"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


ዛሬ ጥር 28 ቅዱስ አማኑኤል ነው አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ምስሌነ /እግዚአብሔር ከእኛጋ ሆነ ማለት ነው እርሱ ከእኛ ጋር ባይሆን በከበበን መከራ እስካሁን በጠፋን ነበር። እኛን ለማጥፋት ዘወትር በሚተጋው ጥንተ ጠላታችን ከይሲ እስካሁን ጠፍተን ነበር።

ነገር ግን "እግዚአብሔር ምስሌነ" የሰራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ በመልካም ጥባቆትህ ጠብቀህ ለሊቱን በሰላም እንዳሳደርከን እንዲሁም ደግሞ መልካም ጥባቆትህ ሳይለየን ቀኑንም በሰላም ጠብቀህ ታውለን ዘንድ ያንተ መልካምና ቅዱስ ፍቃድ ይሁንልን አሜን በእውነት ቅዱስ አማኑኤል በቀኝ ያውለን ጥበቃው ማዳኑ አባትነት ጌትነቱ አይለየን🤲🌷


Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
መልክአ ቅዱስ አማኑኤል📗


በጨነቃችሁ በችግራችሁ ጊዜ ሁሉ ቅዱስ አማኑኤል አለሁ ይበላችሁ።

🥰🙏🥰

Orthodoxtewahdoc
ሼር ሼር ሼር🤍💫


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33☦📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ጥቅምት ፳፰/28

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊




ብረት ከእሳት እየተጨመረ እየተቀጠቀጠ እየተቀጠቀጠ የያዘውን ኣፈር እያራገፈ የበለጠ እየጠነከረ እየጠነከረ ይመጣና እየረዘመ እየሰፋ ይመጣል ፡፡መጨረሻ ላይ መቀጥቀጡ ሲያበቃ ከውሃ ይነከራል፡፡ክርስቲያንም በፈተናወች እየተፈተነ፣እየተገላታ፣እየተሰቃየ ይመጣና ከጥንካሬው ደረጃ ሲደርስ መንፈስ ቅዱስ ይዋሃደዋል።

🌷መልካም ሌሊት🤲🥰✝


በሰው የተከፈተልህ በር በሰው ይዘጋል
እግዚአብሔር የከፈተልንን በር ግን ማንም አይዘጋውም
ከምናስበው በላይ ለኛ የሚያስብልን እግዚአብሔር ስሙ ለዘለአለም የተመሰገነ ይሁን መልካምና የተባረከ ምሽት ይሁንላችሁ🙏

943 0 13 7 65

በጨነቃችሁ በችግራችሁ ጊዜ ሁሉ ቅዱስ አማኑኤል አለሁ ይበላችሁ።

🥰🙏🥰


Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
♨ወር በገባ በ28 ቅዱስ አማኑኤል ነው እንኳን አደረሰን🌹

📌#ኦ_ቅዱስ_አማኑኤል ጌታዬ ሆይ ልቤ ላይ ዳናውን የተወው ለቅሶዬ መከፋቴን ይነግርኃልና ስማው፤ ስለ ሥጋ መኖርን አላስተማርከኝምና ስለ ሥጋ አላውራ፤ ማንም ያሻው ሁሉ በትልቅ እመጫት የሚያስገባብኝ አልሁን፤ ተሸራርፈው እያለቁ ነገር ግን ጡረታ እንዳልወጡ ባሊዎች አሊያ ሁሉም ወሬ ሲከካባቸው ከንፈራቸውን የሸራረፈባቸው በቡና የወየቡ ሲኒዎች ሆኜብሃለውና ከኃጥያትና ከሰው የሐሜት ዝተት አሳርፈኝ፤ ክዳናቸው የራሳቸው እንዳልሆነ ጀበኖች በትንሽ እሣት እንደሚገነፍሉ እኔም በሞትህ ክብር ባከበርከው ክቡር ሕይወቴ ላይ ክዳኔ ባልሆነው በዓለም ምቾት ተተብትቤ በትንሽ መከራ ተፈቅፍቄብሃለውና ውለታህን ከፊቴ ሳልልኝ❣🙏

አሜን በእውነት

ቤተሰብ ይሁኑ https://t.me/Orthodoxtewahdoc




Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
📕 #ቅዱሳን አባድር እና #እኅቱ ኢራኒ 🌹🙇

📌•••ወር በገባ በ 28 የቅዱሳን #አባድር_እና_እኅቱ_ኢራኒ ወርኅዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው  ሰማዕታቱ ቅዱስ አባድርና እኅቱ ቅድስት ኢራኒ፡- እነዚህም ሰማዕታት የመንግሥት ወገን የሆኑ የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ፋሲለደስ የእኅቱ ልጆች ናቸው፡፡
📌••••አባድር በአባቱ መንግሥት የሠራዊት አለቃ ቢሆንም እርሱ ግን በድብቅ ሌሊት በጸሎት ሲተጋ ያድራል፡፡ አንድ ሌሊት ጌታችን ተገልጦለት ‹‹የሰማዕትነት አክሊልን ትቀበል ዘንድ እኅትህ ኢራኒን ይዘህ ወደ ግብፅ አገር ሂድ፡፡

=> ስለ ሥጋችሁም እንዲያስብ ሳሙኤል የሚባለውን ሰው እኔ አዘዋለሁ›› ካለው በኋላ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
ጌታችን ለቅዱስ አባድር በስሙ ሰማዕት እንዲሆንና ለዚህም ወደ ግብፅ ሄዶ ክብሩን በከሃድያን ነገሥታት ፊት እንዲመሰክር ከነገረው በኋላ እንዲሁ ጌታችን አሁንም ለእኅቱ ኢራኒ ተለተልጦት ‹‹የወንድምሽን ቃሉን ስሚው፣ ትእዛዙንም አትተላለፊ›› በማለት እርሷም ከወንድሟ ጋር አብራ ሰማዕት እንድትሆን ነገራት፡፡ ኢራኒም ጌታችን ተገልጦላት የነገራትን ነገር ለወንድሟ አባድር ሄዳ ነገረችውና እጅግ ደስ አላቸው፡፡

=> ክብር ይግባውና ስለጌታችን ቅዱስ ስሙ ብለው ደማቸውን አፍስሰው ሰማዕት ይኑ ዘንድ በአንድ ሀሳብ በቁርጥ ኅሊና ተስማሙ፡፡ የአባድር እናቱ ልጇ ሰማዕት ይሆን ዘንድ መዘጋጀቱን ስትሰማ ከንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ ጋር እንዳይጣላ ትማፀነው ጀመር፡፡ ወደሌላ አገር ሄዶ በሰማዕትነት እንደሚሞት ግን አላወቀችም ነበር፡፡

=> ከዚህም በኋላ ቅዱስ አባድር ራሱንም ሳይገልጥ በድብቅ ልብሱን ቀይሮ በመውጣት ለእስረኞች ውኃ እየቀዳ እግራቸውን ያጥባቸዋል፡፡ እስከሚነጋም ድረስ እንዲሁ ያደርጋል፡፡ በር የሚጠብቀውንም ሰው ‹‹ይህን ለማንም አትናገር፣ ነገር ግን ይህንን ሥራ ብትገልጥ እኔ ራስህን በሰይፍ እቆርጣለሁ›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አባድር እኅቱን ቅዱስት ኢራኒን ይዞ ወደ ግብፅ ሄዶ እስክንድርያ ደረሰ፡፡ በዚያም ያሉ ወታደሮች አባድርን ዐውቀውት ‹‹አንተ የሠራዊት አለቃ ጌታችን አባድር አይዴለህም እንዴ?›› አሉት፡፡

=>  ነገር ግን አባድር ፈገግ ብሎ ‹‹ብዙዎች እንዲሁ ይሉኛል እኔ ግን እመስለው ይሆናል እንጂ እርሱን አይደለሁም›› አላቸው፡፡ ከዚያም ወደሌላ ቦታ ሄደ፡፡ በዚያም ያሉት ጭፍሮች እንዲሁ ማንነቱን ማለትም በአባቱ መንግሥት የሠራዊት አለቃ መሆኑን ቢያውቁትም እርሱ ግን ‹‹በመልክ ተመሳስለን ነው እንጂ እኔ አይደለሁም›› አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ከእስክንድርያ ከተማ ወጥቶ ወደታላቋ ምስር አገር ሄደ፡፡

=> በምስር አገርም ከአባ አበከረዙን ጋር ተገናኝተው አባድርና እኅቱ ከእርሱ ቡራኬን ተቀበሉ፡፡ ከዚያም ወደ እስሙናይን ደርሰው ከዲያቆን ሳሙኤል ጋር ተገናኙ፡፡ በማግስቱም ወደ እንጽና ከተማ ሄደው በከሃዲው መኮንን በአርያኖስ ፊት የጌታችንን ክብር መሰከሩ፡፡ መኮንኑም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸው፡፡ ሁለቱም በጽኑ ሥቃይም ውስጥ ሳሉ ጌታችን ነፍሳቸውን ነጥቆ ወስዶ የሰማዕታትን መኖሪያ የብርሃን ቤቶችን አሳይቷቸው አጸናቸውና ወደ ሥጋቸው መለሳቸው፡፡

=> አርያኖስም በመጨረሻ ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ አንገታቸውን እንዲቆርጧቸው አዘዘ፡፡ አንገታቸውንም ከመቆረጣቸው በፊት አርያኖስ ቅዱስ አባድርን ‹‹በአምላክህ አማጽኜሃለሁ ማንነትህን ንገረኝ?›› አለው፡፡ አባድርም መኮንኑን ‹‹ማንነቴን በነገርኩህ ጊዜ ራሳችንን እንዲቆርጡ ያዘዝከውን ትእዛዝ እንዳትለውጥ አንተም ማልልኝ›› አለው፡፡ አርያኖስንም ትእዛዙን እንዳይሽር ካስማለው በኋላ ቅዱስ አባድር ‹‹የሠራዊት አለቃ እኔ አባድር ነኝ›› በማለት ማንነቱን ነገረው፡፡

=> መኮንኑ አርያኖስም በዚህ ጊዜ ‹‹ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ ጌታዬ ሆይ በአንተ ፈንታ እኔ ልሞት ይገባኛል፣ ይህን ሁሉ ጽኑ ሥቃይ እስከአሠቃየሁህ ድረስ አንተ ጌታዬ እንደሆንክ እንዴት አላስረዳኸኝም›› እያለ አለቀሰ፡፡ ቅዱስ አባድርም ‹‹በመጨረሻ አንተም እንደእኔ በሰማዕትነት ትሞት ዘንድ አለህና አትዘን አሁን ግን የእኔንና የእኅቴን ሰማዕትነታችንን በፍጥነት ፈጽምልን›› አለው፡፡ መኮንኑም የቅዱስ አባድርን ፈቃዱን ይፈጽምለት ዘንድ የአባድርንና የእኅቱን አንገት በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ፡፡ በሰይፍም ራስ ራሶቻቸውን ቆረጧቸውና የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ሆነ፡፡

=>  በተአምራቶቻቸው ያሳመኗቸው 3,685 ማኅበርተኞቻቸውም እንዲሁ በጌታችን አምነው ተሰይፈው የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጅተዋል፡፡
  ጌታችን አስቀድሞ ለቅዱስ አባድር ‹‹ስለ ሥጋችሁም እንዲያስብ ሳሙኤል የሚባለውን ሰው እኔ አዘዋለሁ›› ብሎ እንደነገረው አሁን እነ አባድር ካረፉ በኋላ ዲያቆን ሳሙኤል የተባለው አገልጋይ የመከራው ዘመን እስኪያልፍ ድረስ ቅዱስ ሥጋቸውን ወደ ቤቱ ወስዶ በክብር አኖረው፡፡

=> በኋላም ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ቅዱስ ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ፡፡ ከሥጋቸውም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ብዙ አስገራሚ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡ 
የሰማዕታቱ የቅዱስ አባድርና የእኅቱ ቅድስት ኢራኒ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን

!ቤተሰብ ይሁኑ https://t.me/Orthodoxtewahdoc




Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
††† እንኳን ለጻድቁ አቡነ ይምዓታ እና ለአበው ቅዱሳን መርትያኖስ ወመርቆሬዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ ይምዓታ ጻድቅ †††

††† ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አባ ይምዓታ ከዘጠኙ (ተስዓቱ) ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::

ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር:-
1.የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ::
2.ዓላማ (የእግዚአብሔር መንግስት) እና
3.ገዳማዊ ሕይወት ነው::

አባ ይምዓታን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::

በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት 5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::

በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ470ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::

ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ "ቤተ ቀጢን" ትባላለች::
አባ ይምዓታና 8ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር::

ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ ይምዓታ እንደ ገና አቀጣጠሉት::

ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት:: የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ::

ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ ይምዓታ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማሕበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::

የነ አባ ይምዓታ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ::
*ዸንጠሌዎን በጾማዕት::
*ገሪማ በመደራ::
*ሊቃኖስ በቆናጽል::
*አረጋዊ በዳሞ::
*ጽሕማ በጸድያ::
*ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::
*አባ ይምዓታ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ምርጫቸው ገርዓልታ (እዛው ትግራይ) ሆነ::

ጻድቁ ወደ ቦታው ሲሔዱ ወንዝ (ባሕር) ተከፍሎላቸዋል:: ወደ ቦታው ደርሰውም ገዳም አንጸዋል:: በቦታውም ብዙ ተአምራትን ሠርተው በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፍርተዋል:: የአቡነ ይምዓታ ገዳም ገርዓልታ (በፎቶው ላይ እንደምናየው) እጅግ ድንቅና ማራኪ ነው::

ነገር ግን እዛው ድረስ ሒዶ ለማየት ብርታትን ይጠይቃል:: በተራሮች መካከል ከመቀመጡ ባሻገር የአባቶቻችንን ጽናት የሚያሳይ ድንቅ ቦታ ነው:: ጻድቁ በዚሁ በፎቶው ላይ በምናየው ገዳም ለዘመናት ተጋድለው በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

††† ቅዱሳን መርትያኖስና መርቆሬዎስ †††

††† እነዚህ ቅዱሳን የቁስጥንጥንያ ሰዎች ሲሆኑ የወቅቱ ፓትርያርክ አባ ዻውሎስም ደቀ መዛሙርት ናቸው:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ በአርዮሳውያን ምክንያት ስደት በሆነ ጊዜ አባ ዻውሎስ: ቅዱስ አትናቴዎስ: ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስና ቅዱስ ሊዋርዮስ ከመንበራቸው ተፈናቀሉ::

በስደቱ ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ሲያርፍ ቅዱሳኑ አትናቴዎስና ሊዋርዮስ ተመለሱ:: አባ ዻውሎስን ግን በእሥር ቤት ውስጥ ሳለ በንጉሡ ትዕዛዝ አርዮሳውያን አንቀው ገደሉት:: ይህንን ያወቁት 2ቱ ደቀ መዛሙርቱ (መርቆሬዎስና መርትያኖስ) ቅዱስ አባታቸውን ቀብረው ንጉሡን ረገሙት::

አርዮሳዊው ታናሹ ቆስጠንጢኖስም ይህንን በሰማ ጊዜ 2ቱንም አስመጥቶ በአደባባይ በሰይፍ አስመታቸው:: ይህ ከተከናወነ ከ50 ዓመታት በሁዋላም ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ሆኖ በመምጣቱ ሥጋቸውን አፈለሠ:: ቤተ ክርስቲያንንም አንጾ ቀድሶላቸዋል::

††† አምላከ አበው ቅዱሳን በምልጃቸው ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ጥቅምት 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ ይምዓታ ጻድቅ (ከተስዓቱ ቅዱሳን)
2.ቅዱሳን መርትያኖስ ወመርቆሬዎስ (ሰማዕታት)
3.አባታችን ያፌት (የኖኅ ልጅ)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
4.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)
6.ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ

††† "በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኩዋ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ: አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት::" †††
(1ዼጥ.3:13)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

https://t.me/zikirekdusn




ወር በገባ 28 አባታችን ቅዱስ አማኑኤል ነው ።

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውረን።🙏❤


ሰማይን የዘረጋ መሬትን ያጸና /፪/
ኃያል ጌታ ሕያው አምላክ ያለ እርሱ ማን አለና /፪/

🌷እግዚአብሔር ይመስገን🤲


🌿ቸርነትህ ብዙ🌿

ቸርነትህ ብዙ ምሕረትህ ብዙ
በጉዟችን እርዳን ጠባብ ነው መንገዱ
ድንቅ ነው አምላክ ሆይ ፍቅርህ ለእኛ
ድንቅ ነዉ ለእኛ አንተ ነህ መልካም እረኛ

አስራኤል ወደቀ እስራኤል ተነሳ (፪)
መንገዱ አልቀናውም አምላኩን ቢረሳ(፪)
የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔርን ይዞ(፪)
ምን እንዳተረፈ አውቆታል በጉዞ (፪)
          አዝ...#
መንገዱ አይታክትም ጎዳናዉ የቀና (፪)
እግዚአብሔር በፊትም ከኋላሞ አለና (፪)
እርሱ በሌለበት ቢመችም መንገዱ(፪)
አቅጣጫው ወደ ሞት አይቀርም መውሰዱ (፪)
        አዝ...
በመንገዱ ዝለን ወድቀን መች ቀርተናል (፪)
የያዕቆብ አምላክ ደግፎ አንስቶናል(፪)
እግዚአብሔር ሲጠራን በቀደመው መንገድ (፪)
ጉዞአችን ወዴት ነው በሞት ለመወሰድ (፪)
          አዝ...
አምላክ ሆይ ፍቅርህን በልባችን ሳለው (፪)
እስከሞት በመስቀል የወደደን ማነው (፪)
በበረሃዉ ጽናት ሲጸናብን ርሀቡ (፪)
በረከት ሞላኸን ተረፈልን ምግቡ(፪)

                መዝሙር
        በዘማሪ አሸናፊ ተሾመ🥰


#መድኃኔዓለም

፩. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርጋታው የተነሣ "የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጧፍ ክርም አያጠፋም" ተብሏል (ማቴ.12፥20)። የእርጋታ መምህር ነው።

፪. የትሕትና መምህር ነው።"ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ" እንዲል (ማቴ.11፥29)።

፫. የይቅርታ መምህር ነው። በመስቀል ተሰቅሎ ይቅርታን ለሰው ልጅ ያደለ እርሱ ነው። "ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ" እንዲል (ሉቃ.23፥34)።

፬. የሰላም፣ የፍቅር፣ የትዕግሥት፣ የሰማዕትነት በጠቅላላው የመልካም ሥራዎች ሁሉ መምህር እርሱ ነው። እርሱን ሁልጊዜ ማሰብ ለነፍስ ዕረፍት ነው። እኛም ዋና አብነታችን እርሱ ስለሆነ መልካም ሥራዎችን ሁሉ አባታችንን እርሱን መስለን እንሥራ።

        ✝እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን👏


"አልብየ ኃይል ለተናግሮ"
"ይህን ለመናገር አቅም የለኝም"
እንዲል አረጋዊ መንፈሳዊ

ስወድቅ ትደግፈኛለህ ስደክም ታበረታኛለህ በቃው ሲባል ኧረ ገና የምትል የእንደገና አምላክ ነህና ያደረግልኝን የባረከኝን ለመናገር ቃል የለኝም

ተሸሽጎ የሚያለቅሰውን የምታይ መንገድ ለጠፋው መንገዱን እውነት ለራቀው እውነቱ
ላሰጣጥህ መስፈሪያ የሌለህ...ሳትሰማ የማትበይን! ደግሞ ምን ፈለግሽ?ብለህ የማትሰለቸኝ ቸሩ መድኃኔዓለም ክብር ምስጋና ይግባህ ተመስገን 🤲🌹

አቅሜ አንተ ስለሆንክ መድኃኔዓለም አባቴ ምስጋና ይግባህ ለደቂቃ እንኳን አትለየኝም እና አብዝቼ አመሰግንሃለሁ እንኳን አደረሰን።
🌸🌺🌸


Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
🌷መልክአ ቸሩ መድኃኔዓለም📗

በሕይወታችን በኑሯችን የጎደለውን ኹሉ የዓለሙ ቤዛ ቸሩ መድኃኔዓለም ይሙላልን አሜን በእውነት🤲

@Orthodoxtewahdoc


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33☦📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ጥር ፳፯/27

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊

Показано 20 последних публикаций.