በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና #በድጋሜ የምትወስዱ ተፈታኞች ምዝገባ እስከ ግንቦት 25/2016 ዓ.ም መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
በዚህም፦
➧ በሰኔ 2015 ዓ.ም እና በየካቲት 2016 ዓ.ም ተፈትናችሁ የነበረና አሁን በድጋሜ ለመፈተን ማመልከት ለምትፈልጉ እንዲሁም
➧ ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት የሕግ መውጫ ፈተና ወስዳችሁ የማለፍያ ነጥብ ያላገኛችሁና አሁን በድጋሜ ለመውሰድ የምትፈልጉና ስም ዝርዝራችሁ ከቀድሞው ዩኒቨርስቲያችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላችሁ አመልካቾች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ምዝገባ እንድታጠናቅቁ ተብሏል፡፡
ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ውጭ የሚቀርቡ የምዝገባ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
በሰኔ 2015 ዓ.ም እና በየካቲት 2016 ዓ.ም ተፈተናችሁ የማለፊያ ውጤት ያልመጣላችሁ አሁን በድጋሜ መፈተን ለምትፈልጉ አመልካቾች የሚጠበቅባችሁን የአገልግሎት ክፍያ በቴሌብር ብቻ የምትፈጽሙ ይሆናል፡፡
ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት ለሕግ መውጫ ፈተና ተቀምጣችሁ በድጋሜ ለመፈተን የምትፈልጉ አመልካቾች ስም ዝርዝራችሁ ከቀድሞ ዩኒቨርሲቲያችሁ መላኩን በማረጋጥ የሚጠበቅባችሁን የአገልግሎት ክፍያ ለዚሁ ጉዳይ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000553176097 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በግልፅ በሚታይ ስካን ኮፒ በማድረግ በ seneexit2016@gmail.com ኢሜል አድራሻ እንድትልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
@tikvahuniversity