የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዳግም ምዝገባ እንዲያካሒዱ ጥሪ ቀርቦላቸው ምዝገባ ባላካሔዱ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ ወስዷል፡፡
የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ዳግም ምዝገባ በማድረግ የተጓደለ መረጃ እንዲያሟ እንዲሁም የተሳሳተ ሰነድ ካላቸው እንዲያስተካክሉ ዕድል ተሰጥቷቸው እንደነበር የባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ማርታ አድማሱ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።
ዳግም ምዝገባ እንዲያደርጉ ጥሪ ከቀረበላቸው 102 ተቋማት ውስጥ 84 የሚሆኑት ዳግም ምዝገባ አለማድረጋቸውን የገለፁት ኃላፊዋ፤ ምዝገባ ያላከናወነ ተቋም በራሱ ፈቃድ ከመማር ማስተማር ሥራው እንደወጣ ይቆጠራል ብለዋል።
እነዚህ ተቋማት ከመማር ማስተማር ሥራው ሲወጡ የመውጫ ፎርም እንዲሞሉ የሁለት ሳምንት ጊዜ ገደብ እንደተሰጣቸው ኃላፊዋ አስታውሰው፤ አሁን ላይ አምስት ተቋማት ብቻ ይህንን ሒደት መጀመራቸውን አንስተዋል፡፡ ወደዚህ ሥራ ያልገቡ ቀሪ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፍታብሔር እና በወንጀል ህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡ #FMC
@tikvahuniversity