Maraki News


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


Addisababa, Ethiopia🇪🇹
👇ማስታወቂያ ለማሰራት
@Adis_pro

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
☑️ @MarakiNews ☑️


በአዲስ አበባ በዛሬዉ እለት ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት በመለየት ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈታ ፕላኑን የጠበቀ ዘላቂ የመፍትሄ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው በዚህ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል::በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ህብረተሰቡ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል::

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ህብረተሰቡ ፈጥኖ እንዲያሳዉቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡
☑️ @MarakiNews ☑️


በራሳችሁ ስም እና ኢሜይል የሚከፈት ቪዛ ካርድ በቅናሽ እኛ ጋር አለ
✅ከውጪ እቃዎችን ለማዘዝ
✅ለፌስቡክ ቡስት
✅የዩንቨርስቲ ክፍያዎች
✅የቪዛ አፕልኬሽን ክፍያዎችን
✅የኦንላይን ኮርሶችን ክፍያዎች
ሁሉንም መክፈል ያስችላል

በተጨማሪም Telegram Premium መግዛት ለምትፈልጉ
    ⭐ 1 Month
    ⭐ 3 Month
    ⭐ 6 Month
    ⭐12 Month

📩 •➤ Contact @Adis_pro
0954190018


የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል።

" በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፤ " ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው " ብለዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል።
☑️ @MarakiNews ☑️


650ሺህ ብር የተጠራው ሰንጋ 🐂

ታላቁ የሆሳዕና ገበያ በዘንድሮው አመት ያልተጠበቁ ሪከርዶችን ይዞ ተከስቷል። ወጣት ሚጥዬ ታደለ በእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ነዋሪ ነው። ወጣቱ በከብት ማድለብ ስራ ከተሰማራ በርካታ አመታትን አስቆጥሯል።

በ2016 ዓ.ም በእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ያወጣል የተባለውን በጣዕሙ እና በአይነቱ ልዩ የሆውን የጅሩ ሰንጋ በሬ አድልቧል።

ወጣት ሚጥዬ በንግግሩ በዘንድሮው አመት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ሆነን ሁላችንም የጅሩ አርሶ አደሮች ጣዕም ያለውን ሰንጋ አድልበናል ጊዜውን ጠብቀንም ለገበያ አምጥተናል ሲል ለእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ሚዲያ ተናግሯል።

650ሺህ ብር የተጠራው የጅሩስ ሰንጋ ስንት ብር ይሸጥ ይሆን? እየተባለ ገዢዎችን እየጠበቀ ነው።
☑️ @MarakiNews ☑️


ይህንን ያውቃሉ ??

በመካከለኛው ዘመን ጀርመናውያን አንድ አስደናቂ እና አስገራሚ ልምምድ ነበራቸው ይሄም በወቅቱ በጥርስ ህመም የሚሰቃዩ ሰዎች ከጥርስ ህመም ለመፈወስ አህያ ይስሙ ነበር ምክንያቱም በጊዜው አህያን መሳም ለጥርስ ህመም እንደ መድሃኒት ይታመን ስለነበረ ነው እንደዛሬ ለምግብነት ሳትወል።
☑️ @MarakiNews ☑️


🌟 Join Our Team! 🌟

We are looking for individuals to join our Telegram channel as News Posters!

As a News Poster, you'll be responsible for sharing engaging content with our audience.

👉 Responsibilities:
- Post news updates regularly on our Telegram channel.
- Ensure content is engaging, relevant, and of high quality.
- Collaborate with the team to brainstorm and develop content ideas.
- Maintain consistency in posting schedule.

💼 What We Offer:
- Flexible working hours.
- Opportunity to work remotely.
- Competitive compensation.

To apply, simply send a message to @Adis_pro with a brief introduction and why you're interested in joining our team.
☑️ @MarakiNews ☑️


ኢትዮጵያ ፤ የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እቅድ እንዳላትና ለእርሱም እየሰራች ነዉ ተባለ

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታዘጋጅ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል።

የአፍሪካ ዋንጫን እ.ኤ.አ በ 2029 ወይም በ2031 ለማዘጋጀት እየሰራን ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለእቅዱ መሳካትም ቢያንስ ስድስት ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ካፍ ከዚህ በፊት ያልነበሩ አዳዲስ መስፈርቶችን በማስቀመጡ ኢትዮጵያ አንድም ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም እንዳይኖራት አድርጓል ሲሉም አቶ ቀጀላ መርዳሳ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ የካፍን ደረጃ የሚመጥኑ ስታዲየሞች የሌላት በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዘም ላሉ ጊዜያት ከሀገሩ ዉጪ ለመጫወት ተገድዶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

የዉድድሩ አዘጋጅ ሀገራት ቢያንስ ስድስት ስታዲየሞችን እንዲያዘጋጁ ካፍ ቢያዝም ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ምን ያህል ዝግጁ ናት የሚለዉ ግን አጠያያቂ ነዉ።
☑️ @MarakiNews ☑️


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
⭐️ ቤተሰብ ይሄ እድል እንዳያመልጣችሁ ከዚህ በፊት Not Coin Tab ስታደርጉ ያመለጣችሁ ሌላ አዲስ Tab የሚደረግ bot መቷል ይፍጠኑ በኋላ እንዳይቆጫችቹ ልክ እንደ Not Coin👇👇👇

https://t.me/tapswap_bot?start=r_985021045

👆ሊንኩን ተጭነው Start በማለት Play ብለው tap tap በማድርግ Coin ያጠራቅሙ

ጥያቄ ለመጠየቅ ግሩፑን Join ያርጉ⬇️
@Ethio_Tapswap


የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በባይት ዳንስ ባለቤትነት ያለው ቲክቶክ ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ ተሽጦ ከቻይና ካልተፋታ በመላው አሜሪካ እንዲታገድ የቀረበላቸው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሕግ ሆኖ  እንዲወጣ አድርገዋል።

ቲክቶክ ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ የተሰጠው ጊዜ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ብቻ ነው።

በዚህ ጊዜ ይህንን ካላደረገ እስከወዲያኛው ከአሜሪካ እንደሚታገድ ተገልጿል።
☑️ @MarakiNews ☑️


ምርትና አገልግሎቶን ያስተዋውቁ

ሚፈልጉትን በሳምንት : በ2 ሳምንት አልያም በ ወር መርጠው ያስተዋውቁ

✅• የምሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች
      
┣➤ የ ድርጅት ማስታወቂያ
┣➤ የቡቲክ ልብሶች ማስታወቂያ
┣➤ ትሪትመንቶች
┣➤ CONSULTANCY
┣➤ ሌሎችም ሽያጮች ማስታወቂያ

📌 አገልግሎት እና ምርቶን እንዲሁም ቻናሎን  በማስተዋወቅ አትራፊ እና ታዋቂ ይሁኑ !

ለማናገር👇
@Adis_pro / 0954190018


በአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ድንጋይ እና አፈር ተደርምሶ የ7 ሰዎች ሕይወት አፏል።

አደጋው የደረሰው በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ወረዳ 12 " ጠሮ መስጂድ " አካባቢ ነው።

ለሊት 11 ሰዓት ገደማ ለቤት ግንባታ የተከመረ ድንጋይ እና አፈር ከላይ ወደ ታች (ወደ ቤቱ) ተንዶ 3 ክፍል ያለው ቤት ላይ አደጋ ደርሷል።

በዚህም ቤት ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

ሟቾቹ ፦
የ4 ዓመት ህጻን ፣ ሶስት የ11 እና የ12 ዓመት ታዳጊዎች  ከ25 እስከ 30 ዓመት ያሉ 3 ወጣቶች ናቸው።

ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች የሁለት ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ ታውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ አደጋው የደረሰበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ምርመራ ላይ ነው።
☑️ @MarakiNews ☑️


ታዋቂው የቱርክ ተዋናይ ትምህርት ቤቱን ወደፍርስራሽነት ለውጦታል

ቻላር አርቱግሩል የተባለው ተዋናይ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቱን ገዝቶ ያወደመው ይገርፉኝ የነበሩ መምህራንን ለመበቀል ነው ብሏል።
☑️ @MarakiNews ☑️


የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ በየነ ተዘራ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በኦንላይን፣ በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

የሪሚዲያል ትምህርት ከታህሳስ ጀምሮ እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም መጨረሻ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ውጤታቸው 30 በመቶ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ሒደት እና 70 በመቶ በማዕከል በሚዘጋጅ ፈተና የሚለይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
☑️ @MarakiNews ☑️


ለሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት

ጉዳዩ፡- የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የአገልግሎት ክፍያን ስለማሳወቅ፤

በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ለሚስጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ ለማካሄድ ይረዳ ዘንድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን ዝርዝር እንድታሳውቁን መጋቢት 23/2016 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ መጠየቃችን ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የመውጫ ፈተናውን #ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎች ለሚያገኙት የአገልግሎት ክፍያ በአንድ ተማሪ 👉500.00 (አምስት መቶ) ብር ብቻ የሚከፍሉ መሆኑ ታውቆ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000553176097 እስከ ሚያዚያ 15/ 2016 ዓ. ም ድረስ ለትምህርት ሚኒስቴር ገቢ እንድታደርጉ እያሳወቅን የተከፈለበትን ደረሰኝ ኮፒ በኢሜይል አድራሻ (antedefar@gmail.com & lakbt2013@gmail.com) እንድትልኩልን እናሳስባለን።

ከት/ት ሚኒስቴር
☑️ @MarakiNews


የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21 ድረስ ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ በማሰባሰብ በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በኩል አረጋግጠው ባሳለፍነው ሳምንት ለትምህርት ሚኒስቴር መላካቸውን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
☑️ @MarakiNews ☑️


የመውጫ ፈተና አገልግሎት ክፍያ

ከኢ...ዲ.ሪ.ት/ሚ/ር በቁጥር 8/342/562/16 በቀን 09/08/2016 ዓ.ም በተፃፈው ደብዳቤ መሰረት ከሰኔ 14-212016 ዓ.ም ድረስ ለሚስጠው የመውጫ ፈተና አገልግሎት ክፍያን አስመልከቶ ተፈታኝ ተማሪዎች #እያንዳንዳቸው 500.00 /አመስት መቶ ብር/ እስከ ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም ድረስ እንዲከፍሉ አሳውቋል።

በዚሁ መሰረት በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ የዘንድሮ አመት ተመራቂ ተማሪዎች ክፍያውን ይከፍሉ ዘንድ ዩንቨርሲቲዎች እያሳሰቡ ይገኛል።
☑️ @MarakiNews ☑️


የ17 አመቷን የግል ተበዳይ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈጸም አንገቷን አንቆ የገደለው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

ከእኔ ጋር በፍቅር ጓደኝነት ለመቀጠል ፈቃደኛ አልሆነችም በሚል የ17 አመቷን የግል ተበዳይ አስገድዶ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈጸም ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገ ግለሰብ በጽኑ እስራት ተቀጣ።

አብዱ ኪያር ዩሱፍ የተባለው ተከሳሽ በጳጉሜን 01 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 6፡30 ሰዓት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ሰፈራ ቀርሳ ቢላ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የግት ተነዳይን አንገቷን አንቆ በመያዝ በአካባቢው ወደሚገኝ ካባ በሚወስዳት ጊዜ ላለመሄድ ስትታገለው ነበር።

ግለሰቡ የግል ተበዳይ ጩኸት ስታሰማ በድጋሚ በልብስ ማሰሪያው ጨርቅ አንገቷን አጥብቆ በመያዝና እራስዋን እንዳትከላከል በማድረግ የግብረ-ስጋ ግንኙነት የፈጸመባት እና አንገቷን በእጅ እና በልብስ የወገብ ማሰሪያ ጨርቅ በማነቅ ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል።

በዚህም ግለሱቡ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶበት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 11ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቶ በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ እንደሌለው በመግለጹ ፍርድ ቤቱ ለሰራው ወንጀል በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
☑️ @MarakiNews ☑️


12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ይፋ አድርጓል።

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁም ይታወሳል፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡

ከ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጋር በተያየዘ አዲስ ነገር ሲኖር በፍጥነት የምናሳውቅ ይሆናል።
☑️ @MarakiNews ☑️


የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በተከሰተ ከባድ የጎርፍ አደጋ 18 ሰዎች ሞቱ።

በተከሰተው ከባድ የጎርፍ አደጋ የ18 ሰው ህይወት መጥፋቱን ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል፡፡

የጣለው ከባድ ዝናብ በበረሃዋ ሀገር ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅን በማስከተሉ የዱባይ ዋና ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ሀገር ውስጥ የሚደረጉ በርካታ በረራዎችን አቅጣጫ ለመቀየር ተገዷል ነው የተባለው።

በቅርቡ የተ.መ.ድ COP28 የአየር ንብረት ጉባዔን ያስተናገደችው አረብ ኢሚሬትስ ከዚህ ቀደም የዓለም ሙቀት መጨመር ለበለጠ ጎርፍ ሊጋልጣት እንደሚችል ተተንብዮ ነበር።
☑️ @MarakiNews ☑️

Показано 20 последних публикаций.