ቤንዚን ?
በአዲስ አበባ ቤንዚን ረጅም ሰዓት ሰልፍ ሳይሰለፉ ማግኘት ዘበት ከሆነ ሰነባብቷል።
ባለፉት ሳምንታት በትንሽ በትንሹ የጀመረው የቤንዚን ሰልፍ ከሰሞኑን እጅግ ብሶበታል።
በአንዳንድ ማደያዎች " ቤንዚን የለም " እየተባለ ሲለጠፍ ቤንዚን ያለባቸው ማደያዎች እጅግ በጣም ረጅም ሰልፍ ነው ያለው።
በዚህም ምክንያት የመኪና አሽከርካሪዎች ቀናቸውን በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ይገኛሉ።
በሜትር ታክሲ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ዜጎችም ስራቸውን በአግባቡ ለመስራት ተቸግረዋል። ቀናቸውን ሁሉ በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ናቸው።
በክልል ከተሞችም የቤንዚን ነገር ብሶበታል።
ቀድሞውንም ቤንዚን በማደያ እንደልብ በማንኛውም ሰዓት ማግኘት የማይቻልባቸው የክልል ከተሞች አሁንም ችግሩ እንዳለ ነው።
በክልል ከተሞች አሽከርካሪዎች ቤንዚን በማደያ " የለም " የሚባሉ ሲሆን በጀርባ ግን በየቦታው በህገወጥ መንገድ በጥቁር ገበያ ቤንዚን ሲቸበቸብ ይታያል።
ይህ ህዝብን እያማረረ ያለው የጥቁር ገበያ የነዳጅ ሰንሰለት መቼ እንደሚበጠስ አይታወቅም። ከዚህ ጀርባ እጃቸው የረዘመ አካላት መኖራቸውን ግን አሽከርካሪዎች ይናገራሉ።
ቤንዚን በክልል ከተሞች ከማደያ ውጭ በእጥፍ ዋጋ ነው የሚቸበቸበው።
@EBS_TV_NEWS