

ስለዚህ ክፍያችሁን ያልፈፀማችሁ ወላጆች ቅጣት ውስጥ ከመግባታችሁ በፊት ቀድማችሁ እንድትከፍሉ ስንል ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ጊዜያችሁን ጠብቃችሁ ለምትከፍሉ ወላጆች ምስጋናችን የላቀ ነው።


ጆርጎ አካዳሚ


22/1/2017 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ወላጆች

ቢሾፍቱ

  ከወረዳው ትምህርት ቢሮ በደረሰን አሰቸኳይ መልዕክት መሠረት ነገ 23/01/2017 ዓ.ም  ከ6:00 ጀምሮ መንገድ ስለሚዘጋጋ የመማማር ማስተማር ሂደት የሚቀጥለው እስከ 6:00 ብቻ መሆኑን ከወዲሁ ማሳሰብ እንወዳለን።

ማሳሰቢያ
አርብ ሙሉ ቀን ትምህር አይኖርም ።

ጆርጎ አካዳሚ


15/1/2017 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ወላጆች

ቢሾፍቱ

  ነገ በበአሉ ምክንያት መንገድ ሊዘጋጋ እና ተማሪዎች ሊቸገሩ ስለሚችሉ ትምህርት የማይኖር መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን።

ማሳሰቢያ
ከሰኞ መስከረም 20 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርታቸውን የሚከታተሉት እስከ 9:00 ሰዓት ነው።

ጆርጎ አካዳሚ


10/1/2017

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ወላጆች

ለ2017 ዓ.ም  የትምህርት ዘመን እንኳን  አደረሰን።

የ2017 ዓ.ም መደበኛ ትምህርት መስከረም 13/2017ዓ.ም እንጀምራለን።

ስለሆነም ሁሉም ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ  በመደመኛ ሰዓት ት/ቤት እንድትገኙ።

ሁሉም  ተማሪ ከሰኞ መስከረም 13 እስከ ሀሙስ መስከረም 16 በትምህርት ቤት ውስጥ የሚቆዩት እስከ 6:20(ግማሽ ቀን)ነው።
     ማሳሰቢያ
1. የተማሪዎች ምሳ ዕቃ ላይ ስማቸው በማይለቅ    ቀለም ይፃፍ።
2. የመማሪያ ቁሳቁስ ያላስረከባቹ (ያላሟላችሁ) ወላጆች የማስረከብያ ጊዜ ሰኞ ከ 7:00-9:00 መሆኑን በድጋሚ እናሳስባለን። ።

ጆርጓ አካዳሚ






ሐምሌ 10 ቀን 2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች

የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከሀምሌ 1 እስከ ሀምሌ 52016ዓ.ም ድረስ መሆኑን አሳውቀናል ።

     ነገር ግን በነዚህ በተጠቀሱ ቀናቶች ውስጥ ያላስመዘገባችሁ ወላጆች አላችሁ በመሆኑም 5 ተጨማሪ ቀናትን ማለትም ከሰኞ ሀምሌ 8 እስከ አርብ 12 2016ዓ.ም ተጨማሪ ጊዜ ሰለሰጠን ወላጆች ይህንን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ እንድታስመዘግቡ በጥብቅ እናሳስባለን።
     
        በተባሉት ቀናት ያላስመዘገበ ወላጅ እንደለቀቀ በማሰብ በቦታው አዲስ ተማሪ ለመውሰድ እንገደዳለን


ጆርጎ አካዳሚ




ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

ለውድ የጆርጎ አካዳሚ ት/ቤት ወላጆች

የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የነባር ተማሪዎች ምዝገባ  ለመጀመር ዝግጅት ጨርሰናል።

በመሆኑም ወላጆች ከሐምሌ 1-5/2016 ዓ.ም ድረስ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ በጥብቅ እናሳስባለን።

በተባሉት ቀናት ያላስመዘገበ ወላጅ እንደለቀቀ በማሰብ በቦታው አዲስ ተማሪ ለመውሰድ እንገደዳለን።

ማሳሰብያ: 1.ምዝገባ የሚከናወነው በባንክ በኩል ነው።2.የባንክ ደረሰኝ ይዛችሁ በመምጣት ማወራረድ እና ፎርሞችን መሙላት ይኖርባቹሀል።
3.ነባር ወላጆች ነርሰሪ ተማሪ ካላችሁ ቅድሚያ ለነባር ወላጅ ስለሚሰጥ በተጠቀሱ ቀናት ብቻ የምናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።


ጆርጎ አካዳሚ





Показано 16 последних публикаций.