የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ውጤት #እንዳልደረሳቸው የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር ገለፀ፡፡
የመውጫ ፈተና ውጤት ለኮሌጆች እንደተላከ ትናንት የተገለፀ ቢሆንም፤ የተፈታኞች ውጤት እስካሁን ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አለመድረሱን የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር #ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።
የተማሪዎች ውጤት ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አለመላኩን ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከተለያዩ የግል ትምህርት ተቋማቱ ማረጋገጣቸውን የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ተፈራ ገበየሁ ገልፀዋል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር መነጋገራቸውን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ፤ "ቴክኒካል የሆኑ ነገሮችን ጨርሰን እንልካለን" መባላቸውን ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም ውጤቱ ተጠናቅሮ ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ እስከሚላክ ድረስ የግል ተፈታኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ሥራ አስኪያጁ ጠይቀዋል፡፡
[ይህ ዘገባ የቲክቫህ ዩንቨርሲቲ ነው]
ትምህርት ሚኒስቴር
ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️
https://t.me/Tmhrt_Minister