ኢትዮ ዜና ስፖርት🔴


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Спорт


ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!
➮የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች
➮የአፍሪካ መረጃዎችን በሙሉ
➮የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሙሉ መረጃ
➮ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዳሰሳዎች
➮ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታዲየሙ
Contact us @EEMET3
@Ethiosportnews_bot
@ethiosportnews_diskbot

ኢትዮ ዜና ስፖርት 2016 ዓ/ም

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Спорт
Статистика
Фильтр публикаций


የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

2:45 ብሬስቶይስ ከ ፒኤስጂ

5:00 ማንችስተር ሲቲ ከ ሪያል ማድሪድ

5:00 ጁቬንቱስ ከ ፒኤስቪ

5:00 ስፖርቲንግ ሊስበን ከ ቦርስያ ዶርትመንድ


“ አሞሪም ስኬታማ ያደርገናል “ ሪያን ጊግስ

የቀድሞ የቀያይ ሴጣኖቹ ተጨዋች ሪያን ጊግስ በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ላይ ትልቅ አምነት እንዳለው ተናግሯል።

“ ማንችስተር ዩናይትድ በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ ነው ነገርግን ከሁሉም በላይ አሰልጣኙን በጣም አደንቀዋለሁ “ ሲል ሪያን ጊግስ ተናግሯል።

ሪያን ጊግስ አክሎም “ ሩበን አሞሪም እደሉ እና በቂ ጊዜ ከተሰጠው ክለቡን በድጋሜ ስኬታማ ያደርገዋል “ ሲል ተደምጧል።


https://t.me/Ethioallball


ሲቲ የተጫዋቹን ግልጋሎት ያገኛል ?

ማንችስተር ሲቲ በነገው የሪያል ማድሪድ ተጠባቂ ጨዋታ የኒኮ ጎንዛሌዝን ግልጋሎት ሊያገኝ እንደሚችል አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

ፔፕ ጋርዲዮላ የወሳኝ ተጨዋቻቸው የሮድሪን ክፍተት ለመሙላት አልመው ያስፈረሙት ኒኮ ጎንዛሌዝ ከቀናት በፊት በኤፌ ካፕ ጨዋታ መጎዳቱ አይዘነጋም።

ለነገው ጨዋታ እንደሚደርስ “ ተስፋ አለኝ “ ሲሉ የገለፁት ፔፕ ጋርዲዮላ ሁለት ቀናት አሉን የሚሆነውን እንመለከታለን በማለት ተናግረዋል::


https://t.me/Ethioallball


35 '

ፕሌይ ማውዝ 0 - 0 ሊቨርፑል ( ኤፌ ካፕ)


የጨዋታ አሰላለፍ !

12:00 ፕሌይ ማውዝ ከ ሊቨርፑል



https://t.me/Ethioallball


ሌዊስ ስኬሊ ወደ እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ወጣት የመስመር ተጨዋች ሌዊስ ስኬሊ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ሊቀርብለት መሆኑ ተገልጿል።

አዲሱ የሶስቱ አናብስት ዋና አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ሌዊስ ስኬሊን በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑ ተነግሯል።

የ 18ዓመቱ ተጨዋች ሌዊስ ስኬሊ በሚቀጥለው መጋቢት ወር ለመጀመሪያ ጊዜ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ሊቀርብለት እንደሚችል ተዘግቧል።


https://t.me/Ethioallball


ማድሪድ ከሳንቲያጎ በርናቦ ስንት ያገኛል ?

የሪያል ማድሪዱ ሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ጥገናው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለሁሉም አገልግሎት ዝግጁ መሆኑን ተከትሎ ከፍተኛ ገቢ እንደሚያስገኝ ተነግሯል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ባለፈው የ 2023/24 የውድድር ዘመን ከሳንቲያጎ በርናቦ 307 ሚልዮን ዩሮ ገቢ ማግኘታቸው ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድ አሁን ላይ ከሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም በቀን 1️⃣ ሚልዮን ዩሮ ገቢ እንደሚያገኙ ተገልጿል።

በተጨማሪም በጨዋታ ቀን ስታዲየሙ የሚያስገኘው ገቢ 10 ሚልዮን ከፍ እንደሚል ተዘግቧል።

ሪያል ማድሪድ በያዝነው የውድድር ዘመን ከስታዲየሙ ጨዋታ ቀን ገቢ ፣ ከዝግጅቶች ሌሎች ገቢዎች 354 ሚልዮን ዩሮ ያገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

https://t.me/Ethioallball


“ 1ለ0 ማሸነፍ መልመድ አለብን “ ማሬስካ

የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቡድናቸው ጨዋታዎችን በጠባብ የነጥብ ልዩነት ማሸነፍ መማር እንዳለበት ተናግረዋል።

ኢንዞ ማሬስካ በንግግራቸውም " ጨዋታዎችን እንዴት 1ለ0 ማሸነፍ እንዳለብን መማር አለብን ትልቅ ቡድኖች ይህንን ያደርጋሉ “ ሲሉ ተደምጠዋል።

ከኤፌ ካፕ መውጣታቸውን " የሚያሳፍር ነው " ሲሉ የገለፁት ኢንዞ ማሬስካ አሳፍሮናል ነገርግን ጥሩ ነገርም አለው ሊጉ እና ኮንፈረንስ ሊግ ላይ ማተኮር እንችላለን ብለዋል።

አሰልጣኙ አክለውም ሬስ ጄምስ ከጨዋታው ውጪ የነበረው በጉዳት አለመሆኑን እና ልምምድም መስራቱን አስረድተዋል።

https://t.me/Ethioallball


የጨዋታ አሰላለፍ !

5:00 ሪያል ማድሪድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ


አንቶኒ ለሁለተኛ ጊዜ የጨዋታው ኮከብ ተባለ !

ከማንችስተር ዩናይትድ ለሪያል ቤቲስ በውሰት በመጫወት ላይ የሚገኘው አንቶኒ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል።

ሪያል ቤቲስ ዛሬ በሴልታ ቪጎ 3ለ2 በተሸነፈበት ጨዋታ አንቶኒ የመጀመሪያ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

ብራዚላዊው ተጨዋች አንቶኒ በጨዋታው የጨዋታው ኮከብ በመባል መመረጥም ችሏል።

አንቶኒ በሪያል ቤቲስ ምን አሳካ ?

- ሁለት ጨዋታዎች አደረገ

- በሁለቱም ጨዋታዎች የጨዋታው ኮከብ ተባለ

- አንድ ጎል አስቆጠረ


ማንችስተር ሲቲ ቀጣዩን ዙር ተቀላቀለ !

ማንችስተር ሲቲ ከሌይተን ኦሬንት ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ አራተኛ ዙር ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች አብዱኮድር ኩሳኖቭ እና ኬቨን ዴብሮይን ሲያስቆጥሩ ለሌይተን ኦሬንት ኦርቴጋ በራሱ መረብ ላይ አግብቷል።

አዲሱ ፈራሚ አብዱኮድር ኩሳኖቭ ለማንችስተር ሲቲ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል።

ሌላኛው አዲስ ፈራሚ ኒኮ ጎንዛሌዝ ጉዳት አጋጥሞት ከእረፍት በፊት ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል።

ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ወደ እንግሊዝ ኤፌ ካፕ አምስተኛው ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።


የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

9:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ መቻል

9:15 ሌይተን ኦሬንት ከ ማንችስተር ሲቲ

12:00 ሀድያ ሆሳዕና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

12:00 ኤቨርተን ከ በርንማውዝ

2:00 ኢምፖሊ ከ ኤሲ ሚላን

5:00 ብራይተን ከ ቼልሲ

5:00 ሪያል ማድሪድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ


ቼልሲ ፓልመርን ወደ ስብስቡ አካቷል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በቀጣይ ለሚያደርጓቸው የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ጨዋታዎች ኮል ፓልመርን ማካተቱ ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ለኮል ፓልመር እረፍት ለመስጠት ከመጀመሪያው ዙር የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ስብስብ ውጪ አድርገውት እንደነበር ይታወሳል።

በተጨማሪም ትሬቮህ ቻሎባህ እና ማቲስ አሞጉ ወደ ስብስቡ መካተት ችለዋል።

በሌላ በኩል ሮሚዮ ላቭያ እና ዌስሌይ ፎፋና በጉዳት ምክንያት ለቀሪው የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ውድድር በስብስቡ አልተካተቱም።


የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ታውቋል !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ ጥር የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የበርንማውዙ ዋና አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ የፕርሚየር ሊገ የወርሀ ጥር የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ በመሆን መመረጣቸው ይፋ ሆኗል።

አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ በዘንድሮው የውድድር አመት ለመጀመሪያ ጊዜ የፕርሚየር ሊጉ ምርጥ አሰልጣኝ ሽልማት መቀበል ችለዋል።


ቼልሲ ተጨዋቾቹ ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ ይርቃሉ ?

የሰማያዊዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ማርክ ጉዩ በዌስትሀም ጨዋታ ጉዳት እንዳጋጠመው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ አረጋግጠዋል።

ማርክ ጉዩ ያጋጠመው ጉዳት ከባድ መሆኑን እና ለረጅም ጊዜ ከሜዳ የሚያርቀው ሊሆን እንደሚችል አሰልጣኙ አያይዘውም ገልጸዋል።

በጨዋታው የተጎዳው ሌላኛው አጥቂ ኒኮላስ ጃክሰን ያጋጠመው ጉዳት “ የከፋ አይደለም “ ያሉት ኢንዞ ማሬስካ በነገው የብራይተን ጨዋታ ሊደርስ ይችላል ብለዋል።

“ ሮሚዮ ላቪያ አሁንም በማገገም ላይ ነው አሁንም ወደ ሜዳ ለመመለስ የተወሰነ ጊዜ ይወስድበታል “ ኢንዞ ማሬስካ


የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታወቀ !

ሀያ ሶስተኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ ጥር የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት የበርንማውዙ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጀስቲን ክላይቨርት የወርሀ ጥር የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጡ ተገልጿል።

ጀስቲን ክላይቨርት በወሩ ባደረጋቸው የሊግ ጨዋታዎች #አምስት ግቦችን አስቆጥሮ #ሁለት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።


“ እድል ያላገኙ ተጨዋቾችን እንጠቀማለን “ አርኔ ስሎት

የሊቨርፑሉ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በእሁዱ የፕሌይ ማውዝ የኤፌ ካፕ ጨዋታ ለወጣት ተጨዋቾች እድል እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

“ የትኛውም የኤፌ ካፕ ጨዋታ ከባድ ነው “ ያሉት አርኔ ስሎት " እነሱ በሜዳቸው ነው የሚጫወቱት የፍፃሜ ጨዋታቸው ነው " ብለዋል።

አሰልጣኙ አክለውም " የጨዋታ እድል ላላገኙ ተጨዋቾች እድል እንሰጣለን በምንፈልጋቸው ሰዓት ዝግጁ ይሆናሉ “ ብለዋል።

“ አርኖልድ ለረጅም ጊዜ ከሜዳ አይርቅም ነገርግን የእሁዱ ጨዋታ ይፈጥንበታል በቀጣይ ጨዋታ ብቁ ከሆነ ይሰለፋል።“ አርኔ ስሎት


UEFA በቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ላይ ተጨማሪ ሰአትን ለመሰረዝ እያሰበ ነው - ጋርዲያን ስፖርት

በዚህ ሁኔታ ቡድኖቹ ወዲያውኑ ፍፁም ቅጣት ምት ይመታሉ.


የዋህ አይደለሁም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነን “ አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድኑን ከመረከቤ በፊት ስለሚመጣው ጫና አውቅ ነበር በማለት ተናግረዋል።

“ እኔ የዋህ ሰው አይደለሁም “ የሚሉት አሞሪም “ ብዙ ጊዜ ተናግሬያለሁ እግርኳስ በውጤት ላይ የተመሰረተ ስፖርት ነው  “ ሲሉ “ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ነን “ ብለዋል።

አሰልጣኙ አክለውም “ የሚገጥመን አስቸጋሪ ሁኔታ እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ ይቀጥላል “ በማለት ተናግረዋል።

“ ጫናው የሚጠበቅ እና አስደሳች ነው ፤ ቡድኑን ለመረከብ ስስማማ ይህ እንደሚገጥመኝ አውቅ ነበር።“ ሩበን አሞሪም

ስለ ራሽፎርድ የተጠየቁት አሰልጣኙ “ እሱ አሁን የአስቶን ቪላ ተጨዋች ነው ይህንን ጥያቄ እነሱን መጠየቅ ትችላላችሁ " ሲሉ ለጋዜጠኞች መልሰዋል።


https://t.me/Ethioallball


ማርሴሎ በይፋ ጫማውን ሰቀለ !

ብራዚላዊው የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ታሪካዊ የመስመር ተጨዋች ማርሴሎ ራሱን ከፕሮፌሽናል እግርኳስ ማግለሉን አስታውቋል።

ማርሴሎ በ 36ዓመቱ ጫማውን መስቀሉን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ አድርጓል።

ማርሴሎ በእግርኳስ ህይወቱ 7️⃣2️⃣1️⃣ ጨዋታዎች ሲያደርግ 5️⃣8️⃣ ጎሎችን አስቆጥሮ 1️⃣1️⃣7️⃣ አመቻችቶ አቀብሏል።

ማርሴሎ በእግርኳስ ህይወቱ ለክለቡ እና ሀገሩ አጠቃላይ 3️⃣1️⃣ ዋንጫዎችን በማሸነፍ ደመቅ ታሪክ መፃፍ ችሏል።


https://t.me/Ethioallball

Показано 20 последних публикаций.