Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
♨ወር በገባ በ16 የቅዱስ አቡናፍር ወርኃዊ በዓሉ ነው ።🌹
#ገዳማዊ አቡነ አቡናፍር 🎚+
❖ ይኸውም ቅዱስ አቡናፍር ጥቂት የሰሌን ፍሬዎችን ብቻ እየተመገበ በበረሃ ውስጥ 60 ዓመት የኖረ ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡
❖ በእነዚህ ድፍን 60 ዓመታት ውስጥ ከቶ የሰውን ፊት አላየም፤ ዛሬ ከምስር ከተማ ውጪ የተሠራች ቤተክርስቲያኑ የከበረችበት ዕለት ነው፡፡
❖ አቡነ አቡናፍር መልካም ሽምግልና ያለው ስም አጠራሩ የከበረ በገዳም የሚኖርና በገድል የተጠመደ አባት ነው፤ ከላይኛውግብፅ የተገኘ ሲሆን ታሪኩን የተናገረለት ጻዲቁ አባ በፍኑትዮስ ነው፡፡
❖ ይኸውም አባ በፍኑትዮስ ወደ በረሃ ውስጥ በገባ ጊዜ አንዲት የውኃ ምንጭና አንዲት የሰሌን ምንጣፍ አግኝቶ በዚያ እየተጋደለ ብዙ ዘመን የኖረ ነው፡፡
❖ በአንዲት ዕለት አባ በፍኑትዮስ ወደ እርሱ ሲመጣ አባ አቡናፍር አየው፤ አባ በፍኑትዮስም የሰይጣንን ምትሐት የሚያይ መስሎት ደነገጠ፡፡
❖ አባ አቡናፍር ፀጉሩና ጽሕሙ ሰውነቱን ሁሉ ሸፍኖታል እንጂ በላዩ ላይ ልብስ አልነበረውም፤ አባ በፍኑትዮስንም በመስቀል ምልክት ባርኮ አጽናናው፡፡
❖ አቡነ ዘበሰማያትንም ከጸለየ በኋላ ‹‹አባ በፍኑትዮስ ሆይ ወደዚህ መምጣትህ መልካም ነው›› ብሎ በስሙ ከጠራው በኋላ ፍርሃቱን አራቀለት፡፡
❖ ከዚህም በኋላ ሁለቱም በጋራ ጸልየው የእግዚአብሔርን ገናናነት እየተነጋገሩ ተቀመጡ፤ አባ በፍኑትዮስም አኗኗሩንና እንዴት ወደዚህ በረሃ እንደመጣ ታሪኩን ይነግረው ዘንድ አባ አቡናፍርን ለመነው፡፡
✍‹እኔ ደጋጎች እውነተኞች መነኮሳት በሚኖሩበት ገዳም ውስጥ እኖር ነበር፤ የገዳማውያንን ልዕልናቸውን ሲናገሩ ሲያመሰግኗቸውም ሰማሁ፤ እኔም ‹ከእናንተ የሚሻሉ አሉን› ብዬ ጠየኳቸው፡፡
❖ እነርሱም ‹አዎን እነርሱ በበረሃ የሚኖሩ በእግዚአብሔር ዘንድ የከበሩ ናቸው፤ እኛ ለዓለም የቀረብን ስለሆንን ብንተክዝና ብናዝን የሚያረጋጋን እናገኛለን ብንታመም የሚጠይቀንና የፈለግነውን ሁሉ እናገኛለን፣ በበረሃ የሚኖሩ ግን ከዚህ ሁሉ የራቁ ናቸው› አሉኝ፤ ይህንንም ስሰማ ልቤ እንደ እሳት ነደደና ወደ ፈቀደው መንገድ ይመራኝ ዘንድ በእኩለ ሌሊት ተነሥቼ ጸለይኩ፡፡
❖ ከዚህም በኋላ ተነሥቼ ወጥቼ ስጓዝ አንድ አባት አገኘሁና የገዳማውያንን ገድላቸውን እያስተማረኝ ከእርሱ ጋር ተቀመጥኩኝ፡፡
ያዘጋጀልኝን ይህችን ሰሌን አገኘኋት፤ በየዓመቱ 12 ዘለላ ታፈራለች፤ ለየወሩም የምመገበው አንዱ ዘለላ ይበቃኛል ውኃም ከዚህች ምንጭ እጠጣለሁ፡፡
❖ በዚህችም በረሃ እስከዛሬ 60 ዓመት ኖርኩ፤ ከአንተም በቀር የሰው ፊት ከቶ አይቼ አላውቅም›› ብሎ አቡነ አቡናፍር ጣፋጭ ታሪኩን በዝርዝር ነገረው፡፡
❖ ይህንንም ሲነጋገሩ የታዘዘ መልአክ መጥቶ የጌታችንን ሥጋና ደም አምጥቶ አቆረባቸው፤ ቀጥለውም ጥቂት የሰሌን ፍሬ ተመገቡ፤ ወዲያውም የአቡነ አቡናፍር መልኩ ተለወጠ፤ እንደ እሳትም ሆነ፤ ወደ እግዚአብሔርም በተመስጦ እየጸለየ ሳለ ቅድስት ነፍሱ ከሥጋው ተለየች፤ አቡነ በፍኑትዮስም በፀጉር ልብሱ በክብር ገንዞ ቀበረው፡፡
❖ ከዚህም በኋላ አባ በፍኑትዮስ በዚያች ቦታ ይኖር ዘንድ ወደደ ነገር ግን ያቺ የሰሌን ዛፍ ወደቀች፤ የውኃዋም ምንጭ ደረቀች፡፡
በረከታቸው ረድኤታቸው ይደርብን፤ በጸሎታቸው ይማረን
አርኬ
✍️ሰላም ለቅዳሴ ቤትከ በአፍኣ ሀገር ዘምስር። እንተ ሐነፅዋ ኬነውት ወጠበብተ ምክር። አቡናፍር አቡየ ሠውረኒ አመ ዕለተ ፍዳ ወፃዕር። በዘከደነከ እምሐሩር ወቊር። እምነ ርእስከ ወጽሕምከ ዘወረደ ጸጒር።
https://t.me/Orthodoxtewahdoc