Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
🌹ወር በገባ በ8 የቅዱስ አባ (ብሶይ) ብሾይ ወርኀዊ መታሰቢያያ በዓላቸው ነው።
#የገዳም ኮከብ ቅዱስ አባ ብሶይ በግብጽ ሼስና በተባለች ቦታ የተወለደ ሲኾን ሰባት ወንድሞች ነበሩት፤ ከዕለታት ባንዳቸው ለእናቱ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልሟ ተገልጾ “ጌታ ከልጆችሽ መኻከል አንዱን እንዲያገለግለኝ ስጪኝ ይልሻል አላት” ርሷም፤ “ጌታ የወደደውን ይውሰድ” ብላ መለሰችለት፤ መልአኩም ቀጭን የነበረውን ሰውነቱም ደካማ የነበረውን የብሶይን እጁን ይዞ “ዝንቱ ውእቱ ወልድ ለእግዚአብሔር ገባሬ ሠናይ” (ለእግዚአብሔር መልካም ሥራ የሚሠራ ይኽ ልጅ ነው” አለ፤ ያን ጊዜ እናቱ “የእኔ ጌታዬን እንዲያገለግለው ጠንካራውን ይውሰድ” በማለት ስትመልስ፤ መልአኩም “ጌታስ የመረጠው ይኽነን ነው” ብሎ መልሶላታል፡፡
ከዚያም በ340 ዓ.ም. ቅዱስ አባ ብሶይ ወደ ሲሐት በረሓ በመኼድ ቅዱስ ዮሐንስ.ሐጺርን ባመነኮሱት በአባ ባውማ እጅ ምንኲስናን ተቀበለ፡፡ አባ ባውማ ባረፈ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና አባ ብሶይ በጸለዩ ጊዜ መልአኩ ለአባ ብሶይ ተገልጾለት ወደ ገዳም መርቶ አድርሶታል፤ በዚያም ወደ ርሱ ለተሰበሰቡ ለብዙዎች መነኮሳት አባት ኾኗቸዋል፤ በቅድስና እጅግ የከበረ፤ በፍቅር፣ በደግነት፣ በርኅራኄ የሚታወቁ በተጋድሎም የበረታ ነበረና ዜናው በመታወቁ ቅዱስ ኤፍሬም ወደ አባ ብሶይ መጥቶ አይቶታል፡፡
ጌታችንን በእጅጉ ከመውደዱ የተነሣ ቅዱሳት መጻሕፍትን አዘውትሮ በማንበብ በመጻሕፍት ቃል ነፍሱን እያረካ፤ እጅግ ጽኑ የኾነ ተጋድሎን በማድረግ በጾም፣ በጸሎት ይጋደል ነበር፤ ሁሌም ርሱን ለማመስገን ከመሻቱም የተነሣ በምሽት ጸሎት ጊዜ እንቅልፍ እንዳይወስደው ጸጒሩን በገመድ በማሰር ይጸልይ ነበር፤ ዛሬ ድረስ ይኽ ማሰሪያ በዚያው ገዳም አለ፤ በዚኽም ንጽሐ ልቡና መኣርግ ላይ በመድረሱ ጌታችን ደጋግሞ ይገለጽለት ነበር፤ ከዕለታት ባንዳቸውም ጌታ በአምሳለ ነዳይ በእንግድነት ወደ በዓቱ በመጣ ጊዜ በእንግዳ ልማድ ውሃ አቅርቦ ለማጠብ ሲዠምር በምስማር የተወጉ እግሮቹን ዳስሶ በማየቱ ጌታችን እንደኾነ ዐውቋል፡፡ ርሱም በደስታ በመኾን ጌታን ያጠበበትን ውሃ ጠጥቶታል፡፡
ይኽነን ብቃቱን አይተው መነኰሳቱ ጌታችን እንዲገለጽላቸው ይለምንላቸው ዘንድ እጅጉን በዘበዘቡት ጊዜ ወደ ጌታችን አመለከተ፤ ጌታም በተራራው ላይ እንደሚገለጽ ነግሮት ለመነኰሳቱ ኹሉ ነገራቸው፤ እነርሱም በማለዳ ወደ ተራራው ጫፍ ሲገሰግሱ ከተራራው ሥር ጌታን በአምሳለ አረጋዊ ኾኖ በመገለጥ ይዘውት እንዲወጡ ቢጠይቃቸው አንዳቸውም በእንቢተኝነት ጸንተው ወደ ተራራው ይሮጡ ጀመር፡፡ በመጨረሻም አረጋዊዉ አባ ብሶይ ወደ ተራራው ሊወጣ ሲል በአምሳለ አረጋዊ የተገለጸው ጌታችን ዐዝሎት እንዲወጣ ጠየቀው፤ አባ ብሶይም በትሕትና በመኾን ታዝዞ ዐዝሎት ሲወጣ በእጅጉ ከበደው ቀስ እያለ ግን ቀለል ቀለል እያለው መምጣቱን ዐውቆ ጌታችን መኾኑን ተረድቶ ቀና ብሎ ቢያይ ዠርባው ላይ በፍቅር የታዘለው ርሱ ነው፤ ጌታም ስለ ትሕትናው ለርሱ እንደተገጠለት ነግሮት አባ ብሶይን ባርኮታል፤ በመኾኑም የባሕርይ አምላክ ክርስቶስን ያዘለበት የአባ ብሶይ ሰውነት ዛሬ ድረስ ሳይፈርስ ሳይበሰብስ ብዙ ተአምራትን እያደረገ በገዳሙ አለ፡፡
ቅዱስ አባ ብሶይ የመንፈስ ቅዱስን ህልውና ክዶ የነበረውን በበረሓ የነበረውን ሰው ስለ ነገረ መንፈስ ቅዱስ ከብሉይ ከሐዲስ በምሳሌ ጭምር በስፋት አስተምሮ እንዲመለስ አድርጓል፤ ቅዱስ አባ ብሶይም ብዙዎች ተጋድሎዎችን ካደረገ በኋላ ሐምሌ 8 በ417 ዓ.ም. በመዐዛ ገነት፣ በይባቤ መላእክት ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጥቷል፡፡
የቅዱሳኑ በረከት ከእኛ ጋር ትሁን፡፡
#መጋቤ_ሐዲስ_ሮዳስ_ታደሰ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc