በ #ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቀበሌያት በሚገኙ የሶዶ ጉራጌ ተወላጆች ላይ ባነጣጠረ የ''ሸኔ'' ጥቃት እስከ 40 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ‼️
ጥቃቱ የደረሰው በክልሉ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ጋር በሚዋሰንባቸው የዱግዳ ቦራ ወረዳ ቀበሌያት ነው።
በዚህም በዱግዳ ቦራ ወረዳ ቢርቢርሳና ጋሌ ተብለው በሚጠሩ ቀበሌያት ልዩ ስማቸው ደረባ፣ ኩሬ እንዲሁም ቢጢሲ ተብለው በሚታወቁ ስፍራዎች አሰቃቂ ጥቃት መድረሱ ተነግሯል።
በተለምዶ ''ሸኔ'' ተብሎ በሚጠራው ቡድን ታጣቂዎች አማካይነት እንደደረሰ በተገለፀው ጥቃት እስከ 40 ሰዎች መገደላቸውንና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን ከስፍራው የደረሱን ተደጋጋሚ መረጃዎች አመላክተዋል።
ጥቃቱ ከትላንት በስተያ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ገደማ ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት መራዘሙን የጠቆሙት የአካባቢው ነዋሪዎችና የሟቾች ቤተሰቦች በጥቃቱ ሕጻናትን ጨምሮ እናቶችና አረጋውያን መገደላቸውንም ተናግረዋል።
የተከፈተባቸውን ጥቃት መመከት ያልቻሉ አርሶ-አደሮች ቤታቸው ውስጥ እያሉ በእሳት እንዲቃጠሉ በማድረግ ከነከብቶቻቸው እንዲሞቱ መደረጉንም ነዋሪዎች ገልፀዋል(አዩዘሀበሻ)።።
👇👇👇👇👇👇👇👇⬇️
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s