ሊቨርፑል ተወልዶ ሊቨርፑላዊያንን የተበቀለው ሩኒ በፅሑፍ|
በወጣትነት እድሜው ሽማግሌ የሚመስለው ማንችስተርን በድል ማማ ያንቀጠቀጠው ምናለባትም ምርጡ ኢንግሊዛዊ ጥራ ብትባል በቀዳሚነት የምትጠቅሰው ዋይን ማርክ ሩኒን አስቃኛችዋለው አብራችሁን ቆዩ።
እ ኤ አ ጥቅምት 24 ቀን 1985 በእንግሊዝ ሊቨርፑል ተወለደ። ሩኒ እግር ኳስ መጫወት የጀመረው ገና በልጅነቱ ሲሆን በ9 አመቱ የኤቨርተንን የወጣቶች አካዳሚ ተቀላቀለ።
ዋይኒ ሩኒ ያደገው በከፋ ድህነት ውስጥ ባይሆንም ነገር ግን በእንግሊዝ ሊቨርፑል ውስጥ ጠንካራ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ያለበት አካባቢ ክሮክስት ውስጥ በሰራተኛ መደብ ውስጥ ነው ያደገው። ቤተሰቡ ሀብታም ባይሆንም እሱንና ሁለት ታናናሽ ወንድሞቹን ለማሳደግ ጠንክረው ሰርተዋል።
አባቱ ቶማስ ዋይኒ ሩኒ የጉልበት ሰራተኛ ሆኖ ይሰራ ነበር እናቱ ዣኔት ሩኒ ደግሞ በአካባቢው በሚገኝ ትምህርት ቤት ውስጥ ትሰራ ነበር። በ አካባቢ ውስጥ እንዳሉ ብዙ ነዋሪዎች ተግዳሮቶች እና እንቅፋቶች ገጥሟቸው ነበር። ቤተሰቦቹ ለ ዋይን ሩኒ ለእግር ኳስ ያለውን ፍቅር በመደገፍ እና የሚያስፈልገው ድጋፍ እና ማበረታቻ በማድረግ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል።
በ 2002 በ 16 አመቱ ለኤቨርተን ፕሮፌሽናል ጨዋታውን ማድረግ ቻለ። ከዛ በኃላ ነው የእንግላዝ ክለቦች አይን ውስጥ መግባት የቻለው።
ሩኒ በወጣትነቱ በጥቅምት 2002 አርሰናል ላይ ያስቆጠረው ሮኬት መሳይ የርቀት ጎል ብዞዎቹን አስገረመ በ 16 አመቱ እንዴት ይሄን ሊያደርግ ቻለ ተብሎ በብዙዎች መነጋገሪያ መሆን ቻለ። በፕሪሜርሊጉም የጎል አካውንቱን አንድ ብሎ ጀመረ።
እ.ኤ.አ. በ 2004 የኤቨርተን ቁልፍ ተጫዋች ነበር እናም በዩሮ 2004 ለእንግሊዝ ባሳየው ብቃት የበለጠ ያስደነቀ ሲሆን በጉዳት ውድድሩን እስከሚያጠናቅቅበት ድረስ በውድድሩ አራት ጎሎችን ከመረብ አዋሀደ።
የሩኒ ተሰጥኦ መርሲሳይድን ተሻግሮ ኒውካስል ዩናይትድ እና ቼልሲን ጨምሮ ታላላቅ ክለቦችን ትኩረት ሳበ። ነገር ግን እሱ ማንቸስተር ዩናይትድ ተቀላቀለ።
ብዙዎች አልጠበቡም ነበር ወደ ማንችስተር እንደሚያቀና ለዚህ ዝውውር ቁልፉ ሰው ሰር አሌክስ ቻክማን ፈርጉሰን ነበሩ። ፈርጉሰን ሩኒን ለሚቀጣጥሉት አመታት የዩናይትድን የ አጥቂ መስመር መምራት የሚችል አድርገው ተመለከቱት እድሜው ትንሽ ቢሆንም ፈርጉሰን ከና 18 አመት ያልሞላውን ሩኒን በኦልድትራፎርድ ማየት ተመኘ።
ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ሩኒን እና ቤተሰቡን በማሳመን ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ፈርጉሰንም ስለ ወጣቱ ኮከብ እቅድ ለመነጋገር በሊቨርፑል ክሮክስት የሚገኘውን የሩኒ ቤተሰብ ማነጋገሩ ተዘግቧል። ከዛም በዋላ ንግግሩ ፍሬ አፍርቶ ማንችስተር ዩናይትድን ሩኒን በ 27 m ፖ አሰፈረመ። ገና በ18 አመቱ እንደ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፣ሪያን ጊግስ እና ፖል ስኮልስ ያሉ ኮከቦች ያካተተውን ቡድን ተቀላቀለ።
ሩኒ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩናይትድ ማልያ ያደረገው ጨዋታ የማይረሳ ነበር። በሴፕቴምበር 28 ቀን እ ኤ አ በ 2004 አ ም በቻምፒየንስ ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ ፌነርባቼን 6-2 ሲያሸንፍ ሀትሪክ መስራት ቻለ። ከዛም በኃለሠ በቲያትር ኦፍ ድሪምስ መድመቁን ተያያዘው።
ሜዳ ውስጥ ያለውን ከመስጠት ወደ ዋላ ማይለው ዋዛ በ 2007 ዓ ም አንድ አስደንጋጭ ነገር ተፈጠረ። ቀኑ ሚያዝያ 27 ነው ውድድሩ ደግሞ Champions League ማንቸስተር ዩናይትድ ሮማን 7-1 በድምር ውጤት 8–3 ባሸነፈበት ጨዋታ ሩኒ ከሮማው ተጫዋች ጋር በ ጭንቅላት ተጋጨ በግጭቱ ፊቱ ላይ ተመቶ ደም በደም ሆነ ነገር ግን ሩኒ ደንታም አልሰጠውም ትኩረቱ ጨዋታው ላይ አደረገ። ይህም ግጥሚያ የሩኒ ጥንካሬ የቡድኑን የትግል መንፈስ ጎልቶ አሳይቷል።
እንግሊዛዊው የሜዳ ደምሳሽ ዋይን ማርክ ሩኒ ከተወለደበት የሀገር ክለብ ሊቨርፑል ጋር ባደረጋቸው 27 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ሰባት ጎሎችን በማስቆጠር ሁለት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል። በጃንዋሪ 17 ቀን 2016 አ ም ሩኒ ማንቸስተር ዩናይትድ በአንፊልድ ሊቨርፑልን 1-0 ባሸነፈበት ጨዋታ ብቸኛዋን ጎል ለማን ዩናይትድ በማስቆጠር የሊቨርፑል ደጋፊዎችን በሜዳቸው አንገት አስደፍቷል።
ይህ ግብ ሩኒን በወቅቱ በፕሪምየር ሊግ ታሪክ ለአንድ ክለብ ብዙ ጎሎችን ያስቆጠረ ተጫዋች እንድትሆን አድርጎታል። ዋዛ በማንችስተር ዩናይትድ መልያ 253 ጎሎችን በማስቆጠር የማንቸስተር ዩናይትድ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው።
ኢቨርተን ጎልበቶ ማንችስተር ዩናይትድ ፋፍቶ ዲሲ ዩናይትድ እና ደርቢ ካውንቲም በመክተም የእግርኳስ ጊዜውን ያሳለፈው እግርኳስ ላይ የተዝናናው ድንቁ የቀድሞ ተጫዋች ዋይን ማርክ ሩኒን አስቃኘዋችሁ🙌
@ermias_ks (ek sport)
@Manchester_unitedfansz